” የሂሳብ መዝገብ እንዲይዙ በህግ የሚገደዱ ግብር ከፋዮች ከመጪው ሀምሌ የግብር ማሳወቂያ ወር ጀምሮ የተሟላ የሂሳብ መዝገብ በመያዝ ካልመጡ በስተቀር አይስተናገዱም “- የገቢዎች ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ከመጪው ዓመታዊ የግብር ማሳወቂያ ወር ጀምሮ የደረጃ “ሀ” እና “ለ” ግብር ከፋይ ሆነው በህግ የሚገደዱ ግብር ከፋዮች ያለ ሂሳብ መዝገብ የማይስተናገዱ መሆኑን አሳውቋል።
አይስተናገዱም የተባሉት በደረጃ “ሀ” እና “ለ” የግብር ከፋይነት የተመዝገቡ እና በህጉ መሰረት የሂሳብ መዝገብ እንዲይዙ የሚገደዱትን ብቻ ነው።
የቢሮው የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደተናገሩት በህጉ መሰረት የሂሳብ መዝገብ እንዲይዙ የሚገደዱ ነጋዴዎች ከሚቀጥለው በጀት አመት በኋላ ግብር ለመክፈል ያላቸውን አጠቃላይ ወጪ እና ገቢያቸውን በዝርዝር የሚያሳይ መዝገብ መያዝ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
አቶ ሰውነት አየለ በዝርዝር ምን አሉ ?
” የሂሳብ መዝገብ ማለት ያላቸውን አጠቃላይ ሽያጭ እና ወጪ በዝርዝር የሚያሳይ ሰነድ/መዝገብ ነው።
ህጋዊ የሆነ ግብይት የሚፈጸም ከሆነ እና በደረሰኝ ላይ የተመሰረተ ግብይት ካለ ከዚህ መዝገብ ጋር ተያይዞ ነው የሚቀርበው።
ይህ ህግ ከወጣ ረጅም ጊዜ ነው ነገር ግን አፈጻጸም ላይ የተለያዩ ክፍተቶች በመኖራቸው በቁርጥ ግብር የሚስተናገዱ ነበሩ።
ለእነዚህ ግብር ከፋዮች በተለያየ መንገድ መረጃዎችን እያደረስን ነው ያለነው ከሚቀጥለው በጀት አመት በኋላ ከዚህ ሂሳብ መዝገብ ውጪ እንደማናስተናግዳቸው እንዲያውቁ እያደረግን ነው።
ግብይቶቻቸውን በደረሰኝ ላይ ተመስርተው ፈጽመው በሂሳብ ባለሙያ አልያም የድርጅታቸው ተቀጣሪ በሆነ የሂሳብ ባለሙያ የተዘጋጀ የሂሳብ መዝገብ ማቅረብ አለባቸው።
ግብር ከፋዮች ከግምት የጸዳ የግብር አሰባሰብ ስርዓት የራሳቸውን ሚና እንዲጫወቱ ለማስቻል ይህንን የማሳወቅ ስራ እየሰራን ነው።
በደረጃ “ሀ” እና “ለ” ከ120 ሺ በላይ ግብር ከፋዮች አሉ ከእነዚህ ውስጥ ገቢ እና ወጪያቸውን በአግባቡ እየመዘገቡ ፣ደረሰኝ እየቆረጡ አመታዊ ግብራቸውን የሚያሳውቁ አሉ ነገር ግን ከዚህ ውጪ ሲስተናገዱ የቆዩ ግብር ከፋዮቾም ነበሩ።
ይህ አሰራር ተለምዶ ከአመት አመት ዝም ብሎ በቁርጥ ግብር ለመስተናገድ የመፈለግ አዝማሚያ ይታያል ህጉ ግን ይህንን አሰራር የማይፈቅድ በመሆኑ ከመጪው ሐምሌ ወር ጀምሮ ሲመጡ በተሟላ መንገድ ሂሳብ መዝገባቸውን ይዘው ካልመጡ በስተቀር አይስተናገዱም።
መያዝ አለባቸው እያልን ያለነው በደረጃ “ሀ” እና “ለ” የግብር ከፋይ ተመዝግበው በህጉ መሰረት የሂሳብ መዝገብ እንዲይዙ የሚገደዱትን ብቻ ነው።
ሁሉንም ማለት አይደለም በተሰማሩበት የንግድ ዘርፋቸው ምክንያት እዚህ ውስጥ የማይካተቱ ይኖራሉ የሚመለከተው የተሰማሩበት የስራ ዘርፍ የሂሳብ መዝገብ መያዝ እያስገደዳቸው በተለያየ ምክንያት የማይዙትን እና በቁርጥ ግብር ሲስተናገዱ የነበሩ የንግዱን ማህበረሰብ ነው።
ይህ አይነቱ አሰራር ግብር በዛብኝ በማለት ለሚቀርቡ ቅሬታዎች መፍትሄ የሚሆን ነው ” ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
TIPS
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring
Ethiopia’s peaceful quest for access to sea gained int’l recognition: PM Abiy