ቼልሲ ከሪያል ቤቲስ ጋር ያደረገውን የኮንፈረንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ 4ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፏል። የቼልሲን ግቦች ኢንዞ ፈርናንዴዝ ፣ ጄደን ሳንቾ ፤ ሞይሰስ ካይሴዶ ፣ እና ኒኮላስ ጃክሰን ማስቆጠር ችለዋል።
ኤንዞ ፈርናንዴዝ በዚህ የውድድር ዘመን በሁሉም ውድድሮች 8 ጎሎችን ሲያስቆጥር 13 አሲስት አድርጓል። ኮል ፓልመር በጨዋታው ሁለት ለግብ የሆነ ኳስ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል በዚህም ። የጨዋታው ኮከብ ተብሎ ተመርጧል
አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ በመጀመሪያ አመቱ ክለቡን ለቀጣይ አመት ቻምፕየንስ ሊግ ተሳታፊ እና ክልቡን የኮንፍረንሰ የዋንጫ ባለቤት አደረጎዋል። ቼልሲ የመጀመሪያውን የአውሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ ዋንጫ አሸንፏል።
ቼልሲ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር በክለብ ደረጃ የሚያዘጋጁትን የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ፣ የአውሮፓ ሊግ ፣የአውሮፓ ሱፐር ካፕ እና የአውሮፓ ኮንፍረንስ ሊግ ዋንጫዎች በማሸነፍ ብቸኛው እና የመጀመሪያው ክልብ በመሆነ ታሪክ ፅፏል።