ማናቸውም የውጭ ግንኙነቶች ማካሄድ ስህተት ብቻ ሳይሆን አደገኛም እንደሆነ ጠቅሶ አዲስ የተዋቀረው የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር መግለጫ አወጣ። በቀድሞ ሌተናል ጄነራል የሚመራው አዲሱ አስተዳደር ይህን መግለጫ ያወጣው በዶክተር ደብረጽዮን የሜመራው የትህነግ አንድ ክፋይ ከሻዕቢያ ጋር መርህ አላባና ኢህገመንግስታዊ ግንኙነት እያደረገ መሆኑን ተከትሎ በየአቅጣጫው የተነሳበትን ተቃውሞ ተከትሎ ነው።
“የትግራይ ህዝብ ህልውናውንና ሀገራዊ ጥቅሙን ለማረጋገጥ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል በማድረግ ላይ ነው። ዋናው ጥያቄው የፕሪቶሪያ ስምምነት ሳይጣስ ተግባራዊ እንዲሆን እና ጥቅሞቹ እና መብቶቹ ከጦርነት ስጋት እንዲጠበቁ ነው” ያለው መግለጫው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የትግራይን ህዝብ መሰረታዊ ጥያቄዎች ለመመለስና ሰላሙንና ደህንነታቸውን ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን አመልክቷል።
በዚህም መሰረት ልዩነቶቻችንን ከፌዴራል መንግስት ጋር ብቻ ሳይሆን ከማንኛውም ሃይል ጋር በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ ለመፍታት የተቻለውን ሁሉ ጥረት ማድረግ ተገቢ እንደሆነ መግለጫው አስታውቋል። “ነገር ግን” ይላል መግለጫው፣ ” ነገር ግን ከላይ ከተጠቀሱት መርሆዎች እና እምነቶች ውጭ ያሉ ማናቸውም የውጭ ግንኙነቶች ስህተት ብቻ ሳይሆን አደገኛም ናቸው። እንዲህ ዓይነቱ ድርጊት በማንኛውም ሁኔታ ተቀባይነት እንደሌለው ልብ ሊባል ይገባል” በማለት የድርጊቱን ተዋንያኖች በስም ሳያነሳ አስጠንቅቋል።
ከማንኛውም የውጭ ኃይል የሚደረግ ዓላማው እና ስትራቴጂካዊ ስልቱ ያልታወቀ ግንኙነት ተቀባይነት እንደሌልው በይፋ በማህበራዊ ገጹ ያስታወቀው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር፣ ቃለ የገባቸውን ነጥቦች ወደ ሁዋላ በመተው ከአፈንጋጩ ኃይል ጋር በመሆን የሴራ ተሳታፊ ሆኗል በሚል ለሚተቹት ሁሉ ግራ ያጋባ ማስጠንቀቂያ ማውጣቱ ከሻዕቢያ ወገን ከፍተና ተቃውሞ ሊያስነሳ እንደሚችል ተገምቷል።፡
እንዲህ ያለው መርህ አልባ አካሄድና ግንኙት የትግራይ ክልልን መንግስት አልባ የሚያደርግ አደገኛ አካሄድ መሆኑን ጊዜያዊ አስተዳደሩ በግልጽ አስታውቋል። ይህ ገለጻው ሕዝብ ጦርነት እንደማይፈልግ ካሳየው ስሜትና ሻዕቢያ ትግራይን የጦርነት አውድና በማድረግ ዓላማውን ለመስፈጸም እያሴረ መሆኑን እየገለጹ ሲወተውቱ ከነበሩት ጋር የሚስማማ ሆኗል።
የትግራይ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ዛሬ ከሰዓት ባወጣው መግለጫ ነው። የትግራይ ህዝብ ህልውናና ጥቅም ይከበር ዘንዳ የፕሪቶሪያው ስምምነት ሳይሸራረፍ ተግባራዊ ይደረግ ዘንዳ እንደሚሰራ አመልክቷል።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በጥቅምት 2015 ዓ.ም በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ከተማ የተፈረመው የግጭት ማቆም ስምምነት የፈጠረውን ዕድል ተፈጻሚ ለማድረግ በእንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝም ቢሮው በመግለጫው ላይ አመልክቷል። የትግራይ ህዝብን ጥቅሞችን እና መብቶች ለማስከበር እንዲሁም ከጦርነት ስጋት እንዲጠበቅ ለማድረግ ጊዜያዊ አስተዳደሩ እየሰራ መሆኑንም ቢሮው አክሏል።
ከፌዴራል መንግስት ጋር ብቻ ሳይሆን ከማንኛውም ኃይል ጋር የሚኖሩ ልዩነቶች ለመፍታት፤ “በሰላማዊ” እና “ህጋዊ መንገድ” “የተቻለውን ሁሉ ጥረት” ማድረግ ተገቢ መሆኑንም መግለጫው አትቷል። ሆኖም “አላማው እና ስትራቴጂካዊ ስልቱ ያልታወቀ”፤ ከማንኛውም የውጭ ኃይል ጋር የሚደረግ ግንኙነት “ተቀባይነት እንደሌለው” ጊዜያዊ አስተዳደሩ ገልጿል።
“ከመርሆዎች እና እምነቶች ውጭ ያሉ ማናቸውም የውጭ ግንኙነቶች፤ ስህተት ብቻ ሳይሆን አደገኛም ናቸው” ሲል ጊዜያዊ አስተዳደሩ በዛሬው መግለጫው አጽንኦት ሰጥቷል። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን በአሁኑ ወቅት እየመሩ የሚገኙት ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ፤ ስልጣኑን በተረከቡበት ስነ ስርዓት ላይ የፈረሙት “የቃል ኪዳን ሰነድ” እነዚህን መሰል ግንኙነቶች እና እንቅስቃሴዎች እንዲቆሙ የሚያስገድድ ነው።
ባለፈው መጋቢት ወር መጨረሻ የተፈረመው ይኸው ሰነድ፤ ጊዜያዊ አስተዳደሩ “ከህገ መንግስታዊ፣ ከህጋዊ ስርዓት፣ ከሀገር ሉዓላዊነት እና ከፕሪቶሪያ ስምምነት ያፈነገጡ ግንኙነቶች እና እንቅስቃሴዎች እንዲቆሙ ማድረግ” ሊፈጽማቸው ከሚገባቸው ተልዕኮዎች መካከል አንዱ መሆኑን ዘርዝሯል። ይህ ስምምነት በተፈረመ ሁለት ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ለሚመራው የህወሓት ጎራ ድጋፍ በመስጠት የሚታወቅ አክቲቪስት፤ “የኤርትራ መንግስት ፕሮፖጋንዳዎችን እንደሚያስተጋባ” ከሚነገርለት አርቲስት ጋር በአካል መገናኘቱ መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል።

አወል ሲዒድ ከተሰኘው ኤርትራዊ አርቲስት ጋር የተገናኘው የትግራይ አክቲቪስት፤ “ሰብ ዝሰኣነ ሰብ” (ልፍዓተይ ተስፋ) በሚል ስያሜ በማህበራዊ ትስስር ገጾች በሚያቀርባቸው “አወዛጋቢ ሃሳቦች” የሚታወቀው ብርሃነ ገብረገርግስ ነው። በዛላንበሳ ከተማ የተቀረጸ መሆኑን የተነገረለት በብርሃነ እና በአወል መካከል የተካሄደው ቃለ መጠየቅ፤ ሌተናል ጄነራል ታደሰ የፈረሙትን “የቃል ኪዳን ሰነድ የሚጥስ ነው” የሚል ትችት ሲቀርብበት ቆይቷል።
ቃለ መጠየቁን ያደረገው ብርሃን፤ ባለፈው ቅዳሜ ምሽት በመኖሪያ ቤቱ አቅራቢያ ቦንብ መፈንዳቱን በመግለጽ ድርጊቱ “የግድያ ሙከራ“ መሆኑን በመጥቀስ ውንጀላ አቅርቧል። ይህን ተከትሎ በትላንትናው ዕለት በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው ብርሃነ፤ ዛሬ ሐሙስ መፈታቱ ተገልጿል። የትግራይ ፖሊስ ኮሚሽን ዛሬ በፌስ ቡክ ገጹ ባወጣው መግለጫ፤ ብርሃንን በቁጥጥር ስር ያዋለው ህጋዊ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ በማውጣት እንደሆነ ኢትዮኢንሳይደር ገልጿል።
ብርሃነ የተያዘው “የተጠረጠረበትን ወንጀል ለማጣራት” እንደነበር የገለጸው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን፤ ሆኖም ምርመራውን እንዳያካሄድ በደረሰበት “ከአቅም በላይ የሆነ ጫና” ምክንያት ተጠርጣሪውን ለመልቀቅ መገደዱን አስታውቋል። ኮሚሽኑ “ተቋማዊ ነጻነቴን ጠብቄ ምርመራዬን እንዳልቀጥል አድርገውኛል” ያላቸውን አካላት ማንነት ከመግለጽ ተቆጥቧል።
ኢትዮሪቪው መንግስት የትህነግ አንጃ ቡድን ከሻዕቢያ ጋር የጀመረውን ህገወጥ ግንኙነት አስመልክቶ ከትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ጋር በጥብቅ መነጋገሩና ማስተካከያ ካልተወሰደ እርምጃ ለመውስድ እንደሚገደድ ማስታውቁን ጠቅሰን መዘገባችን አይዘነጋም። ሻዕቢያ ትግራይንና አማራ ክልልን የጦርነት አውድማ ለማድረግ አቅዶ እየሰራ መሆኑንና ትናንት ያለ አንዳች ርህራሄ የጨፈጨፈውን ህዝብ ያለሃፍረት አጋር እላምድረግ የሄደበት ሃፍረተ ቢስ ርቀት እንደማይሳካ ሰለባዎችን ጠሰን ዘገበን ነበር።
ኢትዮሪቬውን ከታች ባሉት ማስፈንጠሪያዎች የከተሉ – የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ @ethioreview
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ ethioreview
ኤክስ ፡ twitter