በሱዳን ብሉናይል ግዛት፣ ለወራት ወታደራዊ ስልጠና ሲወስዱ የቆዩ በቁጥር በርከት ያሉ ታጣቂዎች፣ ከሰሞኑ የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጠው ወደ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መዝለቃቸውን ራሳቸውን ተጋዳላይ ያደረጉት ነዓምን ዘለቀ በግል የቲውተር ገጻቸው አሰራጩ።
አቶ ነዓምን ዋቢ ያደረጉት የዞብል ፖስት የተባለን ሚዲያ ነው። አቶ ነዓምን የጠቀሱት ይህ ገጽ ” … ከብሉናይል ሰልጥነው የመጡት ታጣቂዎች የቤንሻንጉል ጉሙዝ ተወላጆች ናቸው” ብሏል።
“በቁጥር በርከት ያሉ” የተባሉት ታጣቂዎች 170 እንደሚደርሱ በአቶ ነዓምን የመረጃ ምንጭ ተመልክቷል። የገቢትም በቤንሻንጉል አቅጣጫ እንደሆነ ተመልክቷል። “ተጋዳላይ” የሚባሉት አቶ ነዓምን የዞብል ፖስት የመረጃ ምንጮችን ማስፈንጠሪያ አያይዘው ያሰራጩት ምንጭ ይፋ ያልሆነበት ዜና “ይሄን ያህል ቁጥር ያላቸው ታጣቂዎች የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጠው ሲመጡ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት መረጃው አልነበረውም” ሲሉ ይወቅሳል።
“ከሻዕቢያ ጋር ጥብቅ ትስስር አላቸው” በመረጃዎች የሚከሰሱትና “ደም ቆጥረው በይፋ ከሻዕቢያ ጋር ገጥመው ኢትዮጵያ ላይ ዘመቻ ከፍተዋል” የሚባሉት አቶ ነዓምን በግል ቲውተር ገጻቸው ያሰራጩት ዜና፣ ታጣቂዎቹ ከብሉናይል የሱዳን ግዛት ወታደራዊ ስልጠና ወስደው ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ የተደረጉት 170 ያህል የጉሙዝ ታጣቂዎችን፣ በስልጠና፣ በቁሳቁስ፣ እና በጦርመሳሪያ አቅርቦት በኩል፣ የግብፅ ድጋፍ እንዳላቸው ጥርጣሬውን አስቀምጧል። ግብጽ ድጋፍ እንዳደረገችላቸው ጥርጣሬ እንዳላው ሆኖ የውቀረበው ዜና የታጣቂዎቹን ቁጥር፣ የሰለጠኑበትን ስፍራ፣ ይፋ ከማደረጉ አንጻር የሻዕቢያን ሚና አላነሳም።
በርዕሱ “በርካታ” በውስጡ ” 170 ታጣቂዎች” በሚል ትልቅ አጀንዳ ሆኖ አቶ ነዓምን ያሰራጩትን ዜና ያዩ የሚስት ፈላጊውንና ደላላውን ወግ እንደሚያስታውሱ ጠቁመዋል። ሚስት ፈላጊው ምን ዓይነት ሚስት እንደሚፈልጉ ተጥይቀው ለደላላው ሲያብራሩ “ረዘም ብላ አጠር ያለች፣ ወፈር ብላ አጠር ቀጠን ያለች፣ ደልደል ብላ …” በሚስት ፈላጊው መስፈርት የተገረመው ደላላ “እንዴት ነው ይሄ የሚሆነው?” በማለት ግራ መጋባቱን መግለጹን ያስታወሱት ክፍሎች የአቶ ነዓምንም ዜና “በርከት ያሉ፣ ነገር ግን አነስ ያሉ” እንደማለት መሆኑን ገልጸዋል። “ዜናው ያልገባን በብዛት ወይስ በጥቂት እንውሰደው?” ሲሉ አቶ ነዓምንን ጠይቀዋል።
ይህ ሁሉ ሰራዊት ድንበር አልፎ ዚገባ መንግስት እንዳላወቀ ተጠቅሶ የሚተቸውን ዜና ያሰራጩት አቶ ነዓምን ከልብ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያስቡ ከሆነ ማን የአዲስ አበባን የቤት ኪራይ እንደሰቀለው አንድ ቀን አጀንዳ በማድረግ እንዲሞግቱ ጥይቀዋል።
“የዘሬ ያንዘርዘኝ ካልሆነ የአዲስ አበባን ቤት ከነዋሪው በላይ በመክፈል በደቦ የሚከራዩት እነማን እንደሆነ ለመረዳት ዋቢ መጥቀስ አያስፈልግም” ሲሉ በቤኒሻንጉል በኩል ከሚገቡት መቶ ሰባ ታጣቂዎች በላይ ከኤርትራ የሚጋዙትና ሆን ተብሎ ኑሮ እንዲወደድ ስለሚደረገው የተጠና ዘመቻ አቶ ነዓምንም ሆነ ባልደረቦቻቸው ምንም አለማለታቸውን ዜናውን ተንተርሰው አንስተዋል።
አንድ ቤት በውድ እየተከራዩ ለሃያና ሰላሳ የሚኖሩ ኤርትራዊያን ዶላር ይለቅማሉ፣ ህገወጥ ተግባራት ላይ ተሰማርተው ሕዝብ እያማረሩ እንደሆነ ቦታና የወንጀል ዓይነቶችን በመጥቀስ የህዝብ ወኪሎች መንግስትን እየከሰሱ መሆኑ ለአቶ ነዓምን ዜና እንዳልሆነ እነዚሁ ወገኖች ይናገራሉ።
አቶ ነዓም በዚህ ማስረጃና ማመሳከሪያ በማያስፈልገው ጉዳይ ሕዝብ በተወለደበት ቀበሌና መንደር ሲሰቃይ አንድም ቀን ተንፍሰው የማያውቁት የሻዕቢያ ደም ስላላቸው እንደሆነ በተደጋጋሚ ይገለጻል። ህዝብ እንዲማረር ማድረግ ተናበው የሚያከናውኑት ዓላማቸው በመሆኑና ሕዝብ በምሬት ተነስቶ አገር እንዲበተን የህልማቸው ማሰሪያ መሆኑን የሚጠቁሙ፣ “አቶ ነዓምን ኢትዮጵያ ላይ ዓመጽ እንዲነሳ ተግተው የሚሰሩት በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ለመሆን ጠይቀው ስላልተፈቀደላቸው ብቻ ወይስ በሌላ ምክንያት?” ሲሉ የሚጠይቁት ክፍሎች፣ አሁን ላይ ተናበው የሚሰሩትን ሁሉ ለተመለከተ ምላሹ ግልጽ እንደሚሆን ያክላሉ።