የግብፅ ፕሬዝዳንት አብደልፋታህ ኤል ሲሲ በጅቡቲ ሰሞኑን ጉብኝት ማድረጋቸው ጥቂት ግለሰቦችን ያሳሰበ ይመስላል፡፡ ግብፅ በጅቡቲ ውስጥ የምታደርጋቸው እንቅስቃሴዎች በተደጋጋሚ የከሸፉ መሆናቸውን ማጋራቱ ጠቃሚ ነው።
• ነፃ ንግድ ቀጣና
ግብጽ በጅቡቲ ነፃ የንግድ ቀጠና (Free Zone) ያገኘችው ከዛሬ 10 ዓመት በፊት እ.ኤ.አ በ2016 የግብጽ ፕሬዝዳንት አብዱልፋታህ ኤል ሲሲ እና ጅቡቲው ፕሬዝዳንት ኦማር ጌሌ ካይሮ ላይ ልዩ የኢኮኖሚና የቴክኒክ ትብብር ስምምነት ( Special economic and technical cooperation agreement ) በተፈራረሙበት ጊዜ ነው።
የግብጽ ሚኒስትሮች ከተለያዩ ዘርፎች የተውጣጡ የግል ባለሀብቶችን ወደ ጅቡቲ በመውሰድ ኢንቨስት እንዲያደርጉ በማለም ነፃ ንግድ ቀጣናውን አስጎብኝተዋቸዋል። ሆኖም የግል ባለሀብቶቹ በነፃ ንግድ ቀጣናው ኢንቨስት ማድረግ አዋጭ አለመሆኑን ለመንግስታቸው እቅጩን ተናግረዋል።
በእርግጥም የግብፅ የነፃ የንግድ ቀጣና አዋጭ አይደለም። ምክንያቱም አንደኛ፣ ጅቡቲ ውስጥ የፍጆታ ዕቃዎች (ዘይት፣ ስኳር፣ ዱቄት፣ ስንዴ፣ ሩዝና ሌሎች) በሌሎች ነፃ ንግድ ቀጣናዎች ውስጥ በሚንቀሳቀሱ የኢትዮጵያና ጅቡቲ ባለሃብቶች እንዲሁም በጥቂት ኤርትራውያን በመያዙ ለግብፃውያን የሚፈጠር ተጨማሪ የገበያ እድል የለም። ሁለተኛ፣ የጅቡቲ ነፃ ንግድ ቀጣናዎች ዋነኛ ገበያ ኢትዮጵያ ናት። ስለሆነም የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን፣ ብሔራዊ ባንክ፣ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር በጋራ መመሪያ አውጥተው x ከተባለ የግብጽ freezone ወደ ኢትዮጵያ ምርት እንዳይገባ ማለት ይችላሉ። as simple as this! ከጂቡቲ ሌላ የትም market access ስለሌለ በአንድ ጊዜ ከስረው ይወጣሉ ማለት ነው።
• የባንክ ዘርፍ
ሌላው ግብፅ የወደቀችበት ጉዳይ የባንክ ቢዝነስ ነው። የውጭ ምንዛሬ ለመቸብቸብ እና ንግድ ለማሰላጥ በማሰብ Bank Misrን በጅቡቲ ከፈቱ ሶስት ዓመት ሆናቸው። እስካሁን ያለውን እንቅስቃሴ ስናይ በአራዳ ቋንቋ “ወፍ የለም”፡፡ በጅቡቲ ውስጥ እድሜ ጠገብ ከሆኑት BCMIR፣ CAC፣ SAALAM BANK፣ EXIM BANK ወዘተ ጋር ተወዳዳሪ የሚያደርገው ካፒታልም፣ ልምድም መልካም ስምም የለውም።
ጂቡቲ ውስጥ የሚገኙ ባንኮች ጭራሽ እንደ ነጋዴ ሸቀጣሸጥ ንግድ ውስጥ የተሰማሩ ናቸው። የግብጽ ባንኮችም ነፃ የንግድ ቀጣናውን እንደ ሰበብ በመጠቀም ሊገቡበት ይችላሉ።
• የአየር በረራ ጉዳይ
ሌላው ግብፅ በጅቡቲ ሞክራ የከሸፈባት ጉዳት የበረራ ጉዳይ ነው። Egypt Air ከስመ ጥሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዲሁም ከባህረ ሰላጤው ሀገራት አየር መንገዶች ጋር የመወዳደር ታሪክም፣ አቅምም መልካም ስምም የለውም።
ግብፅ በጅቡቲ ውስጥ ያላት እውነተኛ ዓላማ
በግብፅ ከፍተኛ ባለስልጣናት ወደ ጅቡቲ የሚደረጉ ጉብኝቶች ዓላማ ከጅቡቲ ጋር የትምህርት እድል፣ የንግድ፣ የመገናኛ፣ የባህል ወዘተ ግንኙነትን ማጠናከር ነው በሚል ቢነገርም እውነታው ግብፅ ጅቡቲ ውስጥ የምትመጣው ኢትዮጵያን በተቻላት መጠን ከቀይ ባህር ለማራቅ እንዲሁም ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝና ላይ ያላትን ፍትሃዊና ምክንያታዊ ተጠቃሚነት ለማስተጎጓል በሚል ከንቱ ምኞት ነው። የታላቁ ህዳሴ ግድብን ለማስቆም ያልፈነቀለችው ድንጋይ አልነበረም፣ እድሜ ለአርቆ አስተዋዩ መሪያችን የግድቡን ሪባን መስከረም ላይ እንቆርጣለን።
ግብፅ ኢትዮጵያን በከበባ ውስጥ በማስገባት ከባህር በር አጀንዳዋ ለማደናቀፍ የምታደርገው እኩይ እንቅስቃሴም በባለራዕዩ መንግስታችን ቁርጠኝነት እንዲሁም በኢፍትሃዊነት ከባህር እንዲርቅ በተደረጉት ኢትዮጵያውያን ብረቱ ጥረት ይከሽፋል።
በጅቡቲ ወታደራዊ ቤዝ ለመመስረት ግብፅ ስትኳን ኖራለች፣ መቼም አይሳካላትም። የጅቡቲ መንግስትም አይፈቅድም፣ ይህ ቢሆን ኢትዮጵያ ጎሮሮዋ ሲዘጋ ቁጭ ብላ እንደማትመለከት እሙን ነው።
ሌላው ግብፅ በጅቡቲ ውስጥ ተቀምጣ የቀይ ባህርን የንግድ መስመር መቆጣጠር ትፈልጋለች። ጅቡቲ ይህንን እንደማትፈቅድ ይታወቃል። ምክንያት ጅቡቲ ከሁቲዎች ጋር በመጋጨት የወደቦቿን እንቅስቃሴ ማስተጓጎል አትፈልግማ !!
እንደ መውጫ
ግብፅ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም መዳከም ተኝታ የማታውቅ ታሪካዊ ጠላት በመሆኗ በጅቡቲም ይሁን በማንኛወም ጎረቤት ሀገር ውስጥ የምታደርጋቸውን እንቅስቃሴዎች በቅርብ መከታተልና ለአስፈላጊው ምላሽ መዘጋጀት ያስፈልጋል
ኢትዮሪቬውን ከታች ባሉት ማስፈንጠሪያዎች የከተሉ – የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ @ethioreview
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ ethioreview
ኤክስ ፡ twitter