ህንድ በፓኪስታን ላይ ጥቃት ለመሰንዘር መዘጋጀቷን የሚያመለክቱ ታማኝ የደህንነት መረጃዎች እንዳገኙ የፓኪስታን የማስታወቂያ ሚኒስትር ገልፀዋል፡፡
ሚኒስትሩ አታውላህ ታራር ህንድ ባለፈው ሳምንት የተፈፀመውን የፔልጋም ጥቃትን ምክንያት አድርጋ በፓኪስታን ላይ ጦርነት ለመክፈት እየተዘጋጀች እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
‹‹ማንኛውም ዓይነት የወረራ ተግባር ከባድ ምላሽ ይኖረዋል፡፡ በቀጣናው ለሚፈጠር አደገኛ ክስተት ህንድ ሙሉ ኃላፊነቱን ትወስዳለች›› ብለዋል፡፡
ሚኒስትሩ ‹‹ታማኝ›› ላሉት የደህንነት መረጃ ተጨባጭ ማስረጃ እንዳላቀረቡና ዝርዝር ነገር ከመናገር መቆጠባቸው ተገልጿል፡፡
የሀገሪቱ የመከላከያ ሚኒስትር ካዋጃ መሀመድ አሲፍ በበኩላቸው፣ ህንድ ጥቃት መሰንዘሯ እንደማይቀር ለ‹ሮይተርስ› የዜና ወኪል ተናግረዋል፡፡ ፓኪስታን በህልውናዋና በደህንነቷ ላይ አደጋ የሚፈጥር ሁኔታ ከተከሰተ የኑክሌር ጦር መሳሪያዎቿን እንደምትጠቀምም አስጠንቅቀዋል፡፡
የህንድ መንግሥት ግን የፓኪስታን ሚኒስትሮች በተናገሩት ላይ እስካሁን በይፋ የሰጠው መግለጫ የለም፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ባለፈው ሳምንት የጥቃቱ ፈፃሚዎች ለህግ እንደሚቀርቡና የሀገሪቱ የጦር ሰራዊት ምን ማድረግ እንዳለበት እንደሚያውቅና የመወሰን ነፃነትም እንዳለው ተናግረዋል፡፡
‹‹ህንድ እያንዳንዱን አሸባሪና ደጋፊውን ትለያለች፣ ትከታተላለች፣ ትቀጣለች፡፡ ይህን መላው ዓለም ይወቅ›› በማለት የጥቃቱን ፈፃሚዎች እንደሚበቀሉ ቃል ገብተዋል፡፡
የመከላከያ ሚኒስትሩ ራጅናት ሲንግ በበኩላቸው፣ ህንድ የምትቀጣው ጥቃቱን የፈፀሙትን ብቻ ሳይሆን ያቀዱትንም ጭምር እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ባለፈው ሳምንት ህንድ በምትቆጣጠረው የካሽሚር ግዛት ውስጥ በምትገኘው ፔልጋም በተፈፀመ ጥቃት 26 ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎ ለወትሮውም በቋፍ የነበረው የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በእጅጉ ሻክሯል፡፡
25 ህንዳውያንና አንድ ኔፓላዊ ከሆኑት ከሟቾቹ መካከል አብዛኞቹ ቱሪስቶች እንደነበሩ ተገልጿል፡፡ ‹‹ሬዚስታንስ ፍሮንት›› (The Resistance Front – TRF) የተባለው ታጣቂ ቡድን ለጥቃቱ ኃላፊነቱን ወስዷል፡፡
ህንድ ጥቃቱን የፈፀመውን ቡድን ያሰለጠነችውና ያስታጠቀችው ፓኪስታን እንደሆነች በጽኑ ታምናለች፡፡ ቡድኑ ከሃሳብ ጀምሮ የመሳሪያና የስልጠና ድጋፍ ያገኘው በፓኪስታን የመከላከያና ደህንነት መስሪያ ቤት አማካኝነት እንደሆነ ገልፃለች፡፡
በተጨማሪም ፓኪስታን ውስጥ ከሚገኙ ሌሎች ታጣቂ ቡድኖች ጋር ግንኙነት አለው ብላለች፡፡ ፓኪስታን በበኩሏ በድርጊቱ እጇ እንደሌለበት ገልፃ፣ ጥቃቱ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ጠይቃለች፡፡
ጥቃቱን ተከትሎ ሁለቱ ሀገራት በየፊናቸው ከአፈሙዝ መልስ ያሉ ምጣኔ ሀብታዊና ዲፕሎማሲያዊ ርምጃዎችን ወስደዋል፡፡
ህንድ ከፓኪስታን ጋር የሚያዋስናትን ድንበር ዘግታለች፡፡ ፓኪስታን ለመስኖ እርሻዋ ከሚያፈልጋት ውሃ ውስጥ 80 በመቶ ያህሉን ከምታገኝበት የኢንደስ ውሃ ስምምነት (Indus Waters Treaty (IWT) መውጣቷን አውጃለች፡፡
አንዳንድ ፓኪስታናውያን ህንድን ለቀው እንዲወጡም ቀነ ገደብ አስቀምጣለች፡፡ ፓኪስታን በበኩሏ ድንበሯንና የአየር ክልሏን መዝጋቷን አስታውቃለች፡፡
ከህንድ ጋር ያላትን የንግድ ልውውጥም አቋርጣለች፡፡ ከዚህ ባሻገር በሁለቱ ሀገራት ድንበር አቅራቢያ የተኩስ ልውውጦች መደረጋቸውም ተሰምቷል፡፡
ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሁለቱ ባለኑክሌር ሀገራት የገቡበትን ፍጥጫ እንዲያረግቡ እየጠየቀ ነው፡፡
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ከፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትርና ከህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ባደረጉት ውይይት፣ ሀገራቱ መጥፎ ውጤቶችን ሊያስከትሉ የሚችሉ መፋጠጦችን እንዲያረግቡ አሳስበዋል፡፡
አሜሪካም ሁለቱ ሀገራት ኃላፊነት የተሞላበት አካሄድን እንዲከተሉ ጠይቃለች፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማርኮ ሩቢዮ ሀገራቱ ነገሮችን ከማባባስ እንዲቆጠቡ መምከራቸውን መስሪያ ቤታቸው አስታውቋል፡፡ ሌሎች ሀገራትም ውጥረቱን ለማርገብ ሚናቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡
ህንድና ፓኪስታን በአወዛጋቢውና ከፍተኛ ስትራቴጂካዊ ጥቅም እንዳለው በሚነገርለት የካሽሚር ግዛት ምክንያት ፍጥጫ ውስጥ ኖረዋል፡፡
በግዛት ይገባኛል የሚወዛገቡት ሁለቱ ጎረቤቶች ካሽሚርን ተከፋፍለው እያስተዳደሩ ቢሆንም፣ ሙሉውን ግዛት ለመጠቅለል ባላቸው ፍላጎት ምክንያት ሦስት ታላላቅ ጦርነቶችን አድርገዋል፤በርካታ ግጭቶችንም አስተናግደዋል፡፡
በአንተነህ ቸሬ via ጋዜጣ_ፕላስ
TIPS
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring
Ethiopia’s peaceful quest for access to sea gained int’l recognition: PM Abiy