ዛሬ ላይ የጃዋር መሐመድ በኦሮሚያ ምድር ላይ የነበረው የፖለቲካ ተሰሚነት በኗል። “ተጽዕኖ ፈጣሪ ነኝ” የሚለው የዕብለት ንግግሩ ከራሱም አንደበት ጠፍታል። የኦፌኮ አንዳንድ አመራሮች እንደሚሉት የጃዋር የፖለቲካ ህይወት ራሱ ተክለፍልፎ ገደል ከቶታል። በጥቅሉ የፖለቲካ ሕይወቱ ሙት ሆኗል። እናም አሁን ላይ ያለው ክፍት የፖለቲካ ሹመት ወደ ሰሜን በመሆኑ እዛ እየደነሰ ነው።
ይህ አስተያየት የተሰማው ሰሞኑን የኦነግ፣ ኦፌኮና የኦሮሞ ነጻ አውጪ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮችና ካድሬዎች ወደ ብልጽግና እየጎረፉ መሆኑን ተከትሎ አስተያየት የተጠየቁ ከተናገሩት ነው።
ከሳምንት በፊት ስዊዲን ማልሞ ሞቢሊያ ሞል ውስጥ ጃዋር መሀመድ ብቻውን ቲሸርት በሸሚዝ ለብሶ ደረጃ ሲወርድ አንድ ኢትዮጵያዊ ያገኘዋል። ምስክሩ እንዳለው በወቅቱ ጃዋር አንድም አጃቢ፣ አጫዋች፣ ቦርሳ ያዥ ወይም … አልነበረም። “ጃዋር” ሲል ይኸው ምስክር ጠርቶት ሲጠጋው ጃዋር በድንጋጤ ሊሮጥ ሲቃጣው “አይዞህ ሰላም ልልህ ነው። የወንዝህ ነኝ። ምነው ብቻህን?” ሲለው “እዚህ ባለቤቴ ጋር መጥቼ ነው” ሲል የመልሳል። አልቆመመ እየሄደ ነው።
በኦሮሚያ ኦርሞ ላይ ያነጣጠረ ዘመቻ እየከረረ መሆኑ ላይ መግባባት የተደረሰ ይመስላል። በተለይም መንግስትን ከኦሮሞነት ጋር በማያያዝ በአደባባይ ‘የጋላን መንግስት እናሳውግድ’ በሚል ባነር ተለጥፎ ቅስቀሳ በማድረግ የተጀመረው እንቅስቃሴ ‘ የኦሮሙማ እሳቤ’ በሚል በገሃድ መንግስትና ኦሮሞን፣ በሰዎች ማንነትና የትውልድ ስፍራ ለይቶ የመፈረጁ ዘመቻ ኦሮሞን ከሊቅ እስከ ደቂቅ አስኮርፏል። ለዚህም ይመስላል ከመቼውም በበለጠ በኦሮሚያ ፖለቲካው ከስሜትና ከግል ፍላጎት በጸዳ ሊከናወን እንደሚገባ ማሰብና መንቀሳቀስ የተጀመረው። እነዚሁ ወገኖች እንደሚሉት ሕዝብ እንደ ሕዝብ በደፈና በመፈረጃ ኢትዮጵያን ለማተራመስ ኢሳያስ የሚመሩት ጥምረት አካሄድ በጥንቃቄ ሊታይ ይገባል። የኦሮሞ ምሁራንና ባለሙያዎች ማህበርም ይህንኑ ነው አሳስቦ ለኢሳያስ ደብዳቤ የጻፈው። ኦሮሞማ ‘ኦሮሞነት’ ነው እንጂ የፖለቲካ እሳቤ ባለመሆኑ አንድን ሕዝብ ከማይሆን እሳቤና ትርጉም ጋር ሰፍቶ ለጥቃት ማጋለጥ እንደማይገባ እነዚሁ 84 የሚጠጉ ምሁራን ሲያሳስቡ ስማቸውን በይፋ አስፍረው ነው። እዚህ ዝርዝር ውስጥ ጃዋር የለበትም።
ጃዋር እስር ቤት እያለ ጤናውን ስትከታተለው ከነበረችውን ዶ/ር ኢሊሊ ጀማል ጋር ከማልሞ ቅርብ ርቀት በምትገኘው ሉንድ ለጊዜው አብሯት/ አብረው እንዳሉ ምስክሩ ያቅ ነበርና “አትፍራ ” ብሎት ተለየው። ይህ ምስክር የኦሮሞ ፌደራል ኮንግረንስ ደጋፊ ነው። ቅርብ የቤተሰቡ አባል በፓርቲው ውስጥ ቁልፍ ሰው ናቸው። በግል ደግሞ ፕሮፌሰር መረራን ይወዳል። ይህን መረጃ ከሰጠን በሁዋላ ጃዋርን አስመልክቶ በፓርቲው ውስጥ የተፈጠረውን ጠቆመንና ማጣራት አደረግን።
ከነጋገርናቸው ስድስት የኦፌኮ ሰዎች መካከል አምስቱ ” አባሎቻችን፣ ካድሬዎች፣ የዞን ተወካዮች፣ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት … ወደ ብልጽግና ማምራታቸው እውነት ነው” የሚል ምላሽ ሰጥተውናል። የፍልሰቱን ምክንያት ሲያስረዱ በዋናነት ጃዋርን ይጠቅሳሉ።
ስማቸው እንዳይተቀስ የጠየቁ የኦፊኮ አንድ አመራር መረጃው እውነት መሆኑን አምነው፣ መገፋት፣ ተስፋ መቁረጥ፣ አሁን ላይ “ኦሮሙማ” በሚል ኦሮሞን ለይቶ የማጥቃትና ለጥቃት እንዲጋለጥ የተጀመረውን ዘመቻ ለመመከት ወዘተ” የሚሉ ምክንያቶችን በማንሳት ድርጅቱን የለቀቁበትን ምክንያት እንዲያስረዱ በተጠየቁበት ወቅት መመለሳቸውን አስታውቀዋል። ከዚህ በላይ ዝርዝር መናገር እንደማይችሉ አምልክተዋል።
ወደ ብልጽግና ካመሩት የዞን አመራር መካከል አንዱ በተለይም ጃዋርን አስመልክቶ የተፈጠረውን ቅሬታ “ትናንት መጥቶ የለፋንበትን፣ ዋጋ የከፈልንበትን፣ የታስርንበትን ድርጅታችን ውስጥ የበላይ ተደርጎ ገፋን። ብር አፍስሶ በጥሞናና በሰከነ እሳቤ ከሌሎች ጋር ተናቦና በሌሎች ተከብሮ ሲንቀሳቀስ የነበረውን ድርጅታችንን አጎደፈው፣ በዘረኝነት እንዲፈረጅ ምክንያት ሆነ። አሁንም የፓርቲው አመራር ሆኖ ከህገ ደንቡ አፈንግጦ እንዳሻው ዓመጽ ሲያደራጅና ሲቀሰቅስ የሚገስጸው የለም። አንድ ድርጅት መርህ የጠፋበት ድርጅት ከሆነ የተሻለውን መንገድ መፈለግ የወቅቱ ምላሽ ነው ” ብለዋል።
ከሁለት ሳምንት በፊት ፕሮፌሰር መረራን በፓርቲያቸው ውስጥ ጃዋርን አስመልክቶ ልዩነት መፈጠሩን፣ በጃዋር ሳቢያ ፓርቲያቸው ላይ የህግ ጥያቄ ሊነሳበት እንደሚችል ስጋት የገባቸው መኖሩንና አሁን ላይ በተለይም የህክምና ባለሙያዎችን ታኮ አመጽ እንዲነሳ በከፍተኛ ትጋት እያሰራጭ ያለው የዓመጽ ጥሪ፣ እንዲሁም ተብ መንጃ ካነሱ ኃይላት ጋር በገሃድ የፈጠረው ህዝብረት ፓርቲያቸው እንደሚያውቀው ጠይቀናቸው ነበር።
ፕሮፌሰር መረራ በጃዋር ላይ ከድርጅቱ ውስጥ ተነሳ የተባለውን ቅሬታ እንደማያውቁ፣ እያሰራጨ ነው የተባለውን የሁከት ጥሪ እንዳላዩ ተናግረዋል። ይልቁኑም የሚያዋጣው ለህክምና ባለሙያዎቹ መፍትሄ መስተት እንደሆነ ጠቁመዋል።
በድጋሚ ጃዋር እያራመደ ያለው አቋም የድርጅታቸው አቋም ስለመሆኑ ተጠይቀው “ምን እያከናወነ እንደሆነ ስላላየሁ የምለው የለም” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። ከዝግጅት ክፍሉ ጃዋር የሚያሰራጫቸውን የማነሳሻ ስራዎች በመዘርዘር ለማብራራት ቢሞከርም ፕሮፌሰር መረራ ሳይዩና ሳያነቡ ምንም ሊሉ እንደማይችሉ አስረግጠው ተናግረዋል።
አቶ በቀለ ገርባ አሜሪካ ከገቡ በሁዋላ ከድርጅቱ ራሳቸውን ሲያገሉ ” ማራመድ የሚገባኝን የፖለቲካ አቋም በግሌ አራምዳለሁ” በማለት በይፋ ራሳቸውን ከድርጅቱ መለያታቸውን አድንቀው የሚናገሩ የኦፌኮ ሰዎች፣ ጃዋር መሐመድ የድርጅቱ ተቀዳሚ ሊቀመንበር ሆኖ የድርጅቱን መርህና የሚታወቅባቸውን ህጎች ሲደረማምሳቸው ዝም መባሉን አይቀበሉም። እንዲስተካከል ቢጠይቁም ምላሽ አላገኙም። እንደ እነዚህ ሰዎች እምነት ጃዋር ወደ ድርጅቱ ይዞት የመጣው ገንዘብ መረን ሲወጣ ለማረቅ እንቅፋት ሆኗል። በቀጣዩ የድርጅቱ ጉብኤ እንደማይመረጥ ግምታቸው ሰፊ ቢሆንም እስከዚያው መተበቅ እንደማይችሉ አመልክተዋል። ፕሮፌሰር መረራ ግን ይህ ሁሉ ጉዳይ አግባብ እንዳልሆነ ነው የሚናገሩት።
ከኦፊኮ፣ ከኦነግና የኦሮሞ ነጻ አውጪ ሰራዊት ወደ ብልጽግና የሚደረገው ፍልሰት እንዴት እንደሚሰላ ጥያቄ ያቀረብንላቸው የዜናው ምንጮችና ብልጽግናን የተቀላቀሉ እንዳሉት ኦነግ በከፍተኛ ደረጃ ፍልሰቱ ጎድቶታል።
ኦነግ የነበሩት ጥቂት የሚታወቁ አመራሮች ካልሆኑ በቀር አሁን ላይ ባዶ ቀርቷል እስኪባል ድረስ አመራሮቹ፣ ካድሬዋቹና በዞን ኃላፊዎች ስራ ያልይ አባላቱ ብልጽግናን መቀላቀላቸውን አስታውቀዋል። እነዚህ ወገኖች እንደሚሉት ኦነግ ወደፊት ምርጫ መወዳደር እንኳን ቢፈልግ በቂ አቅም እንደማይኖረው ይናገራሉ።
“የሚገርመው” ያላሉ እነዚህ ወገኖች፣ የሚገርመው ፓርቲው ይህ ሁሉ እየሆነ፣ ፍልሰት እየጨረሰው፣ አባላቱ እየከዱትና ባዶ እየሆነ ከላይ ያሉት አመራሮች ዝም ማለታቸው ነው። ምንም ማድረግ ይገባቸው እንደነበር ለተጠየቁት ” ቢያንስ ከአባሎቻቸው ጋር የፍልሰቱን ምክንያት አንስተው መነጋገርና መፍትሄ መፈለግ ሲገባቸው ተኝተዋል” ሲሉ ይወቅሱዋቸዋል።
ከውጭ አገር ሳይቀር ደጋፊዎቻቸው፣ የቅርብ አጋሮቻቸውና በውጭ አገር ወኪል የነበሩ አገር ቤት እየገቡ ብልጽግናን ሲቀላቀሉ አለመደንገጣቸው ምክንያቱ ባይገባቸውም፣ ከአሁን በሁዋላ ኦነግ ባሉት አመራሮች ያንሰራራል የሚል ዕምነት እንደሌላቸው ነው የሚገልጹት። ኦነግ አሁን ላይ በከፍተኛ ድባቴ ውስጥ እንደሚገኝ፣ በዚሁ ድባቴ ውስጥ ሆኖ አልፎ አልፎ “ቢሮ ተዘጋብኝ፣ አባላቶቼ ተሳደዱብኝ” ከሚለው ትንፋሹ ውጪ የፖለቲካ ክንዱ የላላ መሆኑንንም እነዚሁ የተለዩት አባላቱ ያስረዳሉ። አዲስ አመራር፣ እሳቤና ዘመናዊ አደረጃጀት የሚከተሉ መሪዎች ካልተገኙ ፓርቲው ሊድን እንደማይችልም አስረግተው ይናገራሉ።
” መሰሶ መሆን ሲገባን የአጥር እንጨት ተደረግን” በሚል ኦፌኮን የለቀቁት እንደሚሉት ከኦነግ ቀጥሎ በከፍተኛ ደረጃ ብልጽግናን እየተቀላቀሉ ያሉት የኦሮሞ ነጻ አውጪ ሰራዊት ተዋጊዎችና አመራሮቻቸው ናቸው።
ጃል ሰኚ ሰማኒያ በመቶ የሚሆነውን የሰራዊቱን ክፍል ከነ አመራሩ ይዞ በስምምነት መግባቱን በማንሳት እንዚሁ ክፍሎች እንዳሉት፣ በየቀኑ ከሚገቡት በተጨማሪ አሁን ላይ የኦሮሚያ ጸጥታ ምክትል ኃላፊ ሆኖ የተሾመው ጃል ሰኚ ራሱ ጋር እየተደራደሩ ያሉ የመቸረሻው ዙር ገቢዎች አሉ።
እነዚሁ ታጣቂዎች በቅርቡ ወደ ስምምነት እንደሚደርሱ የገለጹት የመረጃው ሰዎች፣ ጃል ሰኚና አብረውት የነበሩት አመራሮቹ ይዘውት የገቡት ኃይል የጃልመሮን አቅም አመናምኖታል።
ከተለያዩ የኦርሞያ ዞኖችና ወረዳዎች የሚወጡ ዜናዎች እንደሚያስረዱት አሁን ላይ በፊት የኦሮሞ ነጻ አውጪ በቋሚነት የሚቆጣጥራቸው የነበሩ አካባቢዎች ነጻ ሆነዋል። በኬንያ ኢትዮጵያ ድንበር ሳይቀር የነበረው ካምፕና ምሽግ ከኬንያ ጋር በተደረገ የጋራ ኦፕሬሽን መደምሰሱን፣ የተማረኩ አባላት እንዳሉ ጠቅሰው የኬንያ ሚዲያዎች መዘገባቸው አይዘነጋም።