የኢትዮጵያ ህክምና ባለሙያዎች ማህበር ችግሮችን ለመፍታት እና መፍትሄ ለመስጠት ከጤና ሚኒስቴርም ሆነ ባለድርሻ አካላት በሚያደርጓቸዉ ጥረቶች አብሮ ለመስራት እና ትብብሩን አጠናክሮ በመቀጠል የመፍትሄዉ አካል ለመሆን ፈቃደኛ እና ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ።
” የጉዳዩ አሳሳቢነት እየጨመረ በመምጣቱ የሚመለከተው አካል አፋጣኝ መፍትሔ ይስጥበት ! ” ሲል ማህበሩ ባሰራጨው መግለጫ አመልክቶ በዝርዝር ሊሆኑ የገባቸዋል ያለውን ምክረ ሃሳብ አስፍሯል።
ማህበሩ በዚሁ ዛሬ ባሰራቸው መግለጫው በአሁን ሰዓት በተወሰኑ የጤና ተቋማት በከፊል የጤና አገልግሎት እየተስተጓጎለ መሆኑን መስማቱን አመልክቷል። የጤና ሚኒስቴር ዘርፉ የስራ ማቆም አድማን የማይደረግበትና በህግ ክልከላ የተጣለበት መሆኑን ማስታወቁ አይዘነጋም።
የጤና አገልግሎት መስተጓጎሉን የገለጸው የማህበሩ መግለጫ፣ ትኩረት ይሻሉ ያላቸውን ጉዳዮች ዘርዝሯል። ማህበሩ ራሱን ጭምር የመፍትሄ አካል በማድረግ ለዘረዘራቸው ጉዳዮች የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲሰጥበት ጥሪ አቅቧል።

ሃኪሞች በሚያነስዋቸው ጥያቄዎች ማለትም የደመወዝ ማነስ፣ ፣የጥቅማጥቅም፣ ፣ የስራ ቦታ ደህንነት እንደ ኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር ተገቢ መሆኑን እንደሚቀበልና ለረጅም ጊዜያት ለሚመለከተው ባለድርሻ አካል ጉዳዩን ሲያቀርብ እና ሲሰራበት እንደቆየ ገልጿል። በአሁኑ ሰዓት ግን የጉዳዩ አሳሳቢነት እየጨመረ በመምጣቱ የሚመለከተው አካል አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጥበት አሳስቧል።
2 . አሁን ያለዉ ሁኔታ ማለትም የጤና አገልግሎቱ እንዲሁም የመማር ማስተማር ሂደቱ በምንም አይነት ደረጃ ቢሆን መስተጓጎሉ ማህበረሰቡን፤ የጤና ባለሞያዉን እንዲሁም የጤና ስርአቱን እጅግ ሊጎዳ የሚችል በመሆኑ ይህ ጉዳይ ወደተባባሰ ደረጃ ከመድረሱ በፊት የጤና ሚኒስቴርና የሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት ከባለሙያዎች ጋር በመሆን አፋጣኝ የሆነ ሃገራዊ ዉይይት በየደረጃዉ እንዲያካሂዱ እና ችግሮቹ በዉይይት እንዲፈቱ እንዲደረግ ማኅበሩ ጥሪ አቅርቧል።
3. ሃኪሞች እንዲሁም የጤና ባለሙያዎች አሁን ካለው ሁኔታ ጋር ተያይዞ በተለያዩ ቦታዎች ለእስር እንደተዳረጉ መሆኑን በመግለጭ ባለሞያዎቹ ከእስር እንዲፈቱ እና ወደስራ ገበታቸዉ ተመልሰዉ ለማህበረሰቡ አገልግሎቱን እንዲሰጡ ቢደረግ የተሻለ እንደሆነ እና በዚህ ረገድ የሚመለከታቸዉ አካላት አስፈላጊዉን እገዛ እንዲያደርጉ አሳስቧል።
4. ማኅበሩ ችግሮችን ለመፍታት እና መፍትሄ ለመስጠት ከጤና ሚኒስቴርም ሆነ ባለድርሻ አካላት በሚያደርጓቸዉ ጥረቶች አብሮ ለመስራት እና ትብብሩን አጠናክሮ በመቀጠል የመፍትሄዉ አካል ለመሆን ፈቃደኛ እና ዝግጁ እንደሆነ አሳውቋል።
5. ኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር፥ በአገሪቱ ሃኪሞች እንዲሁም የጤና ባለሙያዎች የሚነሱ ጥያቄዎችን አስመልክቶ ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት የተለያዩ የሙያ ማህበራትን እና ስፔሻሊቲ ሶሳይቲዎችን በማስተባበር ዉይይት በማድረግ እንዲሁም ሙያ ማህበራቱ ከጤና ሚኒስቴር ጋር ተከታታይ ውይይቶች እንዲያደረጉ በማመቻቸት ጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጠዉና አስቸኳይ መፍትሄ እንዲቀመጥ ጥረት ሲያደርግ እንደቆየ አስታውሷል።
ጤና ሚኒስቴር ማናቸውንም ጉዳዮች በጠረጴዛ ዙሪያ መነጋገር እንደሚቻል ጠቅሶ ጥቂቶች ስራ ላይ የፈጠሩትን መስተጓጎል እንደማይቀበለውና እርምጃ እንደሚወስድ ጠቅሶ በሳምንቱ ማተቃለያ ላይ መግለጫ መስጠቱ የሚታወስ ነው። የተለያዩ የመብት ተከራካሪ ድርጅቶች የታሰሩ የህክምና ባለሙያዎች እንዲፈቱ ጠይቀዋል። በተመሳሳይ ጃዋር መሀመድን ጨምሮ የፖለቲካ ድርጅቶችና በተቃዋሚ ቅጭትና ድጋፍ የሚሰሩ የመንግስት ተቃዋሚ ሚዲያዎች የህክምና ባለሙያዎች ያቀረቡትን ጥያቄ ለማስፋት በዘመቻ እየሰሩ ነው። አንዳንዶቹ ነገ ሰኞ አመጽ እንደሚቀጣተል ምንጭና ማህበሩን ሳይጠቅሱ እየጻፉና እየቀሰቀሱም ነው።