ኢትዮሪቬው ፡- ” የትህነግ ግርድና በዚህ ደረጃ የትግራይን ሕዝብ ያዋረደ ነው” ይላሉ አዲሱ “ጸምዶ” የሰሙ፡፡ “ጸምዶ” መጣመር ወይም መቀናጀት ወይም ቅንጅት እንደማለት ነው፡፡ እንግዲህ ይህ “ጸምዶ” ሲጀመር የሁለቱም ፕሮፓጋንዲስቶች የትግራይና የኤርትራ ወንድማማች ሕዝብ በሚል እንዳይቀሰቀሱ ትህነግ ተስማምቷል፡፡ ይህንኑ መረጃ በይፋ በመጥቀስ የትግራይ ተወላጆች ” ትህነግ ለሻዕቢያ ለመገረድ የገዛ ወገኑን ማዋረድን የስምምነቱ አንዱና ዋናው መስፈርት አድርጓል” ሲሉ እየዘነጠሉት ነው።
ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ የሚለው ትህነግ በልብ ወዳጆቹ ሳይቀር አሁን ላይ የሚጠራው በግርድና የቁልምጫ ስሞች ነው፡፡ ትህነግን አምልኮ አድርገው ሲሰግዱለት፣ ሲምሉበትና የምስራቅ አፍሪቃ አብሪ ኮከብ እያሉ ሲያሞካሹት የነበረውን ፓሪያቸውን “የተገረደ፣ ገረድ፣ የፖለቲካ አመንዝራ፣ የሻዕቢያ ሽንት ወዘተ ” እያሉ እየተሳለቁበት ነው፡፡
ደራሲ አስራት አብርሃ “ትህነግ ከሻዕቢያ መፈጠሩ በራሱ ሃጢያት ነው” ይላል፡፡ ፕሮፌሰር ጌታቸው ደግሞ ” ትግራይ ላይ የበቀለ አረም” ሲሉ አቆሽሸውታል፡፡ ትህነግ ለዚህ ደረጃ ውግዘትና የስድብ ውርጅብኝ የተዳረገው “ጭንቅላቱንና አንደበቱን ለሻዕቢያ ሰጠ” በሚል ነው፡፡
በጦርነቱ ወቅት “ውሮ ወሸባዬ” ሲሉ ከነበሩት መካከል አንዱ የነበረው የትህነግ የልብ ወዳጅ ቴዎድሮስ በራሱ ርዕዮት ሚዲያ በተደጋጋሚ ” ካርቶኖች፣ ድንጋዮች” ያላቸው የትህነግ አመራሮች ሻዕቢያ ስር መለጠፋቸውን አስመልክቶ ” ለሻዕቢያ ለመገረድ የራሱን ህዝብ አሳልፎ የሰጠ፣ በዚሁ መስፈሪያ የተሰፈረ፣ አሽከርነትን በቋሚ የፖለቲካ አቋምነት የያዘ” ሲል ክፉኛ ሰድቦ ለተሳዳቢዎች የስድብ ደረጃ መድቦና ሰፍሮ በማውጣት አሳልፎ ሰጥቷቸዋል፡፡ በዚሁ አቅጣጫ መሰረት ትህነግ አሁን ላይ “መገረድና የሚገረድ” እየተባለ በቅብብል ስድብ እየተቀባ ነው፡፡

ቀደም ሲል ገና ከፍጥረቱ ጀምሮ የትህነግ አቋምና ማዕረጉ የገባቸው ድርጅቱ ለትግራይም ሆነ ለተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ መከራ እንደሆነ ሲናገሩ ሰሚ አልነበረም፡፡ እንደውም ስለም ተነፈሱ ተብለው በጸረ አብዮታዊ መስመርተኝነት ተፈርጀው መከራ የተቀበሉ አሉ፡፡ ነብስ ይማር ፕሮፌሰር አስራትና ሌሎች።
ዛሬ ከግማሽ መዕተ ዓመት በሁዋላ አምላኪዎቹ ዓይናቸው ተገለጠ፡፡ ትህነግ የተሰራበትን የዘር ሽንት ገባቸው። እናም ” እርም፣ ለኢትዮጵያም ሆነ ለትግራይ መከራ የሆነ፣ ከሻዕቢያ ችንት የተጸነሰ፣ ተጸንሶም ጊዜውን ሳይጨርስ የተወለደ ሾተላይ ” መሆኑን በራሳቸው አንደበት ገለጹት። ትህነግን “ለምን ተነካብን” በሚል ሲገድሉ፣ ሲያስሩ፣ ሲያሰድዱ፣ ሲያባርሩና ሲያሸማቅቁ የነበሩ ዛሬ ነቁና በሰልፍ በተመረጡ የውረደት መስፈራያ እየሰፈሩት ነው፡፡
ምንም እንኳን የነቁት አንድ ሚሊዮን የትግራይ ህዝብ ካለቀና የትግራይ ሕዝብ ትርጉም በሌለው ጦርነት ማቅ ከለበሰ፣ ከተፈናቀለ፣ በራሳቸው መረጃ መሰረት 120 ሺህ የሚሆኑ ሴቶች ከተደፈሩ፣ ድፍን ትግራይ በሻዕቢያ ሙልጭ ተደርጋ ከተዘረፈች በሁውላ መሆኑ ቢቆጭም እንዳልረፈደ ብዙዎች እየገለጹ ነው።
ሃፍረት የማያውቃቸው ካድሬዎች ትናንት ” ጦርነት ለትግራይ ባህል ነው፡፡ የባህል ጨዋታችን ነው” እያሉ ሲቀሰቅሱ የነበሩትን ሰምተው፣ “ግን ለምንድን ነበር የተዋጋነው? ተዋግተን ምን አገኘን? አንድ ዓመት ቆይተን ምርጫ ብናደርግ ምን ችግር ነበረው? ወደ ጦርነት የከተተን ጉዳይ ምን ነበር? ” የሚሉ ድምጾች ከትግራይ መሰማታቸው የትህነግ ግብአተ መሬት መቃረቡን የሚያሳይ ሆኗል፡፡
ደራሲ አስራት አብርሃ “እያደር እየወደቀ የነበረው ትህነግ መጥፊያውን ያፋጠነው ከሻዕቢያ ጋር ዳግም ግንኙነት የጀመረ ዕለት ነው ” ይላል፡፡ አክሎም “ከአሁን በሁዋላ ትህነግ እንደ ፓርቲ ይቀጥላል ብዬ አላስብም” ሲል ርዕዮት ላይ ተናግሯል። ትህነግ ከፍጥረቱ ጀምሮ ከሻዕቢያ ጋር ያደረገው ግንኙነት በሙሉ ከሃጢያት ጋር የሚመደብ እንደሆነም አመልክቷል።
ትግራይን ማቅ እንድትለብስ ያደረገውን ጦርነት ሲያቀጣጥሉ ከነበሩ፣ በቅስቀሳው ተታለው ከገቡበትና ለይስሙላ በትህነግ ስራ አስፈጻሚ ውስጥ ከነበሩት ሰዎች መጨረሻ ላይ የተሰማው ምስክርነት የደራሲ አስራት አብርሃን ድምዳሜ አመልካች ነው፡፡
በክህደት ሽንት ተወልዶ በክህደት ባህር እየሰመጠ ያለው ትህነግ
“ጦርነቱ ተጀምሮ የኢትዮጵያ ወታደሮች እየተዋደቁ ባለበት ቅፅበት አገሪቱ (ኢትዮጵያ) ሳታውቅ መለስ ወደ አስመራ ሄዶ ነበር። አንድ መሪ አገሪቱ በመሰል ወሳኝ ሁነት ውስጥ እያለች ከወታደራዊ ካውንስልም ሆነ ከካቢኔው ዕውቅና ውጪ በግሉ ወስኖ በግሉ የሚፈፅመው ምንም አይነት ተነሳሽነት ሊኖረው ተገቢ አልነበረም። መለስ ግን አድርጎታል። ጦርነቱ ኤርትራን እንደሚጎዳ ስላወቀ የተጀመረው ጦርነት እንዲቆም ኢሳያስን ለማሳመን ነበር ወደ አስመራ የሄደው። በነገራችን ላይ መለስ ዜናዊ ኤርትራን የሚመለከትበትና የሚያስተናግድበት መንገድ በፃድቃንና በስዬ ተደጋጋሚ ወቀሳና ትችትን አስተናግዷል” የሚለን ጠባቂያቸውና አብሯቸው ከአቶ መለስ ጋር አስመራ ሲመላለስ የነበረው ሚኪ ራያ ነው፡፡
አቶ ስብሃት ነጋ በአንድ ወቅት ኤርትራዊ የሆኑ፣ ግማሽ ኤርትራዊ የሆኑ፣ አመራር ላይ እንዳሉ፣ እሳቸውም ኤርትራዊነት እንዳለባቸው ጠቅሰው እንደመሰከሩት ኢትዮጵያ ትነዳ የነበረው ግርድናን ክብራቸው ባደረጉ ከሃጂዎች መሆኑን ያሳያል፡፡
ይህ ከበረሃ ጀምሮ እንደ ቋሚ የፖለቲካ አቋም የተያዘው በበታችነት ለሻዕቢያ ገረድ ሆኖ የማገልገል አቋም፣ በኤርትራ አንድ ባህል እንዲገነባ ምክንያት ሆኗል፡፡ ባህሉም ሃውልት ሆኖ ወደ አምልኮ ተቀይሯል፡፡ ትህነግ አማራን በጠላትነት ፈርጆ ሲያስተምር፣ ሻዕቢያ ትግሬዎችን የሚያቆሽሽ ትምህርት ለኤርትራ አዲስ ትውልድ ይግት ነበር።
የርዕዮቱ ቴዎድሮስ ትህነግ በሙሉ ስልጣኑ ፈላጭ ቆራጭ ሆኖ ኢትዮጵያን ሲመራ በነበረበት ወቅት ይፈጽም የነበርረውን እያወቀ አይውቅም ነበር፡፡ አዲስ አበባ ተቀምጦ የኪነት ዝግጅቶችን እያደመቀ ለሌሎች ስቃይ “ጥሪ አይቀበልም” ባይ ነበር። ትህነግ የአገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የክደት ጦርነት ከፍቶ ትግራይን ለሻዕቢያ መፈንጫ ካዳረገው ጦርነት ውጤቱ በሁዋላ እንደ በርካቶች 360 ዲግሪ የዞረው ቴድሮስ፣ ሻዕቢያ የትግራይን ተወላጅ ወገኖቻችንን እንዴት እንደሚያቸው በቁጭት ይናገራል።
ዛሬ “ሲፈጠር ጀምሮ ገረድ፣ የተገረደ” ሲል የነበረው ቴዎድሮስ የሻዕቢያን ወንጀሎች እየደረደረ እንዳለው ከሆነ ለኤርትራ አዲስ ትውልድ ከህጻንነት ጀምሮ የትግራይ ተወላጆችን ” ድሃ፣ ጅል፣ የአዕምሮ ዝግመት ያለባቸው፣ ኋላ ቀሮች፣ ወዘተ” እያሉ ያስተምሯቸዋል፡፡ ከትግራይ ዱቄት፣ ጭልፋ፣ ሲኒ፣ በር፣ መስኮት፣ ልብስ፣ ጫማ … ምንም ሳይመርጡ የዘረፉ የድጋይ ዘመን ነዋሪዎች ሌሎችን “ደሃ” እንዲሉ የሚያስተምሩ የዘመን ዘገምተኞች ደጅ ሄዶ የተደፋውን ትህነግን ክፉኛ የሚሰድቡና የሚቃወሙ ዋና መነሻሸው ይህ ነው።
እንግዲህ በዚህ ደረጃ የትግራይን ሕዝብ የሚያየው ሻዕቢያ ነው ዳግም ትግራይ ላይ ሊፏልል የተፈቀደለት፡፡ ትህነግ የመከላከያ ሰራዊትን በክህደት ሲመታና መከላከያ ራስን በማዳን ግብግብ ሲወጠር በዚያ መካከል ዘሎ ትግራይን የተቆጣጠረው የሻዕቢያ ሰራዊት የትግራይን ሕዝብ በትዕዛዝ ጨፍጭፏል፡፡ የቻለውን ንብረት ሁሉ አግዟል፡፡ ማጋዝ ያልቻለውን አውድሟል፡፡ 120 ሺህ ሴቶችን ደፍሯል፡፡ ያላደረገው የለም፡፡ ይህን የግፎች ሁሉ እናት ነው እነ ደብረጽዮን ዳግም እየሰገዱለት ያሉት፡፡ የእነ ደብረጽዮን ፕሮፓጋንዲስቶችም ” ወንድም ሕዝብ እንዳትሉን” እየተባሉ ሻዕቢያ እግር ስር የሚነደባለሉት።

ኢትዮጵያዊያንን የጥርሳቸው ወርቅ ሳይቀር እየነቀለ፣ ያሳደደ ልክስክስ፣ ደሃ፣ ማጅራት መቺ፣ ወሮበላ፣ ደንቆሮና ወንበዴ ቡድን ደጅ የሚጠናው የትህነግ ጉራጅ፣ ገና ከጅምሩ ካሻዕቢያ የቀረበለትን አስገዳጅ ጉዳይ ደም የሚያንተከትክ ነበር፡፡
በዓለም ላይ ጨለማ፣ ሰዓት የቆመባት፣ ምንም ዓይነት የስልጣኔ ምልክት የማይታይባት፣ ወደ ዘመነ ድንጋይ የተቀየረች፣ ዜጎቿ ዓለምን ረስተው በኢሳያስ ቡራኬ ብቻ የሚኖሩባት፣ አገር ላይ ሆኖ “የትግራይና የኤርትራ ሕዝብ ወንድማማች ህዝብ ነው አትበሉ” የሚል ቱልቱላ ለሚነፋ ረሃብተኛ ቡድን ያፈነደደው የደብረጽዮን ቡድን መሳቂያና መሳለቂያ፣ እንዲሁም የዘመን ሁሉ የሃፍረት ትርጉም ማስተማሪያ እንደሚሆን የተበሳጩ እየገለጹ ነው፡፡
ገና ሲመሰረት ጀምሮ ሻዕቢያ የትግራይን ህዝብ ማጥፋት የፕሮግራሙ የማዕዘን ድንጋይ ነው፡፡ ይህን አቋሙን ከበረሃ ጀምሮ ረሃብ ለሚያሰቃያቸው የትግራይ ተወላጆች እህል እንዳይተላለፍ በሩን ከርችሞባቸዋል። ከእነ ስብሃት ጋር እየተስማማ የትግራይን ተወላጆች ማግዷል። አገር ሰላም በነበረበት ወቅት ወረራ ፈጽሟል፡፡ ንጹሃንን ጨፍጭፏል፡፡ በቅርቡ በተካሄደው ጦርነት ትግራይን አውድሟል። በጅምላ ሴት፣ ወንድ፣ አዋቂ፣ ትንሸ፣ትልቅ፣ ሳይል ጨፍጭፏል፡፡ እህቶቻችንን ዕድሜ ሳይለይ ደፍሯል። እናም ለዚህ በተደጋጋሚ ውንብድና ለፈጸመ ወነጀለኛና አረመኔ ቡድን ድጋሚ መገረድ የትህነግን የፖለቲካ ጋለሞታነት፣ ለሻዕቢያ ዓላማ መሳካት ኮማሪት የመሆን ታማኝነቱን የሚያሳይ ይሆናል።
ለሻዕቢያ ህልውና የትግራይ ሕዝብን አሳልፎ የመስጠት ሃይማኖት የሚከተለው ትህነግ ዛሬ ላይ በትግራይ ተወላጆች ዘንዳ በስፋት እየተተፋ ነው፡፡ አስራት አብርሃም እንዳለው በመክሰሚያው ማውዜማ ላይ ነው፡፡
“ከጅምሩ ጉባኤ ከማድረጋችን በፊት ጦርነቱን አስመልከቶ ስንከተል የነበረውን አካሄድ እንገምግም” ለሚለው ጥያቄ ፈቃደኛ ሳይሆን ራሱን አንጃ ማድረግ የመረጠው የደብረ ጽዩን ትህነግ፣ አንጃም ሳይሆን በፊት ትግራይን ለሻዕቢያ አሳልፎ የመስጠት አሳብ ይዞ በውጭ አገር በሚገኙ የድርጅቱ አባቶች አማካይነት ይወያይ እንደነበር መረጃ እየወጣ ነው።
አቶ ስብሃት ነጋ ከእስር ከመለቀቃቸው በፊት በተደረገላቸው ክብካቤ ከሞት ወደ ሕይወት ሲመለሱ የትህነግን ሙሉ መረጃ ትምባሆዋቸውን እያቦነኑ ለመንግስት ተርከዋል፡፡ ኬሪያ ኢብራሂም “ብልጽግና እንኳን እኔን መረጃ ሊጠይቁኝ እኔ ነበር መረጃ ከነሱ ያማገኘው። ሁሉም መረጃ ነበራቸው” ስትል የተናገረችው ምን አልባትም ይህንን ስለምታውቅ ሊሆን ይችላል።
ስብሃት ነጋ ከሞት ወደ ሕይወት ሲሸጋገሩ ከእስር ለመውጣት ራሳቸው ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት የትህነግን ሚስጢር ሁሉ አፍሰዋል። ሌሎችም መጸጸታቸውን በይፋ ገልጸው በተመሳሳይ የሚያውቁትን መረጃ የሰጡ አሉ። እናም የደብረጽዮን ቡድን ለሻዕቢያ ግርድና የአስመራውን አምባገነን ጫማ አውልቆ እግር መላሱ የማይጠበቅ አልነበረም።
“ጸምዶ” አዲሱ የሻዕቢያና የትህነግ የግርድና ጥምረት እየተባለ የሚነገርለት አዲሱ ትግራይን አሳልፎ ከነክብሯ ለሻዕቢያ የመስጠት ህልም “አሰብን ለትግራይ” በሚል የድንቁርና ቅስቀሳ እያታጀበ ነው። የቀይ ባህር ኢትዮጵያዊ አፋር ይህን ዜና ጥርሱን እየፋቀ እየሰማው ነው። ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ “ዝግጅታችን ጨርሰናል” ሲሉ የተናገሩትን የትህነግ በቀቀኖች አልሰሙም። ዝግጅቱ ለማን ይሆን? አየር ኃይልን ወደ ቀድሞ ማማው የመለሱት ይልማ መርዳሳ በዚሁ ሳምንት ምን አሉ?
ኢትዮሪቬውን ከታች ባሉት ማስፈንጠሪያዎች የከተሉ – የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ @ethioreview
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ ethioreview
ኤክስ ፡ twitter