አሰብ፣ቂጣና፣ እንዳሽችሁ ኤርትራ ኑ የሚሉት አዲስ መረጃዎች የተሰሙት “ ወንድማማች ህዝብ አትበሉን፣ ያለፈውን በደል ስለማወራረድ ጭራሽ አታንሱ” በማለት የትግራይን ሕዝብ ዝቅ የሚያደርግ ክብረ ነክ መመሪያ መተላለፉ በገሃድ ከኤርትራ የፕሮፓጋንዳ ሰዎች በተላለፈ ማግስት ነው። ይህ መመሪያ ያበሳጫቸው የትግራይ ተውላጅ የሆኑ ቁጣቸው ሳይበርድ “ቂጣ እንካፈላለን” የሚለው አዋጅ መድመጡ ልዩነቱን አስፍቶታል።
“ለትግራይ ህዝብ መልካም ዜና” ይላል ከአስመራ የተላከ መሆኑን የሚናገረው የፕሮፓጋንዳ ሰው” ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ የተላከ መልዕክት ይዤላችሁ መጥቻለሁ” ሲል ድምጹን ከፍ አድርጎ በማሰማት ” አዋጅ አዋጅ መልካም ዜና ለትግራይ ሕዝብ” እያለ ኢሳያስ በሰብአዊነት ለትግራይ ያቀረቡትን ስጦታ ይዘርዝራል።
አዲስ አበባ ተወልደው፣ አድገውና አርጅተው ኢትዮጵያን ወርaሪ አድርገው “ነጻነት” ያሉትን ጨምሮ በየቀኑ የሚጎርፉትን ከስምንት መቶ ሺህ በላይ የኤርትራ ተወላጆችን የኢሳያስ ደግነት አስገርሟል። የትግራይ ሕዝብ ላይም ለመሳለቅ የሞከሩም ታይተዋል።
ኢሳያስን “ዲክታተርና አሸባሪ” የሚሏቸው ነገሩ ገብቷቸዋል። ከሁሉም በላይ ወደ መጨረሻቸው እያመሩ እንደሆነ የገባቸው ኢሳያስ፣ በኮንትሮባንድና በህገወጥ መንገድ ኢትዮጵያ ላይ የሚያካሂዱት ሌብነት ሳያንስ አማራ ክልልን ቀድሞ በማተራመስና ትህነግን ዳግም ባሪያ በማድረግ መጨረሻቸውን ለማሳመር እየተሯሯጡ እንደሆነ የሚገልጹ ” የአማራም ሆነ የትህነግ ሰዎች ሊወድቅ የደረሰ ዛፍ ባይደገፉ ” ሲሉ መመከር ከጀመሩ ቆይተዋል። በተለይም ትግራይንና አማራ ክልልን የጦርነት አውድማ በማድረግ ኢትዮጵያን ለማድከም የያዙትን ዕቅድ መመርመር እንደሚገባ የሚመክሩ ጥቂት አይደሉም።
ለትግራይ ሕዝብ ” ከአሁን በሁዋላ አትራቡም። የምንበላውን ቂጣም ቢሆን እናካፍላችኋለን” ሲሉ ኢሳያስ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ተከትሎ፣ “ አንተ ራስህ ምን የምትበላው አለህ? የኤርትራን ህዝብ ጨለማ ውስጥ ያሰርክ አምባገነን” በሚል በአውሮፓ የሚኖሩ ተቃዋሚዎቻቸው ተችተዋል። ተቃውመዋል። ያሰሩዋቸውን የኤርትራ ህዝብ እንዲለቁ ጠይቀዋል።
ከመንግስትም ሆነ ጉዳዩን ከያዙት ወገኖች በይፋ ባይገለጽም ኢሳያስ በሶማሊያና በየመን ካሉ እንቅስቃሴዎችና የመሳሪያ ዝውውር ጋር በተያያዘ ወደ ለመዱት ማዕቀብ ሊመለሱ እንደሚችሉ እየተሰማ ነው። በተለይም በሶማሊያ አሁን ላይ የአልሸባብ ሃይል ከመጠናከሩ ጋር በተያያዘ ኢሳያስ ቀደም ሲል ሲከሰሱበት የነበረውን ፋይ አድሰው እጃቸውን እንደከተቱ መረጃዎች መኖራቸው እየተሰማ ነው። ይህን ጉዳቸውን ይዘው ነው አሁን ደረስ በአሜሪካ የአሸባሪዎች ሊስት ውስጥ ተመዝግቦ ከሚገኘው ትህነግ፣ ኦነግና ከአማራ እንቅስቃሴ ጋር ህብረት ለመፍጠር እየሰሩ ያሉት።
ሻዕቢያን ባበሳጨው የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት እልባት ባገኘው ጦርነት አንድ ሚሊዮን የትግራይ ተወላጆች ህይወት አልፏል። የተለያዩ የትግራይ ወገኖች ይህንኑ ቁጥር ጠቅሰው ጦርነቱ ያስከተለውን ጉዳት ይፋ ሲያደርጉ በዋናነት የሚያነሱትና ተጠያቂ የሚያደርጉት የኢሳያስ አፉወርቂን ሰራዊት ነው። የመቀለ ዩኒቨርስቲ ባደረገው ጥናት “ህይወታቸው አለፈ” ከተባሉት አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ የትግራይ ተወላጆች መካከል 76 ከመቶ ወይም ከ760 ሺህ የሚልቁት የተጨፈጨፉት በኢሳያስ ትዕዛዝ በሻቢያ ሰራዊት ነው። “እንግዲህ ይህን ያደረገ ነፍሰ ገዳይ ነው ትግራይን በቂጣ ሊደልል የሚዳዳው” የሚሉ ኢሳያስን ሳይሆን እነ ደብረጽዮንን ነው “ከሃጂ ልክስክስ፣ ገረዶች” እያሉ ስድብና ተቃውሞ የሚያዘንቡባቸው።
በትግራይና በትግራይ ሕዝብ ላይ ከተፈጸመው ዝርፊያ፣ 120 ሺህ የሚጠጋ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል፣ ውድመትና አካል ላይ የደረሰ ጉዳት ከጭፍጨፋው ጋር አንድ ላይ ተዳምሮ ትግራይን መቶ ዓመት ወደ ሁዋላ የመለሳት ጦርነት የተቋጨው በፕሪቶሪያው ስምምነት እንደሆነ ይታወሳል።
የተኩስ አቁሙ ይፋ መሆኑን ተከትሎ ሻዕቢያ ” እንዴት የሰላም ስምምነት ታደርጋላችሁ?” በሚል ኩርፊያ ከፌደራል መንግስት ጋር ተቆራረጠ። በግልጽ ኢሳያስ ይህን ተቃወሙ። ቀደም ሲል የአገር መከላከያ ሰራዊት ትግራይን ለቆ ሲወጣ ቅሬታ እንደነበራቸው ያስታወቁት ኢሳያሰ፣ በድጋሚ የፕሪቶሪያው ስምምነት ያሰቡትን እንዳይፈጽሙ በማድረጉ ቁጣቸውን በሚደጉሟቸው ሚዲያዎች በኩል ተናገሩ።
“ጦርነቱ ለምን ቆመ” በሚል የተበሳጨው ሻዕቢያ ሳይውል ሳያድር ከአፈንጋጩ ትህነግ ጋር ግንኙነት መጀመሩ ተሰማ። በርካታ የትግራይ ተወላጆች፣ በመቀለ ያሉ የተቃዋሚ ድርጅቶችና በራሱ በትህነግ ውስጥ ያሉ ከፊል የፖለቲካ አመራሮችና የጦር መሪዎች ተቃውሞ አሰሙ። ልዩነቱም ሰፋ። “በሬ ካራጁ” የተተረተበት የእነ ደብረጽዮን ቡድን ግን መስሚያውን ዘግቶ ገፋበት።
ይኸው የውስጥ ለውስጥ ግንኙነት እያደር ጠንክሮ ዶከተር ደብረጽዮን የሚመሩት የትህነግ አንድ ስንጣቂ በታጣቂ ኃይሎች በመታገዝ የክልሉን ጊዜያዊ አስተዳደር አፈረሰ። ከትግራይ የሚወጡ መረጃዎች እንደሚሉት ከሆነ ይህ ከሆነ በሁዋላ የሻዕቢያ ሰላዮችና የጦር አበጋዞች እንዳሻቸው ትግራይ ውስጥ እየተንቀሳቀሱ ነው። ቀድሞም ጊዜያዊ አስተዳደሩ እንዲፈርስ መመሪያ የሰጡት ኢሳያስ ነበሩና ሻዕቢያ በግፋና በንጹሃን ደም በተጨማለቀበት ትግራይ መናኘት ጀመረ።
ይህንኑ ተከትሎ የአይን እማኝ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች እነ ደብረጽዮንን በመቃወም በርካታ ታጣቂዎች እየከዱ ከትግራይ መውጣታቸውን ማስታወቅ ጀመሩ። እነዚሁ ክፍሎች በማህበራዊ ገጾችና በላቸው መድረክ ሁሉ እነ ደንረጽዮን ላይ ተቃውሞ እንዳየለባቸው ዛሬ ድረስ እየገለጹ ነው። ከትህነግ ሰራዊት ራሳቸውን የለዩ ለውጊያ መዘጋጀታቸውንም ሲገልጹ የሚያሳይ ቪዲዮም እየተሰራጨ ነው።
በተደጋጋሚ የትግራይ ታጣቂ አመራሮችና የፖለቲካ መሪዎች በኦፊሳል ወደ አስመራ ተመላልሰዋል። ወደ ሱዳንም የዘለቁ አሉ። ከሱዳን መንግስት የዲፕሎማት ፓስፖርት ያገኙ እንዳሉም ለትግራይ ፖለቲካ ቅርብ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች ይፋ እያስታወቁ ነው። ስም ጠቅሰው ሱዳንን ረግመዋል።
እስከ ሃያ ሺህ የሚጠጉ የትግራይ ተወላጆች ለሱዳን እየተዋጉ መሆኑን፣ በዚህም የትግራይ ባለስልታኖች ክፚ እያገኙ መሆኑ ሰሞኑን በስፋት ከመረጃ ጋር እየወጣ ባለበት ሰዓት ነው አመራሮቹ በኤርትራ በኩል ወደ ሱዳን ያቀኑት።
ከምንም በላይ ” የትግራይና የኤርትራ ህዝብ ወንድማማች ነው አትበሉ፤ ያለፈውን ኪሳራ አታንሱ” በሚል ሁለት አስገዳጅ ገደብ የተጀመረው የፕሮፓጋንዲስቶች ቅርርብ የተጀመረውን ግንኙነት እንዲያግዝ አቅጣጫ ቢቀመጥም የተቀመጡት ሁለት ክልከላዎች ብስጭት አስነስተዋል። ከኤርትራ ወገን ያሉ አክቲቪስቶች “ወንድማማች አትበሉን” በሚልና ሻዕቢያ የትግራይ ሕዝብ ላይ የፈጸመውን በደል ማንሳት እንደማይቻል እያጣቀሱ በገሃድ መናገራቸው ግንኙነቱ መርሃ አልባ፣ የትህነግን ግርድና የሚያሳይ፣ ትህነግ ሲፈጠር ጀምሮ የሻዕቢያ ገረድ መሆኑን የሚያሳይ እንደሆነ በመጠቀስ ትችት ተነሳበት። ትችቱ ሰፊ መሰረትና ወደ ሁዋላ ሄዶ በትግል ዘመን ሻዕቢያ ትግራይና የትግራይ ታጋዮች ላይ የፈጸመውን አሳዛኝ ግፍ እያጣቀሰ ቀጥሏል።
በዚህ የጋለ ተቃውሞ መካከል፣ ትህነግን ” የተገረደደ” በሚል የሚፈርጁት ተሰሚነት ያላቸው የትግራይ ተወላጆች ጩኸት በርክቶ በሚሰማበት በዚህ ወቅት፣ አወል ሰዒድ የተባለው የሻዕቢያ የፕሮፓጋንዲስት “ከኢሳያስ አፈወርቂ የተላከ መልዕክት ይዤላችሁ መጥቻለሁ” ሲል መሪውን እያደነቀ አደባባይ ወጣ። “መሪዬ ኢሳያስ አፈወርቂ” አለ አወል እንደ ብራቅ እየጮኸ
- ሁሉም የትግራይ አክቲቪስቶች በፈለጉበት ሰዓትና ጊዜ ወደ ኤርትራ መግባትና መውጣት እንዲችሉ መፈቀዱን
- ከአሁን በሁዋላ በርሃብ የሚሞት የትግራይ ሰው መኖር የለበትም።ስለሆነም እኛ ከምንበላው ቂጣ ልናካፍላችሁ ዝግጁ ነን መባሉን
- የአሰብ ወደብ ለትግራይ በረከት መሆኑን
በተደጋጋሚ ከኢሳያስ አፉወርቂ ለትግራይ ሕዝብ የተላከ ሰማያዊ ይዘት ያለው መልካም ዜና መሆኑን አበሰረ። ኢሳያስ ክንፍ ያላቸው መለዐክ ተደርገው በለጋስነት ለትግራይ ሕዝብ የጭንቅ ጊዜ መልዕከተኛ ሆነው ቀረቡ። በጩኸትና በቃለ አጋኖ በግፍ በጨፈጨፉዋቸውና ባስጨፈጨፏቸው የትግራይ ልጆች መቃብር ላይ ዳግም እንዲነግሱ ጥሪ ቀረበ።
ትህነግ በሚባለው ትግራይ ላይ የበቀለ አረም የተነሳ በክህደት የተጀመረው ጦርነት ሲሳይ የሆነለት ሻዕቢያ ሰርግና ምላሹን ተጫወተ። አራዊቶቹን ልኮ ደም ተጋተ። ይህንኑ የተጋተውን የንጹሃን ደም በቂጣ እንዲወራረርድ የትግራይ አክቲቪስቶች ወደ አስመራ ጋበዘ።
አጋጣሚን አድብቶ ሲጠብቅ የነበረው ሻዕቢያ በቻለው ሁሉ ያፈረሳት፣ የዘረፋት፣ ያወደማት፣ የጨፈጨፋት፣ የደፈራት፣ ከማሽነሪ እስከ ተራ ጭልፋ ያጋዘባት ትግራይ በቂጣ መስዋዕት በደሏን እንድትረሳ የትግራይ ልጆች እንዲቀሰቅሱ ስልጠና ወሰዱ። ከኢሳያስ ቡራኬ ወሰዱ። እነዚህን “ክaርቶን ራስ” በሚል የሚጠሯቸው የትግራይ ተወላጆች ግን አቋማቸው ያው የድሮው ሆነ። ሻዕቢያ የትግራይ ሕዝብ ታሪካዊ ጠላት መሆኑን ወንከጀሉን እየዘረዘሩ እየከሰሱ ነው። የትግራይ ሕዝብም ዓይኑ ተገልጦ “ ወገዱ” ማለት ጀመሯል።
ለኢሳያስ የድፍረት ድፍረትና የንቀት ሁሉ ንቀት ደብረጽዮን ፊት መሪ ሆነው እየተገረዱ መሆናቸውን የሚገልጹ፣ ትህነግን መንቀል ዋንኛ መፍትሄ መሆኑን እየጠቆሙ ነው።
ትህነግ ህገመንግስቱን በመጣስ ከሻዕቢያ ጋር እያደርገ ያለውን ግንኙነት በውስጥ መስመር ከመምከር በዘለለ በአደባባይ ያለው ነገር የለም። የፖለቲካ ስሌቱን በሚያምናቸው ፕሮፓጋንዲስቶቹ ማስታወቅን የተካነበት ሻዕቢያም ቢሆን በኦፊሳል አቋሙን አለማንጸባረቁ ምን አልባትም ለመንግስት ምላሽ አደጋች ሊሆን እንደሚችል የሚገምቱ አሉ።
ከሁሉም የሚገርመው ሻዕቢያ አማራ ላይ እየቆመረ ያለው ቁማር ነው። “አማራ ነን፣ ለአማራ መብት ለመታገል ጫካ ገብተናል” የሚሉ የተወሰኑ ቡድኖች የሚንቦጫረቁበት የሻዕቢያ ፍቅር፣ “መሬታችሁን ለማስመለስ ሆነ ለልማት ከእኛ ጋር የምትሰሩ ከሆነ የአሰብ ወደብን እንሰጣችኋለን ብሎናል” ሲል ኃይለ ደደቢት በድምጽ የተናገረው በቂ ማስረጃ እንደሆነ የሚጠቁሙ ” ከትህነግ በላይ ሻዕቢያ ወልቃይት ጠገዴ ሲቲት ሁመራን ይመኛል” በሚል ቀደም ሲል የከዳ የሻዕቢያ ሰላይ ይፋ ያደረገውን ሚስጢር ያረጋገጠ ሆኗል።
በምንም ተዓምር ትግራይ መውጫ ሊኖራት እንደማይገባ በይፋ ሲያስታውቅ የኖረው ሻዕቢያ በጥብቅ የተያዘውን የእርቅ ንግግር ቢጨርስና ዳግም ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ቢስማማ ትህነግ ምን ይገጥመው ይሆን?
ኢትዮሪቬውን ከታች ባሉት ማስፈንጠሪያዎች የከተሉ – የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ @ethioreview
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ ethioreview
ኤክስ ፡ twitter