በትግራይ የ1967 ዓም ዓይነቱ የዘመነ “ወይን” ዓይነት እንቅስቃሴ በስፋት እየታየ መሆኑ ተሰማ። ትህነግ ትህነግን ” ተቃዋሚ” ሲል ሊያጠፋው መነሳቱን አስታወቀ። ለትግራይ የሚላክ ነዳጅ ወደ ኤርትራ እየተጋዘ መሆኑን እማኞች ተመለከተ።
አቶ ኃይሉ ከበደ የሳልሳዊ ወያኔ ትግራይ የወጭ ግንኙነት ኃላፊ እንዳሉት በትግራይ አሁን ላይ ልክ እንደ 1967 ዓም የሚያልሙ ኃይሎች መኖራቸውን አመልክተዋል። ጉዳዩን “አሳዛኝ” ሲሉ ገልጸውታል።
የትህነግን ሁለት ቦታ መሰንጠቅ ተከትሎ የተያዘው አቋምና በተግባር እየታየ ያለው እንቅስቃሴ ሕዝቡ ካለው የሰላም ተስፋ፣ የጦርነት ስጋትና ግጭት መጠየፍ በሚቃረን ደረጃ እያመራ ነው።
“ሁለት ታጣቂ ኃይሎች ተፈጥረው የትግራይን ህዝብ ለማጥፋት ወደ እርስ በዕርስ ግጭት አያመሩ ነው” በማለት በርዕዮት ሚዲያ የተናገሩት አቶ ኃይሉ፣ ከዚህም በተጨማሪ የኤርትራ ኃይሎችና የፌደራል መንግስት ጦርነት ከጀመሩ ትግራይ የጦርነት አውድማ ልትሆን እንደምትችል ስጋቱ ማየሉን ገልጸዋል።
የእን ዶክተር ደብረጽዮን ትህነግ ከሻዕቢያ ጋር የጀመረው ወዳጅነት ያስቆታቸው የትግራይ ያጣቂዎች ኃይል በከፊል በተለያዩ ደረጃ ካለ አመራራቸው ጋር “ሐራ መሬት” በማምራት በደቡብ ትግራይ አቅጣጫ መስፈራቸውና አሁንም ወደ እዛው አቅታጫ በየቀኑ የሚሄዱ እንዳለ የተገለጸ ነው። አቶ ኃይሉ በአንድ ክልል፣ በአንድ ብሄር ስም እርስ በእርስ የሚጋደል ኃይል ከተነሳ አደጋው የከፋ ነው። ይህንኑ ሁኔታ ነው “በትግራይ የ1967 ዓይነት ስሜት እየታየ ነው። ያስለቅሳል” ሲሉ የገለጹት።
አቶ ኃይሉ ይህን ከማለታቸው በፊት፣ የእነ ዶክተር ደብረጽዮን ቡድን ለዓለም ዓቀፍ ማህበረሰብ ባሰራጩት የአቤቱታ ደብዳቤ ” የፌደራል መንግስት ተቃዋሚ በማደረጃት ሊያጠፋን ነው” ያሉት። “ተቃዋሚ ” ሲሉ የጠሩት ይህ ኃይል ከራሳቸው ውስጥ አኩርፎ የወጣ እንጂ አዲስ የተቋቋመ አይደለም። ይህን ኃይል መልሶ ማደረጃትና አቅጣጫ እንዳይበትን ማድረግ እንደሚያስፈልግ አቶ ጌታቸውና ወ/ሮ ኬሪያ መናገራቸው አይዘነጋም።
በየትኛውም አግባብ በሚታወቅ አመራር በግልጽ ይህ ኃይል በእነ ዶክተር ደብረጽዮን ላይ ጦርነት እንደሚከፍት ባይገልጽም አቶ ኃይሉ እንቅስቃሴውን ” የዘመነ ወይን” ዓይነት ትግል የመጀመር አዝማሚያ እንደሆነ አመልክተዋል።
“በትግራይ ያለው ሁኔታ ውጥንቅጡ የወጣ፣ ደርዝ ማስያዝ የማይቻል ችግር ነው” ያሉት አቶ ኃይሉ፣ በዚህ ላይ በክልሉ የሚታየው መርሃ አልባ ግንኙነት ችግሩን የሚያብስ ቁልፍ ጉዳይ ነው። ይህን ውጥንቅጥ “ትህነግ በከፍተኛ የአጥፍቶ መጥፋት ስካር ውስጥ እንዳለ የሚያሳይ ነው” ብለውታል።
ሁሉም ወገኖች ከስሜትና እልህ ተላቀው ወደ ጠርጴዛ ዙሪያ ማምራት አለባቸው ያሉት አቶ ኃይሉ ፓርቲያቸው ይህን ስጋት ለመቅረፍ በትግራይ ደረጃ ሁሉን ያካተተ ብሄራዊ የተባለ ጉባኤ እንዲያደርጉ ድርጅታቸው መጠየቁን አመልክተዋል።
አንድ ላይ በመሰባሰብ ያላቸውን ጥያቄና ልዩነት ለፌደራል መንግስት ማቅርብ ነባራዊ ሃቅ እንደሆነ አቶ ኃይሉ አመልክተዋል። ከስልታን ውጪ መኖር የማይችሉ፣ ልኑርም ቢሉ ምንም ዓይነት ሌላ ሙያ የሌላቸው፣ በወንጀል ላለመጠየቅ ጦርነትን ብቻ መፍትሄ አድርገው የሚሰሩት የትህነግ አመራሮች መላ ሊሉ እንደሚገባም ጠቁመዋል።
የሻዕቢያ ኃይሎች በስፋት በሚንቀሳቀሱባቸው አካባቢዎች በኩል በገሃድ ነዳጃ እነደሚጋጋዝ የገለጹት የዓይን ዕማኞች ናቸው። በተለይም በራማ አቅጣጫ መጠነኛ ግብይት መጀመሩን አመልክተዋል። ከተለያዩ አካባቢዎች ነዳጅ እያጋጋዙ በሚያቀርቡ አማካይነት ነዳጅ ወደ ኤርትራ እንደሚጋዝ “በዓይናችን አይተናል። እያየን ነው። የተለመደና በገሃድ የሚፈጸም ነው” ብለዋል።
በትግራይ የነዳጅ አቅርቦት ችግር እንዳለ፣ በመጠቀስ የእነ ዶክተር ደብርጽዮን ቡድን ሰሞኑን ለዓለም ዓቀፍ ህማህበረሰብ ባሰራጩት ደብዳቤ ላይ ማስታወቃቸው አይዘነጋም። የዓለም ማህበረሰብ እንዲያውቅላቸው ዘርዝረው በአቀረቡት ክስ ላይ የነዳጅ እጥረት ከፍተኛ እንደሆነ አጽንዎት ሰጥተዋል።
ኤርትራ እንደ አገር የተመሰረተችው በገንዘብ አጠባና ኮንትሮባንድ እንደሆነ የሚገልጹ እንደሚሉት ላለፉት አምስት ዓመታት በትግራይ በኩል ዘረፋውን ሳይጨምር በርካታ ንብረት ይጋዛል። ከወርቅ አዘዋዋሪዎች ጀምሮ ነዳጅን ወደ ኤርትራ የሚያዘዋውሩ የፈጠሩት ችግር ከፍተኛ መሆኑን ምስክሮቹ ተናግረዋል።
የሁሉም የስማቸው ግንድ ” ነጻ አውጪ” ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ትህነግን በከፋ ደረጃ እየተቹት ያሉ የክልሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ወደ ኤርትራ የሚደረገው ኮንትሮባንድ መረን የለቀቀ እንደሆነ እየጠቀሱ መሆናቸው አይዘነጋም። ክልሉ በጣጣቂ ኃይሎች የበላይ አመራርነት የሚተዳደርና የፖለቲካ ኃይሉ አቅም አልባ መሆኑም ለዚሁ መረን ለወጣ ኮንትሮባንድ ዓይነተኛ ምክንያት እንደሆነም የፓርቲዎቹ ኃላፊዎች በተለያዩ መድረኮች እያስታወቁ ነው።
የትግራይ ምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ቢሮ ሃላፊ አቶ ጠዓመ አረዶም “ነዳጁን በሙሉ ወስደው ጨርሰውታል። እሱም አልበቃ ብሏቸው ከራያ አላማጣና ከአፋር እያስመጡ ነው” ሲሉ ኃላፊነታቸውን መሰረት አድርገው ለትግራይ ሕዝብ እውነታውን ማሳወቃቸው አይዘነጋም። እሳቸው የነዳጅ እጥረት የተከሰተበትን ምክንያት ሲያስታውቁ እሳቸውን በመጠቅሰ አስቀድመው “የትግራይ ሕዝብ በነዳጅ እጥረት እንዲሰቃይ ተፈረደበት” በማለት ዜና ያሰራጩና የፌደራሉን መንግስት የወነጀሉ ይቅርታ አልተየቁም። ኃላፊውን ጠቅሰን የዘገብነውን ዘጋባ እዚህ በመጫን ላይ ያንብቡ።
አቶ ጠዓመ አረዶም ” ከጂቡቲ የሚመጣውን ነዳጅ በሙሉ በቀጥታ አዲ ፀፀር (ሸራሮ አካባቢ ) ፣ አዲክልተ፣ ገዛ ተጋሩ ፣ ዛና ፣ ህርሚ ፣ ሰመማ ፣ አዲደቂ በቅሊ ወዘተ በሚባሉ አካባቢዎች ውስጥ አከማችተውታል” በማለት ለጦርነት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋ ነበር። በዚያ የተከማቸው ነዳጅ ወደ ኤርትራ እንደሚጋጋዝ ደግሞ በቅርብ የሚከታተሉ ማናገራቸው የሚታወስ ነው።