“አሁን ለተገኘው ነጻነት መላው የአማራ ሕዝብ ዋጋ ከፍሎበታል”
በአማራ ክልል ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የወልቃይት ጠገዴ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አባላት ስልጠና በትናትናው እለት ተጠናቋል።
ለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ለተገኘው ነጻነት መላው የአማራ ሕዝብ ወጋ ከፍሎበታል ያሉት የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ እና ሰላምና ጸጽታ መምሪያ ኃላፊ እንዲሁም የወልቃይት ጠገዴ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ከብዙ ድካምና በርካታ መስዋዕትነት በሗላ በተባባረ ጽናታችን ነጻነታችን አግኝተናል ብለዋል።
ለዘመናት በገዛ እርስታችን ስንሳደድ የባርነት ቀንበርን ተሸክምን ቆይተናል ብለው ያገኘነውን ነጻነት በህግ አግባብ ለማረጋገጥ በመተባበርና በመቀናጀት ልንሰራ ይገባል ብለዋል።
ነጻነታችን ለማረጋገጥ የማንነት ኮሚቴው በርካታ ችግሮችን በመቋቋም በጽናት ተጋድሎ አድርጓል ብለው ይህም ፍሬ አፍርቶ በጋራ በነጻነት እንድንገናኝ ሁነናል ብለዋል።
አስመላሽ ኮሚቴው አሁንም የነበረውን ተጋድሎ በማስቀጠል አማራዊ ማንነታችን በህግ አግባብ ለማጽናት በመቀናጀት ልንሰራ ይገባል ሲሉ አንሰተዋል።
ለቀጣዩ ትውልድ እዳን አናወርስም ያሉት የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ አሸተ ደምለው ትጋላችን የእውነትና የፍትህ ትግል በመሆኑ የሰማዕታትን አደራ በማስቀጠል ዛሬም እንደትናንቱ በመተባር ልንስራ ይገባል ብለዋል።
ማንነት ሊቀየር የማይችል በተፈጥሮ የሚሰጥ ነው ብለው የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ባለፉት አመታት እኔ አማራነኝ ብሎ ሲታገልና ሲሳደድ ቆይቷል ሲሉ ገልፀዋል።
ይህ ትውልድ ለዘመናት ዋጋ የተከፈለበት አማራዊ ማንነት በመተባበርና በመቀናጀት በህግ አግባብ ሊያጸና ይገባል ሲሉ አንስተዋል።
አማራዊ ማንነታችን ለማስመለስ ባለፉት ዓመታት የብዙ ወንድሞቻችን ሕይወት አተናል ያሉት የአስመላሽ ኮሚቴው አባላቶች የሰማዕታትን አደራ በማስቀጠል ማንነታችን በህግ አግባብ እንዲረጋገጥ ከምንጊዜውም በላይ እንሰራለን ብለዋል።
ትግላችን ራስን የመሆን ትግል ነው ሲሉ ተናግረው ራስን የመሆን ትግል በራስ ባህል የመጠቀም፣በፈለጉት ቋንቋ የመጠቀም እና በፈለጉት ስርዓት በነጻነት የመኖር መብት ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ማንነት የሚሸጥና የሚቀየር አደለም ብለው ጨካኞች እኛን ካልመሰላችሁ በማለት በሀይል ሌላ ማንነት ለመስጠት ሲታገሉ ቢቆዩም የእውነት ጊዜዋ ደርሶ ነጻነታችን አግኝተን በአማራዊ ማንነታችኝ በአደባባይ እየገለጽን ነው ሲሉ አንስተዋል።
የራሳችን አሳልፈን አንሰጥም የማንንም አንፈልግም እኛ አማራዎች ነን ያሉ ሲሆን መንግስት ማንነታችን በማረጋገጥ እንደዜጋ በጀት የማግኘት መብታችን እንዲያሰፈንልን ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።