” በላያችን ላይ ያንዣበበው የደህንነት ስጋት መፍትሄ እስኪበጅለት ድረስ ለጊዜው ማንኛውም የዳኝነት አገልግሎት መስጠት አቁመናል ” – ፍርድ ቤት
ዛሬ ግንቦት 12 /2017 ዓ.ም በመቐለ ማእከላይ ፍርድ ቤት ደጃፍ የተለጠፈው ማስታወቂያ፥ ” በላያችን ላይ ያንዣበበው የደህንነት ስጋት መፍትሄ እስኪበጅለት ድረስ የመቐለ ማእከላይ ፍርድ ቤት ጨምሮ በሰባቱ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ዳኞችና ፍርድ ቤቶች ለጊዜው ማንኛውም የዳኝነት አገልግሎት መስጠት አቁመዋል ” ይላል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የማስታወቂያውን ትክክለኝነት ለማረጋገጥ ሐውልት ፣ ዓይደር ፣ ቀዳማይ ወያነ ወደ ተባሉ ክፍለ ከተሞች ተዘዋውሮ ተመልክቷል።
በዚህም ማንኛውም አይነት አገልግሎት መቆሙን አረጋግጧል።
ዛሬ ከሰዓት በኋላ ደግሞ የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ፍርድ ቤቶቹ መዘጋታቸው አረጋግጦ ለመዝጋታቸው ምክንያት የሆነ ችግር አጣርቶ እርምጃ እንደሚወስድ ቃል ገብቶ ዳኞቹ ወደ ስራ ገበታቸው እንዲመለሱ ተማፅኗል።
ለመሆኑ ፍርድ ቤቶቹ እስከ ስራ ማቆም እርምጃ እንዲወስዱ የገፋፋቸው ምክንያት ምንድን ነው ?
ባለፈው አርብ ግንቦት 8/2017 ዓ.ም በመቐለ ማእከላይ ፍርድ ቤት ዘውዱ የተባለች ሟች ላይ የተፈፀመ ወንጀል ለመዳኘት በተጠራው ችሎት ላይ የበዳይ ተጠርጣሪ ቤተሰቦች ችሎቱ ከመረበሽ በዘለለ በዳኞችና አቃቤ ህግ ላይ መጥፎ ቃላት በመጠቀም ዝተዋል።
በረብሻው ምክንያትም በዛው ቀን በተጠርጣሪዎች ላይ ሊሰጥ የነበረው የመጨረሻ ውሳኔ ተሰርዞ ለግንቦት 18/2017 ዓ.ም ተለዋጭ ቆጠሮ ተይዘዋል።
ይህንንና ሌሎች ስጋቶች ” አላሰራ ብለውኛል ” ያለው የትግራይ ዳኞች ማህበር በፍትህ አረጋጋጭ ዳኞች ላይ የሚታዩ ችግሮች ካልተፈቱ እስከ ስራ ማቆም የሚደርስ እርምጃ እንደሚወስድ ግንቦት 9/2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አሳውቆ ነበር።
ይህንን ተከትሎ ዛሬ ግንቦት 12/2017 ዓ.ም የስራ ማቆም እርምጃ ወስዷል። እርምጃው የጀመረበት እንጂ የሚቆምበት ቀን አልተገለፀም።
ዳኞችና ፍርድ ቤት ለጠሩት ስራ የማቆም አድማ ምክንያት የሆነው ችግር ትኩረት ሰጥቶ እንደሚፈታ የገለፀው የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ዳኞች የህዝባዊ አገልግሎታቸውን እንዲቀጥሉ በማመፀን የተፈጠረው ችግር በአስቸኳይ አጣርቶ ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ቃል ገብቷል።
Via ቲክቫህ
TIPS
ሱዳን ያለባትን የኤሌክትሪክ እዳ ለመፍፈል 1 ዓመት ከ6 ወር እንዲሰጣት ጥያቄ አቀረበች
በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የተሰጠ መግለጫ
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ታላቅ የምረቃ ሥነስርዓት ፤ የሁለተኛው ግድብና ዘመናዊ ከተማ መሰረት ይጣላል፤
በተለይ ወንዶች ላይ የሚከሰተውን የፕሮስቴት ካንሰርን በተመለከተ ሊያውቋቸው የሚገቡ ነገሮች
የአፍ ምሬት ከምን ይመጣል?
በደህንነት ስጋት ለጊዜው ማንኛውም የዳኝነት አገልግሎት መስጠት አቁመናል ” መቐለ ፍርድ ቤት
” የቅድመ ክፍያ መጠን ከ5 ሺህ ወደ 50 ሺህ ዶላር ከፍ ተደርጓል ” ብሔራዊ ባንክ
ይድረስ ለክቡር ገና…. ስለወርቃማ አክሲዮንና ዲጅታል ሉዓላዊነት የራሴን ምልከታ
የውጭ ዜጎችን የመሬት ባለይዞታ የሚያደርግ ረቂቅ አዋጅ ነገ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይቀርባል
ሞኝን እባብ ሁለቴ ነደፈው – አንዴ ሳያይ፣ ሁለተኛ ደግሞ ሲያሳይ <br>(ክቡር ገና)
አሌክሳንደር ኢሳክ ከኒውካስል ሊለቅ ይችላል ተባለ
ኢዜማ የህክምና ባለሙያዎችና መንግስትን መከረ፤ ሰላማዊና ሕጋዊ የመብት ጥያቄ ብቻ
የሻዕቢያና የወያኔ ሶስት የቢሆን ዕቅዶችና ወቅታዊ ግምገማዎች፤ ያኮረፈው አርሚ ስጋት ሆኗል
የውጭ ባንኮች 2018 አጋማሽ ላይ ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
“ሾልኮ ወጣ” የተባለው የዝርፊያ ሰነድና ለትግራይ ጊዜያዊ አስተዳር የቀረበ ምላሽ
የኢትዮጵያ ነርሶች ማህበር ታካሚዎች ለሞትና እንግልት እንዳይዳረጉ አስጠነቀቀ