እየተንገዳግደ የፕሪማየር ሊጉን ዋናጫ ባያነሳም ኤፍ ኤ ካፕን ጨምሮ ሌሎች ዋንጫዎችን መውሰድ የቻለው ማንችስተር ዩናይትድ ለዩሮፕያን ሊግ ፍጻሜ ከቶትንሃም ጋር ደርሷል። ማንችስተር አትሌቲክን በድምሩ ሰባት ለአንድ፣ ቶትነሃም ቦዶን በድምሩ አራት ለአንድ አሸንፈው ነው ለፍሳሚ የበቁት።
ለበርካታ ድል ሲተበቅ የነበረው አርሰናል በጉዳት ሳቢያ ቢንሸራተትም ከሁሉም ውድድር መውጣቱ ደጋፊዎቹን አበሳጭቷል። በፕሪምየር ሊጉ ታች የሚዳክሩት ሁለቱ ክለቦች ለፍጻሜ መገናኘታቸውን ተክትሎ ፍፃሜው ከአሁኑ ያሳስበኝ ጀምሯል “ ሲል አሞሪም ተነግሯል። አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ቡድኑ የዩሮፓ ሊግ አሸንፎ ደጋፊውን ለማስደሰት እንደሚጥር አስታውቋል።
“ ከአሁኑ ስለ ፍፃሜው መጨነቅ ጀምሬያለሁ፤ ምክንያቱም የማናሸንፍ ከሆነ ሁሉም ልፋታችን ጥቅም አልባ ይሆናል “ብሏል። በቀጣይ የሊጉ ጨዋታ ተጨዋቾቹ ለጉዳት እንዳይጋለጡ እያንዳንዱን ነገር መጠንቀቅ አለብን ሲሉ ሩበን አሞሪም አያይዘው ተናግረዋል።
” ቶተንሀም ከኖርዌይ ቡድኖች አይሻልም “ የቦዶ ተጨዋቾች በአገራቸው የክለቦች ታሪክ የመጀመሪያ በሆነው የፍጻሜ ማግስት ጨዋታ ቶተንሃምን አጣጥለው ነበር።
የኖርዌዩ ክለብ ቦዶ ግሊምት ተጨዋቾች ከመጀመሪያው ዙር ጨዋታ በኋላ በሀገሪቱ ለሚነበብ ጋዜጣ ቶተንሀም “ ደካማ ቡድን ነው “ ሲሉ ተችተው ነበር። ይሁንና አንድም የረባ ኳስ ሳይሞክሩ በሜዳቸው ተሸንፈዋል።
ደጋፊዎቻቸው ቢጫና ጥቁር ለብሰው ትንሹን ከተማ በጭስ አጥነው አዲስ ታሪክ ለማስመዝገብ ኒመኙም አልሆነም። ባልተለመደ ሁኔታ የክለቡ ተከላካይ ፍሬድሪክ ሾቮልድ ” ቶተንሀም የሚፈጥሩት ጫና በቀላሉ የሚቆም ነው በቀላሉ ይወድቃሉ ከኖርዌይ ሊግ ቡድኖች አይሻሉም ” ብሎ ቶተንሃምን የሚያክል ቡድን አጣጥሎ ነነበር። አንድሬ ጆርካን በበኩሉ ” የተሸነፍነው በቡድኑ ጫና ሳይሆን በግለሰቦች ጥረት ነው “ ሲል ተደምጧል።
ይህንን የሰሙት የቶተንሀም አሰልጣኝ አንሄ ፖስቴኮግሉ “ በጣም ጥሩ ዛሬ ምሽት ስታዲየሙ ሁሉንም ይናገራል ” ሲሉ ዝተዋል። እንዳሉትም ቦዶን በሜዳው አሸንፈው ወጥተዋል፡፡
ኢትዮሪቬውን ከታች ባሉት ማስፈንጠሪያዎች የከተሉ – የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ @ethioreview
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ ethioreview
ኤክስ ፡ twitter