የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት እና ልማት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊና የጽህፈት ቤት ኃላፊ ከስልጣናቸው መነሳታቸው ተሰማ።
“የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባዶ መሬት ይዘወርበታል” ተብሎ የሚነገርለት ይህ ተቋም፤ የተለያዩ ኃላፊዎች ለአጭር ጊዜ የሚቆዩበት እንደሆነ ይታወቃል።
አሁን ደግሞ የቢሮ ኃላፊው አቶ ሲሳይ ጌታቸውና የጽህፈት ቤት ኃላፊው አቶ ካሊድ ነስረዲን ከአርብ ሚያዚያ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ከኃላፊነታቸው እንደተነሱ ሰምተናል ።
በከንቲባ አዳነች አቤቤ ደብዳቤ ከስራቸው የተነሱት ሁለቱ ኃላፊዎች ቀጣይ ማረፊያ የት እንደሆነ አልታወቀም ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ያሉ ባዶ ቦታዎች፤ ለሊዝ ሽያጭ፣ ለምደባ፣ ለኢንቨስተር የሚሰጡት በዚህ ቢሮ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ ካሉት ወሳኝ እና ቁልፍ ተቋማት ውስጥ አንዱ ነው።
ማህበራዊ ችግር ያለባቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን ከተረጂነት ባለፈ በቂ ስልጠና በመስጠት መስራት የሚችሉትን የማሸጋገር ስራ ሰርተናል።ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የኑሮ ውድነትና ጫናን ለማቃለል አለም አቀፋዊ ሁኔታን አገናዝበን ምላሽ ለመስጠት ሞክረናል።
* ኑሮ ውድነትን ለመቅረፍ አቅርቦትን ማሳደግ ላይ በትኩረት በመስራት በአምስቱም የከተማችን መግቢያ በሮች የግብርና ምርቶችን አቅርቦትን ተደራሽ ማድረግና የደላሎችን ሰንሰለት መበጣጠስ ችለናል።
* የኑሮ ውድነት ችግርን ማቃለል የምንችልበት መንገድ አምራችነትን በማሳደግ እንደመሆኑ መጠን የከተማችን ነዋሪ በተለያዩ አግባባች አምራችነቱ እንዲያድግ ስልጠና የመስጠትና የግብአት አቅርቦት እገዛ እያደረግን ነው።
* የገበያ ማረጋጋት ስራን በተመለከተ በቁጥጥር፣ በክትትልና፣ በድጎማ ህቦረተሰባችንን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየሰራን ነው።ውጤትም አግኝተንበታል።
* ለማህበራዊ ችግር የተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎችና የእናቶችን የኑሮ ጫና ለማቃለል የሰራነው ስራ ሁሌም የምንኮራበት ነው።
* 26 የምገባ ማዕከላን በመክፈት ዝቅተኛ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመመገብ ፍትሀዊ ተጠቃሚነታቸዉን ከማረጋገጥ ባሻገር ዜጎች አብሮ የማደግ ባህል እንዲጎለብት አድርገናል።
* 2የገበያ ማዕከላት ተጨማሪ በመገንባት የምርት አቅርቦት እንዲጨምርና የግብይት ስርዓቱ እንዲዘምን በትኩረት እየተሠራ ነዉ::
ኢትዮሪቬውን ከታች ባሉት ማስፈንጠሪያዎች የከተሉ – የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ @ethioreview
ፌስቡክ ገጻችንን ላይ