ጋሽ ክቡር ገና ቴሌ ለውጭ ባለሃብት የአክሲዮን ድርሻ መሸጥ የለበትም በማለት ምክንያታቸውን ዘርዘር አድርገው አካፍለውናል። እንዲሁም የአለም የፋይናንስ እና የባንክ ተቋማት የሚሰጡን ምክረ ሃሳብ ሃገራችንን እንደ አርጀንቲና እና ሌሎች ሃገራት ሊያዳክም እንደሚችል ገልፀዋል። ይህን ምልከታቸውን መሰረት አድርጌ በተለይ ስለአለም አቀፍ የንግድ ኩባንያዎች፣ ስለወርቃማ አክሲዮን እና ዲጅታል ሉዓላዊነት የራሴን ምልከታ ላካፍላችሁ ወደድኩ። እነሆ!
የሃቬር ሜሌ የአርጀንቲና የኢኮኖሚ ማሻሻያ ተአምራዊ እየተባለ ነው። ማሻሻያው ከIMF እና የዓለም ባንክ ምክረ ሃሳብ የመነጨ ሳይሆን ፕሬዝዳንቱ ከሚከተለው ሊብርትሪያን ፓለቲካ የኢኮኖሚ ፍልስፍና (libertarian political Economy) የመነጨ ነው። በሂደቱ እነዚህ ባለብዙ ወገን የዓለም የፋይናንስ ተቋማት የፋይናንስ ድጋፍ አድርገውለታል።
የአለም የፋይናንስ ተቋምና ባንክ(IMF & WB) ለኢትዮጵያ መንግስት የሃገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ በሰጡት ምክረ ሃሳብ መንግስት የልማት ድርጅቶችን ለውጭ ባለሃብት መሸጥ እንዳለበት አያስገድድም። ይልቅ አዋጭነቱን መዝኖ የልማት ድርጅቶችን ለሕዝብ ወይም ለውጭ ባለሃብት አክሲዮን ድርሻ በመሸጥ ሊያስተዳድር ይችላል።
ልክ አልባው ጥርጣሬ..
እኔ የማይገባኝ ግን የውጭ ካምፓኒ ሃላፊነት የማይሰማቸው ዘራፊ እና አታላይ ተደርጎው መፈረጃቸው ነው። ያትውልድ ከሚከተለው ርዕዮት አለም የመነጨ ወይም የሶቭየት ፕሮፓጋንዳ ሰለባ በመሆኑ የዓለም አቀፍ ተቋማት ላይ እምነትና መተማመን እንዳይኖረን አድርጓል። ይህ አጉል ፍርጃ በዚህ የመረጃ ዘመንም ቀጥሏል። ያሳዝናል።
ከኛ በላይ ሃላፊነት የሚሰማቸው ስለመሆኑ….
ጌታዬ! አለም አቀፍ ካምፓኒዎች ለመልካም ስማቸው፣ ለንብረት ባለቤትነታቸውና ስራቸው እና ለሰራተኞቻቸው አብዝተው የሚጨነቁ ናቸው። እንዲሁም ስለ ኢኮኖሚ ርትዕ፣ ማህበራዊ ሃላፊነት እና ፍቃድ(Social licensing)፣ የንግድ ስራ ማስፋፋት(Expansion)፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር ወዘተ ላይ የተመሰረት ተግባራትን ይፈፅማሉ። እነ ቻይና እና የኤዥያ ሃገራት በዚህ መልኩነው ያደጉት። የውጭ ካምፓኒዎችን በጠቅላላው በዝባዥ አድርጎ መፈረጅ ተገቢ አይመስለኝም።
ይልቅ ሊያሳስበን የሚገባው ጉዳይ…..
አንደኛ አሁን ኢትዮጵያ ያለችበት ቀጠናዊ የጂኦፓለቲካ ሁኔታ እውነተኛዎቹ የውጭ ካምፓኒዎች መዋዕለ ንዋያቸውን ኢንቨስት እንዲያደርጉ ተገማችና ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል ወይ? የሚለው ነው።
ሁለት፣ የንግድ ህጉ ውስጥ ልዩ የውሳኔ ስልጣን (መብት) የሚሰጥ የወርቃማ አክሲዮን መርህ በማስገበት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ለውጭ ባለሃብቶች አክሲዮን ድርሻ በመሸጥ ወይም አዲስ የንግድ ድርጅት በሽርክና በማቋቋም የሚሰሩበትን ምቹ ሁኔታ መፍጠር ይችላል። ይህ ወርቃማ አክሲዮን ለመንግስት የልማት ድርጅቶች ልዩ መብት ስለሚሰጣቸው እርሰዎ የጠቀሷቸውን ችግሮች ለመቅረፍ ያስችላል።
ሶስተኛ የቴል የዲጅታል መሰረተ ልማቶች በኛ ሃገር ያልተመረቱ በመሆናቸው የዲጅታል ሉአላዊነት የለንም፣ በማንኛውም ሰዓት ለደህንነት ስጋት ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ ነው። ስለዚህ ቴሌ ለውጭ ባለሃብት ድርሻ ባይሸጥም ተጋላጭነቱ እንዳለ ነው። ይልቅ እነዚህ ድርሻ የሚገዙ የውጭ ኩባንያዎች የተሻለ ቴክኖሎጂ ተጠቅምው የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነታችንን ሊቀንሱት ይችላሉ።
አክባሪዎ!
TIPS
ሱዳን ያለባትን የኤሌክትሪክ እዳ ለመፍፈል 1 ዓመት ከ6 ወር እንዲሰጣት ጥያቄ አቀረበች
በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የተሰጠ መግለጫ
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ታላቅ የምረቃ ሥነስርዓት ፤ የሁለተኛው ግድብና ዘመናዊ ከተማ መሰረት ይጣላል፤
በተለይ ወንዶች ላይ የሚከሰተውን የፕሮስቴት ካንሰርን በተመለከተ ሊያውቋቸው የሚገቡ ነገሮች
የአፍ ምሬት ከምን ይመጣል?
በደህንነት ስጋት ለጊዜው ማንኛውም የዳኝነት አገልግሎት መስጠት አቁመናል ” መቐለ ፍርድ ቤት
” የቅድመ ክፍያ መጠን ከ5 ሺህ ወደ 50 ሺህ ዶላር ከፍ ተደርጓል ” ብሔራዊ ባንክ
ይድረስ ለክቡር ገና…. ስለወርቃማ አክሲዮንና ዲጅታል ሉዓላዊነት የራሴን ምልከታ
የውጭ ዜጎችን የመሬት ባለይዞታ የሚያደርግ ረቂቅ አዋጅ ነገ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይቀርባል
ሞኝን እባብ ሁለቴ ነደፈው – አንዴ ሳያይ፣ ሁለተኛ ደግሞ ሲያሳይ <br>(ክቡር ገና)
አሌክሳንደር ኢሳክ ከኒውካስል ሊለቅ ይችላል ተባለ
ኢዜማ የህክምና ባለሙያዎችና መንግስትን መከረ፤ ሰላማዊና ሕጋዊ የመብት ጥያቄ ብቻ
የሻዕቢያና የወያኔ ሶስት የቢሆን ዕቅዶችና ወቅታዊ ግምገማዎች፤ ያኮረፈው አርሚ ስጋት ሆኗል
የውጭ ባንኮች 2018 አጋማሽ ላይ ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
“ሾልኮ ወጣ” የተባለው የዝርፊያ ሰነድና ለትግራይ ጊዜያዊ አስተዳር የቀረበ ምላሽ
የኢትዮጵያ ነርሶች ማህበር ታካሚዎች ለሞትና እንግልት እንዳይዳረጉ አስጠነቀቀ