“የኢትዮጵያ መንግስት በመጪው ዓመት መስከረም ወር መጨረሻ የታላቁ ህዳሴ ግድብን በታላቅ ድምቀት ለማስመረቅ ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገ ነው” የሚል መረጃ እዚህ ሰፈር ሲዘዋወር ተመልክቼ “የአዋጁን በጆሮ” ቢሆንብኝ ጊዜ እንሆ የግል ምልከታዬን ላጋራችሁ ወደድኩ።
[መረጃው ትክክል ነው] መንግስት በመጪው ዓመት የህዳሴ ግድብን በማጠናቀቅ የሺህ ዘመናት የኢትዮጵያውያን ተከታታይ ትውልዶች ጥያቄ የነበረውን “ዓባይን በቤቱ የማሳደር ህልም እውን አድርጎ በአፍሪካ ታላቁን ግድብ ፍጻሜ በታላቅ ድምቀት ያስመርቃል።
ዝግጅቱ በትንሹ ሁለት ሣምንት የሚወስድ ሲሆን ሌሎች ዝርዝር ክንዋኔዎች እንደተጠበቁ ሆኖ ከዚህ እንደሚከተለው በዝርዝር የቀረቡ ተግባራት የምረቃ ሥነስርዓቱ አካል ናቸው፦
❶ የህዳሴ ግድቡን እውን ያደረገው ይህ ትውልድ በዓይነቱ ልዩ የሆነ እውቅናና ሽልማት ይበረከትለታል፤ መታሰቢያም ይቆምለታል፣
❷ የወዳጅ ሃገራት መሪዎችና በግድቡ ግንባታ ከኢትዮጵያ ጎን የተሰለፉ ተቋማትና ታዋቂ ግለሰቦች ይታደማሉ፤ እውቅናም ይሰጣቸዋል፣
❸ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ- ሥርዓት በጉባ ተራራ ጫፍ ላይ ይከናወናል፣
❹ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ተወካዮች በሙሉ ይታደማሉ፤ ባህላዊ ትርዒትም ያቀርባሉ፣
❺ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ደማቅ ትርዒት ያቀርባል፤ አየር ሃይል የአየር ላይ ትርዒት የሚያቀርብ ሲሆን ባህር ሃይል በተመሳሳይ ደማቅ የባህር ላይ ትርዒት ያቀርባል፤ በምረቃ ሥነስርዓቱ የፌድራል ፖሊስ ዝግጁ ያደረገው የባህር ሃይል ፖሊስ (Navy Police) ወደስራ ይገባል፤ ደማቅ ትርዒትም ያቀርባል፣
❻ የግድቡን ዙሪያ ተከትሎ የታላቁ ዓባይ ወንዝ ማራቶን (The Grand Nile River Marathon) ይካሄዳል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚታወቁ አትሌቶች ጥሪ ይደረጋል። የእግርኳስ ውድድርን ጨምሮ ሌሎች ስፖርታዊ ውድድሮች ይደረጋሉ።
❼ ደማቅ የሙዚቃ ኮንሰርት ይደረጋል፤ የአገር ውስጥና የውጭ ታዋቂ ዘፋኞች የሙዚቃ ዝግጅታቸውን ያቀርባሉ፤
❽ በዓባይ ወንዝ ላይ የሚገነባው ሁለተኛው የሃይልና መስኖ ግድብ መሰረት ይጣላል፤
❾ በህዳሴ ግድብ አቅራቢያ ለሚገነባው እጅግ ዘመናዊ ከተማ የመሰረተ ድንጋይ ይቀመጣል፣
❿ ሁሉም ክንውን በቀጥታ ሥርጭት (live streaming) በዓለም ዙሪያ ይተላለፋል፤ ታዋቂ የሚዲያ ተቋማት ይጋበዛሉ፣
via Getenet Aleaw
TIPS
ሱዳን ያለባትን የኤሌክትሪክ እዳ ለመፍፈል 1 ዓመት ከ6 ወር እንዲሰጣት ጥያቄ አቀረበች
በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የተሰጠ መግለጫ
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ታላቅ የምረቃ ሥነስርዓት ፤ የሁለተኛው ግድብና ዘመናዊ ከተማ መሰረት ይጣላል፤
በተለይ ወንዶች ላይ የሚከሰተውን የፕሮስቴት ካንሰርን በተመለከተ ሊያውቋቸው የሚገቡ ነገሮች
የአፍ ምሬት ከምን ይመጣል?
በደህንነት ስጋት ለጊዜው ማንኛውም የዳኝነት አገልግሎት መስጠት አቁመናል ” መቐለ ፍርድ ቤት
” የቅድመ ክፍያ መጠን ከ5 ሺህ ወደ 50 ሺህ ዶላር ከፍ ተደርጓል ” ብሔራዊ ባንክ
ይድረስ ለክቡር ገና…. ስለወርቃማ አክሲዮንና ዲጅታል ሉዓላዊነት የራሴን ምልከታ
የውጭ ዜጎችን የመሬት ባለይዞታ የሚያደርግ ረቂቅ አዋጅ ነገ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይቀርባል
ሞኝን እባብ ሁለቴ ነደፈው – አንዴ ሳያይ፣ ሁለተኛ ደግሞ ሲያሳይ <br>(ክቡር ገና)
አሌክሳንደር ኢሳክ ከኒውካስል ሊለቅ ይችላል ተባለ
ኢዜማ የህክምና ባለሙያዎችና መንግስትን መከረ፤ ሰላማዊና ሕጋዊ የመብት ጥያቄ ብቻ
የሻዕቢያና የወያኔ ሶስት የቢሆን ዕቅዶችና ወቅታዊ ግምገማዎች፤ ያኮረፈው አርሚ ስጋት ሆኗል
የውጭ ባንኮች 2018 አጋማሽ ላይ ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
“ሾልኮ ወጣ” የተባለው የዝርፊያ ሰነድና ለትግራይ ጊዜያዊ አስተዳር የቀረበ ምላሽ
የኢትዮጵያ ነርሶች ማህበር ታካሚዎች ለሞትና እንግልት እንዳይዳረጉ አስጠነቀቀ