የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ” የውጭ ምንዛሪ ገበያ ሥርዓትን በይበልጥ ለማሻሻል ከዛሬ ጀምሮ የተወሰኑ የለውጥ እርምጃዎችን ወስጃለሁ ” ሲል አሳውቋል። የቅድመ ክፍያ መጠን ከ5 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ወደ 50 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ከፍ ተደርጓል
የለውጥ እርምጃዎቹ የኢትዮጵያን የውጭ ምንዛሪ ገበያ ከዓለም አቀፍ አሠራር ጋር ከማጣጣም ባሻገር ለአስመጪዎችና ለውጭ ሀገር ተጓዦች የተሻለ ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ ናቸው ብሏል።
ዛሬ የተደረጉ የማሻሻያ እርምጃዎች ምንድናቸው ?
1. ለአስመጪዎች የቅድመ ክፍያ (አድቫንስ ፐይመንት) መጠንን ከ5 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ወደ 50 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ከፍ ተደርጓል።
ይህ የማሻሻያ እርምጃ አስመጪዎች ለውጭ ሀገራት አቅራቢዎቻቸው የሚያደርጉትን የውጭ ምንዛሪ ቅድመ ክፍያ (አድቫንስ ፐይመንት) መጠን የሚገድበውን የቆየ አሠራር ለመለወጥ እንደሚረዳ ተገልጿል።
በመሆኑም፤ ብሔራዊ ባንክ በአስመጪዎች ላይ የተጣለውን የቅድመ ክፍያ ገደብ ከፍ ማድረጉን አሳውቋል።
“ ከአቻ ሀገራት ተሞክሮ በመነሣትና ለብዙ ዓመታት ለውጥ ሳይደረግበት የቆየውን አሠራር የመለወጥን አስፈላጊነት በመገንዘብ፣ ሸቀጦችን ከውጭ ለማስገባት ሊከፈል የሚችለውን የቅድመ ክፍያ መጠን ከ5 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ወደ 50 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ከፍ ተደርጓል ” ብሏል።
2. ለውጭ ሀገር ተጓዦች የሚፈቀደውን የውጭ ምንዛሪ ጥሬ ገንዘብ መጠን ከፍ ተደርጓል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ” ለውጭ ሀገር ተጓዦች ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ሲባል ወደ ውጭ ሀገር ለሚጓዙ ኢትዮጵያውያን በጥሬ ገንዘብ የሚፈቀደው የውጭ ምንዛሪ መጠን እንዲጨምር ተደርጓል ” ሲል አሳውቋል።
በአዲሱ ገደብ መሠረት ለግል ተጓዦች የሚፈቀደው የውጭ ምንዛሪ ወደ 10 ሺህ የአሜሪካ ዶላር፣ ለንግድ ሥራ መንገደኞች ደግሞ 15 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ሆኗል፡፡
ይህንንም የውጭ ምንዛሪ በጥሬ ገንዘብ ወይም በካርድ መውሰድ ይቻላል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ፣ የውጭ ምንዛሪ የባንክ ሂሳብ ያላቸው ግለሰቦች ከሂሳባቸው ላይ በካርድ መጠቀም የሚችሉት የውጭ ምንዛሪ መጠን ከ10 በመቶ ወደ 20 በመቶ ከፍ እንዲል ሆኗል፡፡
3. የባንኮችን የውጭ ምንዛሪ ክፍያዎችን ሥርዓት ለማስያዝ እርምጃ ተወስዷል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ” በኢትዮጵያ የሚሠራባቸውን ከውጭ ምንዛሪ ጋር የተያያዙ አስተዳደራዊ ክፍያዎችን ከዓለም አቀፍ ሁኔታዎች ጋር ለማጣጣም ሲባል ባንኮች ለውጭ ምንዛሪ አገልግሎት የሚያስከፍሏቸው ወጪዎች ተወዳዳሪነትን፤ ግልጸኝነትንና ምቹነትን ታሳቢ ያደረጉ እንዲሆኑ አበረታታለሁ “ ብሏል።
በዚሁ መሠረት፣ ከገቢ ንግድ፣ ከአገልግሎት ክፍያ ወይም ከጥሬ ገንዘብ ጋር በተያያዘ ባንኮች ለውጭ ምንዛሪ አገልግሎት የሚያስከፍሏቸው ማናቸውም አስተዳደራዊ ወጪዎችና ክፍያዎች ከግንቦት 18፣ 2017 ጀምሮ ከ4 በመቶ እንዳይበልጡ ተወስኗል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ፣ ከውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ጋር የተያያዙ አስተዳደራዊ ወጪዎች ለተጠቃሚዎች ግልጽና ቀላል መሆናቸውን ለማረጋገጥ ሲባል ባንኮች የሚያስከፍሏቸውን የተለያዩ ተጨማሪና ጥቃቅን የአገልግሎት ወጪዎች እንዲያስቀሩ ባንኩ መመሪያ አስተላልፏል፡፡
በመጨረሻም፣ ከውጭ ምንዛሪ ግብይት ጋር የተያያዙ የባንኮችን አስተዳደራዊ ክፍያዎች ግልጽነት ለማረጋገጥ ብሔራዊ ባንክ ከሰኔ ወር 2017 ጀምሮ በድረ ገጹ ላይ መረጃዎቹን በመደበኛነት ለሕዝቡ ይፋ እንደሚያደርግ አሳውቋል።
NBE
TIPS
ሱዳን ያለባትን የኤሌክትሪክ እዳ ለመፍፈል 1 ዓመት ከ6 ወር እንዲሰጣት ጥያቄ አቀረበች
በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የተሰጠ መግለጫ
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ታላቅ የምረቃ ሥነስርዓት ፤ የሁለተኛው ግድብና ዘመናዊ ከተማ መሰረት ይጣላል፤
በተለይ ወንዶች ላይ የሚከሰተውን የፕሮስቴት ካንሰርን በተመለከተ ሊያውቋቸው የሚገቡ ነገሮች
የአፍ ምሬት ከምን ይመጣል?
በደህንነት ስጋት ለጊዜው ማንኛውም የዳኝነት አገልግሎት መስጠት አቁመናል ” መቐለ ፍርድ ቤት
” የቅድመ ክፍያ መጠን ከ5 ሺህ ወደ 50 ሺህ ዶላር ከፍ ተደርጓል ” ብሔራዊ ባንክ
ይድረስ ለክቡር ገና…. ስለወርቃማ አክሲዮንና ዲጅታል ሉዓላዊነት የራሴን ምልከታ
የውጭ ዜጎችን የመሬት ባለይዞታ የሚያደርግ ረቂቅ አዋጅ ነገ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይቀርባል
ሞኝን እባብ ሁለቴ ነደፈው – አንዴ ሳያይ፣ ሁለተኛ ደግሞ ሲያሳይ <br>(ክቡር ገና)
አሌክሳንደር ኢሳክ ከኒውካስል ሊለቅ ይችላል ተባለ
ኢዜማ የህክምና ባለሙያዎችና መንግስትን መከረ፤ ሰላማዊና ሕጋዊ የመብት ጥያቄ ብቻ
የሻዕቢያና የወያኔ ሶስት የቢሆን ዕቅዶችና ወቅታዊ ግምገማዎች፤ ያኮረፈው አርሚ ስጋት ሆኗል
የውጭ ባንኮች 2018 አጋማሽ ላይ ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
“ሾልኮ ወጣ” የተባለው የዝርፊያ ሰነድና ለትግራይ ጊዜያዊ አስተዳር የቀረበ ምላሽ
የኢትዮጵያ ነርሶች ማህበር ታካሚዎች ለሞትና እንግልት እንዳይዳረጉ አስጠነቀቀ