ኢትዮጵያ ይህን ያህል Hብ ይዛ ተዘግታ እንድትቀመጥ የሚፈርድ፣የባሕር በር አያስፈልጋትም የምል አካል ይኖራል ብለው እንደማያምኑ፣ የናህር በር ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ዕድገትና ለህዝቦቿ ተጠቃሚነት ወሳኝ መሆኑን በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አብርሃም ንጉሴ (ዶ/ር) ተናግሩ። የአስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔትናሁ ኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባህር ለመመልሰ የምያደገውንጥረት እንደሚደግፉ በገሃድ ማስታውቃቸው አይዘነጋም።
የባህር በር ጉዳይ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ዕድገትና የህዝቦቿን ተጠቃሚነት ለማስቀጠል መፍትሔ ማግኘት እንደሚገባው በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አብርሃም ንጉሴ (ዶ/ር) ገለጹ።
ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት የጀመረችው ሰላማዊ ዲፕሎማሲ አካሄድ ተገቢ መሆኑንም አምባሳደሩ አስገንዝበዋል።
በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አብርሃም ንጉሴ (ዶ/ር) ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ የባሕር በርን ለመጠቀም ያቀረበችው ጥያቄ በሰላማዊ የዲፕሎማሲ አካሄድ የቀረበ ነው።
ኢትዮጵያም የባሕር በርን ለመጠቀም ያቀረበችው ጥያቄ አስፈላጊና መሰረታዊ ጉዳይ መሆኑን ጠቁመዋል።
ለኢትዮጵያ የባሕር በር ማግኘት ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር የሚኖርባት እና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማስቀጠል የሚያግዝ መሆኑን ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያን የባሕር በር መሻት ለፍትሕ ቀናዒ የሆኑ የዓለም አገሮች ሁሉ በትክክል ያዩታል የሚል እምነት አለኝ ያሉት አምባሳደር አብርሃም፤ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር የተሸከመች ሀገር የባህር በር አጥታ ልትኖር አይገባትም ብለዋል።
የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄም እያደገ የመጣውን ኢኮኖሚ ለማስተናገድ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህን ሁኔታ የማይረዳ መንግስትም ሆነ አገር ስለማይኖር በሰላማዊ የዲፕሎማሲ አካሄድ መፍትሔ የሚያገኝ ጉዳይ መሆኑንም ተናግረዋል።
© EBC