” እናቴ አታልቅሺ አልሞትኩም” የሚለው ጃዋር ስም ቀይሮ የገደለው ወጣት ነው። በራሱ አገላለትጽ “ዛሬ እኔም አለው ሞት ተፈርዶብኝ በሰው እጅ” ሲል ጃዋር ሞት እንደፈረበት ያስታውቃል። መለስ ይልና የሞትን ጥላ እያየ “ምን እላለሁ ደካማውን ረዳህኝ፤ እኔ በህይወት አለሁ። ነጌ መልካም ይሆናል” በማለት ለነብሱ መልካም ይመኛል።
“በሕይወት አለሁ አልሞትኩም። አንጆኒዮ ጮሎ ወይንም አብዮት ጮሎ እባላለሁ። በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የእኔን ፎቶ እየተጠቀሙበት ነው። (ጃዋር ግን ሆነ ብሎ ነው) እባካችሁ ያልተረጋገጠ ዜና በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በማሰራጨት እንዳትሳሳቱ፤ ሌሎችንም አታሳስቱ። ከተደበኩበት ወደ አደባባይ ወጣሁ” የሚለው አብዮት ጃዋር ለዓላማው ሲል የሰጠው ስም በረከት ሀማ የተሳሳተ መሆኑን ያስገነዝባል።
ምንም ሳይቀነስና ሳይጨመርበት ጃዋር ለዓመጽ ይረዳው ዘነዳ ስም ቀይሮ የገደለው ወጣት ምስክርነት የተወሰደው Anjoneyo Cholo (Abiyot Cholo) ከሚለው የግል ኦፌሳል ገጹ ላይ ነው። ስሙን በመጫን የግል ፌስቡክ ገጹ በማየት ማመሳከር የበለጠ መረጃ ማግኘት ይቻላል። በርካቶችን ያሳዘነው ይህ እከተለጠፈ ድረስ ጃዋር በሃሰተኛ ስም ስለገደለው ወጣት ማስተባበያም ሆነ ይቅርታ አልጠየቀም። የልጃቸውን ሞት ስም ቀይሮ በፎቶ ያረዳቸው እናት “ልጄ ሞተ” እያሉ ከዘመድ አዝማድና ቤተሰብ ጋር አንብተዋል። ይህ ሃዘንና ድንጋጤ ከዚህ ቀደም ” ሂሳቡን እኔ አወራርዳለሁ” በማለት የድሃ ልጆችን ሲማግድ ለነበረው ጃዋር ሙዚቃው ነው።
“… ፖሊሶች ጭምር አሰቃቂ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ወዳጅ ዘመድ የጠፋባችሁ ካላቹ ዘውዲቱ ቼክ አድርጉ። የታሰሩት ወደ አንድ አዳራሽ ሰብስበዋቸዋል። ካልለቀቋቸው ወዴት እንደሚወስዷቸው ተከታትለን እናሳውቃለን” በሚል ዜና ሕዝብ ያተራመሰው ጃዋር መሐመድ ሲዳማ ቡናና ወላይታ ዲቻ ለኢትዮጵያ ዋንጫ ፍጻሜ በዝግ ሜዳ እንዲጫወቱ መወሰኑን ሰርግና ምላሽ ሆኖለት እንደነበር ተግባሩ ያስታውቃል። አስገራሚው ጉዳይ ተብሎ በበርካቶች የተገለጸው ግን ጃዋር ይህን ሁሉ ሲያደርግ የመንግስት የመረጃ ሰዎች ምን እየሰሩ ነበር የሚለው ነው።
ጃዋር በዛ አላቆመመ “ዛሬ በእግር ኳስ ደጋፊዎች ላይ በተተኮሰ ጥይት የተገደለው ወጣት ይሄ ነው። በረከት ሀማ ይባላል” በሚል ባሉት በማህበራዊ ገጾቹ አስተጋባ። ጃዋር በተከታታይ በሚለጥፋቸው ልጥፎች ስር ውርጅብኝ ቢወርድበትም አላቆመም። መጨረሻ ላይ ፎቶው ተለጥፎ በጃዋር ሞት የተፈረደበት በረከት ሀማ ” ጃዋር አልሞትኩም ስሜም ሌላ ነው” ሲል ለሟርቱ ምላሽ ሰጠ።
በዚህ አልበቃም ” ሂዱና አስከሬናችሁንና ቁስለኞቻችሁን ዘውዲቱ ሆስፒታል ፈልጉ” የተባሉት የክለቡ አመራሮች፣ “አንድም በጥይት የተመታም ሆነ የሞተ ሰው የለም። ዘውዲቱ ሄደን አጣራን …” ብለው ለቲክቫህ አዋሳ ዘጋቢ አስታወቁ። አሁን ድረስ ጃዋር ” ልብ ሰባሪ” ብሎ ስለገደለው ወጣት ማስተባበያም አልጻፈውም። ቤተሰቦቹን፣ ወዳጆቹንና ራሱን ስም ቀይሮ የገደለውን ወጣት ይቅርታ አልጠየቀም።
“ዛሬ ጠዋት መንግስት በእግር ኳስ ደጋፊዎች ላይ ባደረሰው ጥቃት የተጎዱ ሰዎች ዘውዲቱ ሆስፒታል ነው የተወሰዱት። በህይወት ያለፉትን ማንነት እያጣራን ቤተሰብ ከተረዳ በኋላ እናሳውቃለን” በማለት ረብሻ ናፍቆት ሲቀሰቅስ የዋለው የኦፌኮ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር ጃዋር መሐመድ” ነገሩን የብሄርም ቅርጽ ለማስያዝ “በነገራችን ላይ የተጎዱት የወላይታ ዲቻ ደጋፊዎች ብቻ አይደሉም። የሲዳማ ቡና እንዲሆም ምንም ውስጥ ያልነበሩ ተራ መንገደኞችም (አንድ ከቱሉ ቦሎ ሲጓዝ የነበረ ኦሮሞ ገበሬን ጨምሮ) የጥቃቱ ሰላባ ነበሩ” ብሏል።
“….የፍጻሜውን ጨዋታ ለመመልከት የተሰባሰቡት የክለቦቹ ደጋፊዎች ወደ ስታዲየም እንዳይገቡ የታገዱት መንግስት ምን አልባትም ወጣቶቹ መሰባሰባቸው ወደ ተቃውሞ ሊለውጥ ይችላል በሚል ስጋት ነው” ሲል ለጻፈው “ሲያምርህ ይቅር” የሚል ምላሽ የሰጡ “እባክህን ከስፖርቱ ላይ እንኳን ገለል በልልን” ሲሉ ጠይቀውታል። የጃዋር ልጥፎች ላይ ባልተለመደ መልኩ የከረሩ ውግዘቶች መስተናገድ ከጀመረ ሰነባብቷል ያንብቡዋቸው።
“Football fans are protesting after the government blocked them from entering the stadium to watch today’s match, fearing the gathering could turn into an anti-regime rally. Several dozen of them have been arrested“
“በመዲናዋ የእግር ኳስ ደጋፊዎች አፈሳ እየተካሄደ ነው። ከከተማ ውጪ እየገቡ ባሉ ባሶችን እየፈተሹ ደጋፊዎችን እያስወረዱ ወደ እስርቤት እየወሰዱ ነው። እንዲጠነቀቁ መልክት አስተላልፍልኝ” ሲል ጃዋር ቅድመ ማስጠንቀቂያም ሲሰጥ ነበር። ይህ ሁሉ ካለፈ በሁዋላ ክለቡ የተባለው ሁሉ ውሸት መሆኑን አስታውቋል። ከስር ያንብቡ።
ለምን ጨዋታው በዝግ ሜዳ እንዲሆን ተወሰነ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ሲሳይ ጂራ እንዳሉት ከመንግስት መመሪያ በተላለፈላቸው መሰረት የፍጻሜው ጨዋታ በዝግ እንዲደረግ ተወስኗል። በደመቀ ስነስርዓት ውድድሩ ቢጠናቀቅ ከማንም በላይ ፌዴሬሽኑ ደስተኛ እንደሚሆን ገልጸው ” መንግስት ለደሕንነት” በሚል የሰጠውን መመሪያ ወደ ጎን መተው እንደማይቻል አመልክተዋል። ግልጽ ያልተደረገው የደህንነት ችግር ምን ይሆን?

ዝግጅት ክፋላችን ለማጣራት ሞክሮ ጨዋታው ከመካሄዱ ቀናት በፊት ፖሊስ ህጋዊና የተፈቀደ ፍተሻ እንደሚያከናውን ይፋ አድርጎ እንደነበር በማስታወስ አስተያየታቸውን የሰጡን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ” ለጊዜው መንግስት ይፋ የማያደርገው ከፍተኛ የጸትታ ስራ ተሰርቷል። ኦፕሬሽኑ አላለቀም። ሲጠናቀቅና ጊዜው ሲደርስ ምን ተፈጥሮ እንደነበር ይፋ ይሆናል የሚል ዕምነት አለኝ” ብለዋል።
የሽብር ተግባር ለመፈጸም የተደራጁ ኃይሎች ሕዝብ በሚሰበስብባቸው አካባቢዎች አደጋ መጣል ዋና ዓላማቸው እንደሆነ ያስታወሱት አስተያየት ሰጪ መንግስት፣ ከወራት በፊት በተጠናቀቀው የአፍሪካ አንድነት ስብሰባ ወቅት የሳፋሪ ሲም ካርዶች ለአራት ቀናት የተዘጉበትን ምክንያት መለስ ብሎ መቃኘት አስፈላጊ እንደሚሆን አመልክተዋል። ደህንነት መረጃ ሲኖረው ለህዝብ ደህንነት ሲል ተለዋዋጭ፣ ጊዜያዊ፣ ቋሚና ስፍራን የለየ ድንገተኛ መመሪያ ወይም ክልከላ ማደረጉ አስገራሚ እንዳልሆነ አመልክተዋል።
እንደሚታወቀው ጃዋር በምናቡ የገደለውና ያቆሰላቸው የወላይታ ዲቻ ደጋፊዎች ናቸው ማህበሩ ደግሞ ” የተገደለ የወላይታ ዲቻ ደጋፊ የለም ” ሲል ለቲክቫህ አዋሳ ሪፖርተሩ በዝርዝር አስረድቷል።
ትላንት በአዲስ አበባ ከተማ በዝግ ስታዲየም ከተካሄደው የሲዳማ ቡና እና ወላይታ ዲቻ ጨዋታ ጋር በተያያዘ በፀጥታ ኃይሎች በጥይት ተመተው የተገደሉ ሰዎች ስለመኖራቸው ፤ ቆስለው ዘውዲቱ ሆስፒታል የተኙም እንዳሉ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስፋት ሲሰራጭ ነበር ይላል ዘገባው። አክሎም “በጥይት ተመተው ተገደሉ፣ ቆስለው ዘውዲቱ ሆስፒታል ተኝተዋል ” የተባሉት የወላይታ ዲቻ ደጋፊዎች እንደነበሩ ያስታውሳል። ይህንኑ መነሻ በማድረግ ቲክቫህ የወላይታ ዲቻ ስፖርት ክለብን እወነቱን ንገሩን ሲል ጠይቋል።
የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ አሰፋ ኦሲሶ ” እኛ አንድም የሞተብን ደጋፊ የለም ” በማለት ነው ምላሻቸውን የጀመሩት። ” ትላንት ማታ የደጋፊ ማኅበር አመራሮች ወደ ሆስፒታል ጭምር ተሰማርተው አጠቃላይ የተባሉትን ነገሮች አጣርተዋል ” ሲሉ ስራ አስኪያጁ በጃዋር ጋባዥነት ያከናወኑትን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ቴሊቪዥን፣ የመንግስት ኮሙኒኬሽን፣ የመንግስት ሚዲያዎች፣ ፖሊስ ወዘተ በዚህ ደረጃ “ሕዝብ አለቀ” በሚል የፈጠራ ዜና አገር ለማመስ ሁሉንም ዓይነት ድንጋይ ለሚፈነቅሉ አጭር መግለጫ በመስጠት እውነታውን ማስታወቅ ሲቻል ዝምታን መምረጣቸው የተደጋገመ ስህተታቸው መሆኑን በርካቶች ይናገራሉ። ውድመት ከደረሰ በሁዋላ ለማስተካከል የሚንፈራገጠው የመንግስት የህዝብ ግንኙነትና ሚዲያዎች ከቲክቫህ በምን አንሰው ነው በፍጥነት አጣርተው ትክክለኛ መረጃ የማይሰጡት? ይህ ቢባል ቢባል ሰሚ ያጣ ችግር እንደሆነ በርካቶች ይስማማሉ። ዘወትር አጀንዳ ተቀባይ ሆነው የሚቀጥሉበት አግባብንም እነዚሁ ወገኖች በስጋት ነው የሚያዩት።
” ለምሳሌ ዘውዲቱ ሆስፒታል ሰው ተመቶ ተኝቷል ብለዋል ሌሎችም ነገሮች ተብለዋል። ሰው ሞቷልም ተብሏል። ግን እኛ እንዳጣራነው አንድም የሞተ ሰው የለም። ሚዲያ ላይ ሲዘዋወር የነበረው ውሸት ነ። ዘውዲቱ ሆስፒታልም ሄዶ የተኛ ሰው የለም። በጥይት የተመታ ሰው የለም “በማለት ስራ አስኪያኩ አስታውቀዋል።
አቶ አሰፋ ኦሲሶ ” የሞተ ሰው ሆነ በጥይት ተመቶ የተኛ ሰው እንደሌለ የደጋፊ ማኅበር አመራሮቹ አረጋግጠዋል ይህንም ሪፖርት ልከውልኛል ፤ በየቦታው የታሰሩ ነበሩ ትላንት አስፈትተዋል ” ሲሉ የሚያውቁትን እውነት መስክረዋል።
የወላይታ ዲቻ ደጋፊዎች ማኅበርም በተመሳሳይ ” በፀጥታ ሃይሎች የተገደለ የወላይታ ዲቻ ደጋፊ የለም ” ብሏል። ” እወነቱ ይህ ከሆነ ጃዋር ከየት አመጣውና የቆሰሉና የተገደሉትን ዘውዲቱ ሂዱና ፈልጉ፣ ቤተሰብ ከተረዳ በሁዋላ ይፋ እንዳደርጋለን አለ? እስር ቤት እያለ የምታክመው የነበረችውና “ይፈታ፣ የግል ሆስፒታል ይተኛ፣ ይፈታ” ወዘተ ስትል የነበረችው አዲሱ ሚስቱ ዶክተር ዘውዲቱ ትሰራ ይሆን ያሰኛል” በሚል በማህበራዊ ሚዲያ ያላገጡበት አሉ።
የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ታደለ ሜጋ ለቲክቫህእንደገለፁት፣ ደጋፊው ተጉዞ አዲስ አበባ ከደረሰና ወደ እየተጓዘም ባለበት በድንገተኛ ውሳኔ ጨዋታው በዝግ ስታዲየም እንዲካሄድ በመወሰኑ እንዲሁም የጨዋታውንም ወጤት ተከትሎ ደጋፊዎች ስሜታቸውን በተለያየ መንገድ ሲገልፁ ነበር ብለዋል።
” ነገር ግን በፀጥታ አካላት በርካታ ደጋፊዎች ተገደሉ እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ውሸት ነው ፤ በፀጥታ አካል የተገደለ የወላይታ ዲቻ ደጋፊ የለም ” ሲሉ አረጋግጠዋል። ከነበረው ሁኔታ ጋር በተያያዘ ግን በአዲስ አበባ የተለያዩ እስር ቤቶች ደጋፊዎች ስለመታሰራቸው ጠቁመዋል።
” ፖሊስ የአንዳንድ ደጋፊዎችን ስሜት ለማብረድና ለማረጋጋት ወደ እስር ቤት ወስዷል ” ያሉት ፕሬዚዳንቱ ” ማምሻውን አብዛኞቹን በመነጋገር አስፈትተናል ፤ የተቀሩትንም ዛሬ እያስፈታን ነው ” ብለዋል።
በትናንትናው ዕለት በዝግ የተካሄደውን የፍጻሜ ጨዋታ ሲዳማ ቡና ወላይታ ዲቻን 2 ለ 1 በማሸነፍ ሻምፒዮን ሆኗል።