በሀገራችን “ሞኝን እባብ ሁለቴ ነደፈው – አንዴ ሳያይ፣ ሁለተኛ ደግሞ ሲያሳይ” የሚባል ምሳሊያዊ አነጋገር አለ፡፡ እንግዲህ ሞኙ መጀመሪያ እባቡን ሳያየው ነደፈው ለሁለተኛ ጊዜ የነደፈው ግን እንዲህ አድርጎ ነደፈኝ ብሎ ለሌላ ሰው ለማሳየት በሚሞክርበት ጊዜ መነደፉን ልብ ይሏል፡፡
ይህ አባበል ከሰሞኑ የኢትዮ ቴሌኮም ሁኔታ ጋር ይመሳሰላል፡፡ መጀመሪያ ላይ ተቋሙ ህዝቡ የኢትዮ ቴሌኮም ባለድርሻ ይሆናል ሲል አበሰረን፡፡ በመቀጠልም የአክሲዮን ድረሻው ለህዘብ ሽያጭ ቀርቦ እቅዱ በጣም ሲያንስ ትረካው ተቀየረ፡፡
አሁን ደግሞ የድርጅቱን ትልቅ ድርሻ የውጭ ባለሀብቶች ይገዙታል የሚል ሽኩሹክታ እየተሰማ ነው፡፡ እናም ለውጭ ባለሀብት ተሸጦ ከታክስ ጠቀም ያለ ገንዘብ ይገኛል፤ ከዚህም ተጠቃሚ እንሆናለን የሚል አይነት ከንቱ አስተሳሰብ እየመጣ ይመስላል፡፡
የወርቅ እንቁላል እምትጥልን ዶሮ በመሸጥ በታክስ መልክ ጥቂት እንቁላሎችን አገኛለሁ ብሎ ማሰብ ስትራቴጂያዊ አመለካከት ሳይሆን ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ እጅ መስጠት ነው፡፡ የወተት ላምን ሽጦ ወተት ከገበያ እገዛለሁ ብሎ እንደመጃጃልም ይቆጠራል፡፡
ባለቤትነት ወሳኝ ነው
በኢትዮ ቴሌኮም ባለቤትነት ከዘለቅን ትርፉን ለራሳችን ጥቅም እናውላለን፣ የወደፊት አድገትና ልማታችን ላይ እንወስናለን እንዲሁም የሚያዋጣንን ስትራቴጂ ነድፈን እንጓዛለን፡፡ ይህ ሳሆን ቀርቶ ተቋሙን ለውጭ ባለሀብት ሽጠን ታክስ እንሰበሰባለን ካልን ግን ከባዶ ተስፋ በስተቀር ምንም ጠብ አይልልንም፡፡ ከታክስ ገቢ እንሰበስባለን ብለን ስናስብ ደግሞ የታክስ ስወራ፣ ገቢን አሳንሶ ማቅረብና ወደ ውጭ ሀገር ማሸሽ እነዳለም አንዘንጋ፡፡ ታላላቅ ድንበር ዘለል ካምፓኒዎች ደግሞ ታክስ በመሰወር፣ በመቀነስና በማሸሽ ረገድ የተካኑ ናቸው፡፡ በዚህ በኩል በሌሎች ታዳጊ ሀገሮች የደረሰው መታለል በኢትጵያም ላይ እንደሚደርስ እሙን ነው፡፡
ነገርን ከሥሩ ውሀን ከጥሩ!
ኢትዮ ቴሌኮም በቅርቡ የ10 በመቶ ድርሻን በአክሲዮን ለህዝብ ሽያጭ ማቅረቡና በእቅዱ መሰረት ያሰበውን ያህል ሽያጭ ያለማከናወኑ ድርሻውን ለውጭ ባለሀብት ለመሸጥ ምክንያት መሆን የለበትም፡፡ እንዲያውም አሁን ድርሻውን ለውጭ ባለሀብት መሸጥ የሚለውን የማያዋጣ ሀሰብ እርግፍ አድርጎ በመተው ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ ጉዳዩን የሚያሰላስልበት፣ የሚተነትንበትና መስተካከል ያለበትን የሚያስተካክልበት ወቅት ነው፡፡
ነገርን ከሥሩ ውሀን ከጥሩ እንደሚባለው ቴሌ ለህዝብ ያቀረበው የአክሲዮን ሽያጭ ለምን አልተሳካም ብሎ መጠየቅ ብልህነት ነው፡፡ ህዝቡ በአሁኑ ወቅት በብዙ ጉዳይ ላይ ጥርጣሬ አለው፡፡ በአክሲዮን ሽያጭ ሂደቱም ላይ ሙሉ መተማማን የለውም፡፡ በዚያ ላይ የካፒታል ገበያው ገና በሁለት እግሩ አልቆመም፣ እንዲሁም ይህ ወቅት ከፍተኛ የጥሬ ገንዘብ እጥረት የተከሰተበት ጊዜ ነው፡፡ ከሁሉም በላይ ግን ህዝቡ በወደፊት እጣ ፈንታው ላይ ጥርጣሬ አለው፡፡ እናም ህዝቡ ተሳስቷል ማለት እንችላለን?
በዚህ ተጨባጭ ሁኔታ ውስጥ ሆነን ያለንን ብሄራዊ አንጡራ ሀብት ለውጭ ባለሀብት አሳልፈን መስጠት ዘመናዊ መሆን ወይም ከጊዜው ጋር መራመድ ሊሆን አይችልም፡፡ እንዲያውም ይህን ካደረግን ከላይ የተቀስነውን ምሳሊያዊ አነጋገር ከመድገምም በላይ ለትውልድ የሚተርፍ ኪሳራ ነው፡፡ እዳውም ይህን ድርጊት ያስፈጸሙ የሀገሪቱ አመራሮች ካለፉ በኋል ኢትዮጵያ በቀጣይነት ስትከፍለው የመትኖረው ነው የሚሆነው፡፡
ለህዝብ የቀረበው የመጀመሪያው የአክሲዮን ሽያጭ ለምን አልተሳካም? አለመሳካቱስ ለምን አያስደንቅም? አትራፊው፣ እየተስፋፋ ያለው፣ 300 ቢሊዮን ብር የሚያወጣ ሀብት ያለው ኢትዮ ቴሌኮም 30 ቢሊዮን ብር በአክሲዮን ሽያጭ ለማሰባሰብ አቅዶ ያገኘው 3.2 ቢሊዮን ብር ብቻ ነው፡፡ ለምን?
ለምን ማለት ጥሩ፡፡ ምክንያቱም አንድ ግለሰብ አንድን ትልቅ ቤት ወይም ህንጻ ገዢዎች በከሰሩበት፣ እርግጠኛ ባልሆኑበትና ሂደቱ ህጋዊነቱን ባለጠበቀበት ሁኔታ መሸጥ ስለማይችል ነዋ!
በዚያ ላይ
የካፒታል ገበያ ስር ባልሰደደበት
የጥሬ ገንዘብ እትረት ባለበት
የአክሲዮን ድርሻን በተመለከተ አስተማማኝ ህጋዊ መዋቅር በሌለበት
አክሲዮን የገዙ ሰዎች አክሲናቸውን ሽጠው ገንዘባቸውን ለማግኘት ግልጽ አሰራር በሌለበት
ክልከላና እገዳ ብቻ በሰፈነበት
የጥርጣሬ ጥቁር ደመና ባጠላበት ሁኔታ ህዝቡ እንዴት አክሲዮን ይገዛል?
በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንደሚባለው ህዝቡ በዋጋ ንረት፣ በግጭት፣ በውጭ ምንዛሪ ተመን ቅነሳ እንዲሁም ባልተረጋጋ የኢኮኖሚ ሁኔታ አሳሩን እየበላ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ዜጎች መቆጠብ አይችሉም፡፡ የሚችሉትም እምት የላቸውም፡፡
የኢትዮ ቴሌኮም የአክሲዮን ሽያጭ በተመለከተ አንድ ግልጽ መሆን ያለበት ነገር አለ፡፡ የአክሲዮን ሽያጩ ከዕቅዱ በጣም ዝቅ ማለቱ ኢትጵያውያን በኢትዮ ቴሌኮም ላይ እምነት የላቸውም ማለት አይደለም፡፡ ይልቁንም የአክሲዮን ድርሻ ባለቤት መሆን ድርጅቱን መቆጣጠር ማለት አይደለም፣ ተገቢ የትርፍ ክፍፍል አናገኝም፣ አክሲዮናችንን ሸጠን ለመውጣት ብንፈልግ ግልጽ ስትራቴጂ የለም ብለው ስሚያምኑ ነው፡፡
እና አሁንስ ምን እያደረግን ነው? ተቋሙም ሆነ የበላይ አመራሮች እነዚህን መሰረታዊ ችግሮች ግልጸኝነት በማጎልብት፣ ሊያሰራ የሚችል ደንብና መመሪያ ባማስፍንና የጥሬ ገንዘብ ፍሰቱን ቀልጣፋ በማድረግ ከመፍታት ይልቅ የውጭ ባለሀበቶች ድርጅቱን እነዲታደጉት ባሻገር እየቃኙ እንደሆነ እየነገሩን ነው፡፡ ይህ ተቃርኖ የአንድን ቤተሰብ የከበረ ቅርስ በርካሽ ከመሸጥ ጋር ይመሳሰላል፡፡
አለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም የመንግስት የልማት ድርጅቶች ወደ ግል እንዲዛወሩ ጽኑ ፍላጎት አለው፡፡ የመንግስት ድርጅቶች ውጤታማ እነዲሆኑና እንዲስፋፉ ለግል ባለሀብት መሸጣቸው አስፈላጊ ነው ሲል ተቋሙ ይሰብካል፡፡ እዚህ ላይ የሚሸጡት ለማን ጥቅም ሲባል ነው ብልን መጠየቅ አለብን፡፡
የኢትዮ ቴሌኮምን ወደ ግል ንብረትነት ማዘዋወር የኢትዮጵያን ዜጎች አቅም እንዲኖራቸው ማስቻል ሳይሆን ህዝቡንና መንግስትን አቅም ማሳጣት ነው፡፡ እንደዚህ አይነት የሀገር ሀብት አንዴ በውጭ ባለሀብቶች እጅ ከገባ መንግስት በተቋሙ ላይ ያለውን ቁጥጥር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ያሳጣዋል፡፡ በዚህም ምክንት መንግስት ዋጋን የመወሰን፣ የቴሌ መሰረተ ልማቶችን ላልደረሳቸው ዜጎች የማዳረስ፣ ቴክኖሎጂን የማስፋፋት፣ አልፎ ተርፎም ብሄራዊ ደህንነትን የመከላከል አቅሙን ያጣል፡፡
ይህ ሁሉ ዘርፈ ብዙ ኪሳራ የሚመጣው ድርጅቱ ተሸጦ የታክስ ገቢ ይገኛል ተብሎና የተሸለ ውጤት ይመዘገባል በሚል አጉል ተስፋ ነው፡፡ ይህ ሁኔታ አንድ ሰው የመኪናውን ሞተር ከሸጠ በኋላ ከነዳጅ ወጪ ድኛለሁ ብሎ እራሱን እነደማሞኘት የሚቆጠር ነው፡፡
ጥገኝነትና ተጋላጭነት – ከፊታችን የተደቀነ አደጋ
ኢትዮ ቴሌኮም ከእጃችን ከወጣ ለፋይናስ፣ ለሀገር ደህንንትና ለኮሙኒኬሽን ወሳኝ የሆነው የኢትዮጵያ የዲጂታል መሰረተ ልማት በውጭ ባለሀብቶች እጅ ይወድቃል፡፡ የውጭ ባሀብቶች ትርፋቸውን ለማጋበስ ይተጋሉ፡፡ ለኛ ብሄራዊ ጥቅም ደንታ የላቸውም፡፡ ይህ ሁኔታ እንደ አርጀንቲናና ዛምቢያ በመሳሰሉ ሀገሮች ታይቷል፡፡ በገዛ ሀገር የውጭ ባለሀብቶች ገባርና ሎሌ መሆን ማለት ይህ ነው፡፡
ዛሬ የኢትዮ ቴሌኮም ገቢ የመንግስትን በጀት ይደግፋል፡፡ ነገ በውጭ ባለሀብቶች እጅ ሲገባ ግን ኒዮርክ፣ ለንደንና ዱባይ በሚገኙ የአክሲዮን ባለድረሻ ቱጃሮች ኪስ ነው የሚገባው፡፡
በእርግጥ ጥቂት ታክስ ይከፍላሉ
ምናልባት!
አልፎ አልፎ!
ለዛውም ደስ ካላቸው!
በዚህ መሀል አይበለውን ኢትጵያ ውስጥ የሆነ ቀውስ ቢፈጠር እነዚህ የውጭ ባለሀብቶች ነቅለው ይወጡና ኢትዮጵያ ዋንኛ የመገኛኛ ድም ስሯን ታጣለች ማለት ነው፡፡ ወይም ደግሞ የቴሌ ኮም አገልግሎት ለማግኘት ክራይ ለመክፈል ትገደዳለች፡፡
የሚያዋጣው መንገድ – ሽያጭ ሳይሆን ማሻሻያ
ኢትዮ ቴሌኮምን በሽያጭ ለውጭ ባለሀብቶች ከማስረከብ ይልቅ ኢትዮጵያ የሚከተሉትን ብትፈጽም አዋጭ ዘዴ ይሆናል ስንል የዜግነት ምክራችንን እንለግሳለን፡-
• በኢትዮ ቴሌኮም ውስጥ መልካም አስተዳደርና ግለጸኝነትን ማጎልበት
• ከበቂ የጥሬ ገንዘብ ፍሰትና የግብይት ድጋፍ ጋር በኢትዮጵያ የመዋለ ነዋይ ሰነድ ገበያ በአግባቡ የአክሲዮን ድሻዎችን ይፋ ማድረግ
• ለአነስተኛ የአክሲዮን ባለድረሻዎች የዋስትና ከለላ በመስጠት መጠነ ሰፊ የዜጎችን ተሳትፎ መፍቀድ
• አክሲዎኖች በግልጽ የሚገዙበትና የሚሸጡበት ሀቀኛ የካፒታል ገበያ ማጎልበት
• በቴሌ ኮም ዘርፍ ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች በኢትዮጵያን ጥብቅ ቁጠጥር ስር እንዲዘልቁ ማድረግ
እምነትን፣ ገበያንና ተቋማትን መገንባት ወሳኝ ነው፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ለህዝብ የቀረበው የቴሌ የአክሲዮን ድረሻ ሽያጭ በሚገባ ባለመታቀዱና በይድረስ ይድረስ በመከናወኑ የተጠበቀውን ያህል ውጤት አላስገኝም፡፡ ይህ ሁኔታ እንደ ኢትዮ ቴሌኮም ያለን የወርቅ እንቁላል የምትጥልን ዶሮን ለውጭ ባሀብት ለመሸጥ የሚያንደረድር አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ የሌሎች ሀገሮችን ስህተት መድገም የለባትም፡፡
እጅግ የከበረ ብሄራዊ ሀብቷን በአንድ ጊዜ ብቻ በሚገኝ ሽያጭ ለባእዳን ማስተላለፍን አሻፈረኝ በማለት የወደፊት መፃይ እድሏን የመወሰን እጣ ፈንታዋን የመወሰን ምርጫ አላት፡፡ እንደ ሞኙ ሁለት ጊዜ በእባብ ከመነደፍ እንጠንቀቅ!
TIPS
የውጭ ዜጎችን የመሬት ባለይዞታ የሚያደርግ ረቂቅ አዋጅ ነገ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይቀርባል
ሞኝን እባብ ሁለቴ ነደፈው – አንዴ ሳያይ፣ ሁለተኛ ደግሞ ሲያሳይ <br>(ክቡር ገና)
አሌክሳንደር ኢሳክ ከኒውካስል ሊለቅ ይችላል ተባለ
ኢዜማ የህክምና ባለሙያዎችና መንግስትን መከረ፤ ሰላማዊና ሕጋዊ የመብት ጥያቄ ብቻ
የሻዕቢያና የወያኔ ሶስት የቢሆን ዕቅዶችና ወቅታዊ ግምገማዎች፤ ያኮረፈው አርሚ ስጋት ሆኗል
የውጭ ባንኮች 2018 አጋማሽ ላይ ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
“ሾልኮ ወጣ” የተባለው የዝርፊያ ሰነድና ለትግራይ ጊዜያዊ አስተዳር የቀረበ ምላሽ
የኢትዮጵያ ነርሶች ማህበር ታካሚዎች ለሞትና እንግልት እንዳይዳረጉ አስጠነቀቀ
የኢትዮጵያ ህክምና ባለሙያዎች ማህበር የመፍትሄ አካል ለመሆን እንደሚተባበር አስታወቀ
የዶላር አካውንት፣ ቪዛ ካርድና አጠቃቀሙ
“ሦስትን ወደ አራት ” ከቨርጂናው ዳማ ሆቴል የተጸነሰ ሤራ – ከኢትዮ 360 ስቱዲዮ እስከ አራት ኪሎ
ትህነግ አፍሪካ ሕብረት አስቸኳስ ስብሰባ እንዲቀመጥ ጠየቀ፤ “የትህነግ መታገድ በፕሪቶሪያ ስምምነት እንቅፋት አይሆንም”
የዳታ ሉዓላዊነት የመንግስት ልዩ ትኩረት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አስታወቁ
ቅዱስ ሲኖዶስ ለመንግስት ከፍ ያለ ምስጋና ማቅረቡን አስታወቀ
የማይጨው ሰለፈኞች “የሻዕቢያ ተልእኮ ከሚያስፈፅም ሃይል ጋር ግንኙነት የለንም ” አሉ
የጤና ሞያ አድማ በህግ የተከለከለ መሆኑን ጤና ሚኒስትር አስታውቆ ማስጠንቀቂያ አሰራጨ