ባርሴሎና እና ላሚን ያማል ኮንትራቱን እስከ ሰኔ 30 ቀን 2031 ለማራዘም ስምምነት ላይ ደርሰዋል ሲል የካታላኑ ክለብ በሰጠው መግለጫ አረጋግጧል። ባርሴሎናን ከላ ማሲያ የወጣቶች አካዳሚ የተቀላቀለው ያማል፤ በ15 ዓመቱ የመጀመሪያ ጨዋታውን ለክለቡ አድርጓል።
ላሚን በቋሚነት ከሚያገኘው ደሞዝ በተጨማሪ በሚያደርጋቸው ጨዋታዎች ፣ በሚስቆጥራቸው ጎሎች እንዲሁም በሚያሸንፈው ባሎንዶር ልክ ቦነስ ይኖረዋል።
ታድያ ላሚን ያማል ገና 18 ዓመት ያልሞላው ሲሆን፤ በአዲሱ ኮንትራት ባርሳ ውስጥ ጉርሻውን ሳያካትት 8 ሚሊዮን ዩሮ እንደሚከፈለው ነው የተዘገበው። ይህም በክለቡ ከፍተኛው ተከፋይ ሊያደርገው ይችላል ሲል ፍራንስ 24 ዘግቧል።