ትህነግ ከፖለቲካ ፓርቲነት መሠረዙን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። ምርጫ ቦርድ እንዳለው ትህነግ የተሰጠውን የሶስት ወር ጊዜ በመጠቀም ማድረግ የሚገባውን ባለማድረጉ ነው ፓርቲው ላይመለስ ተሰርዟል።
ራሱን ህወሃት ወይም የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር (ትህነግ) ከግማሽ ምዕተ ዓመት በሁዋላ ከፖለቲካ ፓርቲነት መሠረዙ ይፋ የሆነው ዛሬ ነው። በዚሁ መሰረት ከግንቦት 5 ቀን ጀምሮ 2017 ዓም ፓርቲው የተሰረዘ መሆኑን ያመለከተው ቦርዱ ለውሳኔው ተግባራዊነት መነXአ ያላቸውን ጭብጦች በመግለጫው ዘርዝሯል። ተግባራዊ የሚደረገውን አዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 99 ጥቅሶ ተግብራዊ እንዲሆን ለፍትህ ሚኒስትርና ለሚመለታቸው አካላት አስታውቋል።
ትህነግ ከቀናት በፊት “ምርጫ ቦርድ ሰረዘን፣ አልሰረዘን የፕሪቶርያው ስምምነት ይቀጥላል፤ አደገኛ የሚሆነው ስለተሰረዛችሁ የፕሪቶርያውን ስምምነትን አናውቀው መባል ሲጀምር ነው” ነው በሚል ማሳሰቢያ መስጠቱ አይዘነጋም። ትህነግ ይህን ከማለቱ በፊት ምርጫ ቦርድ የሚሰርዘን ከሆነ አደገኛ ትርምስ ይፈጠራል ማለቱም አይዘነጋም።
ቦርዱ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ ህወሓት ከየካቲት 5 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ እግድ በመጣል ህወሓት የሚጠበቅበትን የዕርምት እርምጃ እንዲወስድ የሰጠው ጊዜ እስኪጠናቀቅ ያታዘዘውን እንዲያደርግ ሲጠብቅ መቆየቱን ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የታገደው ትህነግ ከዞህ ውሳኔ በሁዋላ ህጋዊ ሆኖ መንቀሳቀስም ሆነ ማናቸውን ተግባራት ማከናወን ስለማይችል በህግ አግባብ የሚወሰድበት ቀጣይ ተግባራት አዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 39 እንደሚከናወን የሚጠበቅ ሲሆን፣ አስቀድሞ በድንበር ላይ ሰራዊትና ትጥቅ ወደ ኤርትራ ማጋጋዝ መጀመሩ ተሰምቷል።
ኤርትራ መውጪያ በር እንደምጸጣቸው ቀደም ተብሎ የተዘገበ ሲሆን ይህንኑ ተከትሎ ከኤርትራ ምድር ላይ የሚነሱ ኃይሎች አንዳች ትንኮሳ ቢፈጽሙ ኢትዮጵያ መራር የተባለውን አጻፋዊ እርምጃ እንደምትወስድ አስቀድማ ማስጠንቀቋ አይዘነጋም። ሰሞኑን ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ” ያንቀለቀላቸው አሉ” ሲሉ አስጠንቀቀዋል።
ይህንኑ አስመልክቶ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያወጣው መግለጫ ሙሉ ቃል ቀጥሎ ቀርቧል



