እንደተጀመረ የተሰማው ዜና ጉዳዮ በደንብ የታሰበበት መሆኑን ነው። እስራኤል የወሰደችው አስገራሚ የተባለው ጥቃት የተጠና ለመሆኑ ኢራን ቁልፍ ስድስት ሰዎቿንና ሙሉ በሙሉም ባይሆን የኒኩሌር ማበልጸጊያ ማዕከሎቿ ላይ ጣቅት መድረሱ ምስክር ነው። ኢራንም የአጻፋ እርምጃ ብትወስድም የእስራኤልን ያህል ጉዳት አላደረሰችም።
የእስራኤልን መከላከያ ጠቅሶ “ቴህራን ከአሁን በኋላ የመከላከል አቅም የላትም፣ የኢራን ዋና ከተማ ለእስራኤል ጥቃት ተጋልጧል” ሲል የስራኤል የጦር ጀቶች እንዳሻቸው እንደሚመላለሱ አለምልክቷል። IDF: ‘Tehran is no longer immune; the Iranian capital is exposed to Israeli strikes”
ከጥቃቱ በሁዋላ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ “…ምርጡንና እጅግ የረቀቀ አውዳሚ የጦር መሳሪያ አምራች ሃገር አሜሪካ መሆኗን ለማስታወስ እወዳለሁ። በአሜሪካ እጅ የሚገኙ ምርጥ የጦር መሳሪያዎች በእስራኤል እጅ ውስጥ ይገኛሉ፤ እንዴትና መቼ መጠቀም እንዳለባቸውም ያውቃሉ። የከፋው ጥቃት ገና ከፊት አለ። በድርድር የጋራ መፍትሄ ላይ ካልደረሰን የከፋ ውድመት እንደሚደርስ ያስገነዘብናቸው ሁኔታውን ተገንዝበው የድርድርን አማራጭ የሰበኩ ኢራናውያን አሁን የሉም፤ በእስራኤል እርምጃ ተገድለዋል። አሁንም የከፋ መተላለቅ ሳይደርስ ኢራን ለመደራደር ዝግጁ መሆን አለባት። አሊያ ግን ኢራን ሁሉንም ታጣላች፤ የከፋ ውድመትን በፈቃዷ ታስተናግዳለች። ሳይመሽ በፊት ወደ ድርድር ተመለሱ…” ሲሉ በትሩዝ ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።
ኢራን እስራኤል በፈጸመችው ጥቃት ስድስት የኒውክሌር ሳይንቲስቶች መሞታቸውን አስታወቀች።
ኢራን “እስራኤል ላይ የሲኦል ደጆች ሁሉ ይከፈታሉ” በማለት ከጥቃቱ በሁዋላ የከፋ፣ እስራኤል ምነው ባላደረኩት ብላ እስክትጸጸት ድረስ አጻፋውን እንደምትመልስ አስታውቃ ነበር። በዚሁ መሰረት እስራኤል ላይ ቦለስቲክ ሚሳይል አዝንባለች። የድሮን ጥቃት ሰንዝራለች። ይህ የሆነው ከዛቻው በሁዋላ ነበር
እስራኤል የምትፀፀትበትን የአጸፋ ምላሽ እናደርጋለን ሲል የኢራን አብዮታዊ ዘብ ምን ብሎ ነበር?
ኢራን በእስራኤል ግዛት ላይ የምትሰነዝረው የአጸፋ ምላሽ ከባድ ሊሆን እንደሚችል የኢራን አብዮታዊ ዘብ አስጠንቅቋል። ኢራን የደረሰባትን ጥቃት ተከትሎ የሀገሪቱ መሪ አያቶላ ሰይድ አሊ ካሚኒ ያስተላለፉትን መልዕክት ተከትሎ የኢራን አብዮታዊ ዘብ ማስጠንቀቂያውን አውጥቷል። አያቶላ በመልዕክታቸው ኢራን የአጸፋ ምላሿ ከባድ እና “እስራኤልን የሚያጸጽት” ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል።
ይህን ንግግር ተከትሎ የኢራን አብዮታዊ ዘብ ለእስራኤል “አስከፊ” ምላሽ በመስጠት በፈጸመችው ጥቃት እንድትጸጸት ያደርጋል ማለቱን የኢራን ዜና አገልግሎት ዘግቧል። የኢራን አብዮታዊ ዘብ ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጀነራል አቦልፋዝል ሸካርቺ ኢራን “ከባድ” አጸፋዊ እርምጃ እንደምትወስድ ተናግረዋል።
ብርጋዴር ጀነራሉ እስራኤል ሌሊቱን የፈጸመችው ጥቃት በአሜሪካ ድጋፍ መሆኑን በመግለጽ ሁሉም “የእጃቸውን ያገኛሉ” ብለዋል። የእስራኤል ጦር በኢራን የተለያዩ አካባቢዎች የኒውክሌር ኢላማዎችን ጨምሮ ከአስር በላይ የሚሆኑ ወታደራዊ ኢላማዎችን መምታቱን ይፋ አድርጏል።
እስራኤል በኢራን የፈፀመችውን የአየር ጥቃት ተከትሎ፣ ኢራን ከ100 በላይ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን (ድሮኖቾችን) ወደ እስራኤል ማስወንጨፏን የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት አስታውቋል። በወቅቱ ኝ ጉዳቱ አልተዘረዘረም።
የኢራን ታስኒም የዜና ወኪል እንደዘገበው በእስራኤል ጥቃት ስድስት የኢራን የኒውክሌር ሳይንቲስቶች መገደላቸውን ዘግቧል።

ኤጀንሲው በኤክስ ላይ ባወጣው ዘገባ በጥቃቱ ስድስት ሳይንቲስቶች – አብዱልሃሚድ ሚኑችህር፣ አህመድሬዛ ዞልፋጋሪ፣ ሰይድ አሚርሆሴይን ፋቂ፣ ሞትላቢዛዴህ፣ መሀመድ መህዲ ቴህራንቺ እና ፌሬይዶን አባሲ ተገድለዋል ብሏል።
ሆሴይን ሳላሚ በዚህ ጥቃት ከተገደሉት ከፍተኛ አመራሮች መካከል አንዱ ናቸው። የአገሪቱ የአቶሚክ ኢነርጂ ድርጅት ኃላፊ የነበሩት የኒውክሌር ሳይንቲስቱ ፍሬይዱን አባሲ መገደላቸውን የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ፍሬይዱን አባሲ ለኢራን የኒውክሌር ማበልጸግ የአንበሳውን ድርሻ እንደተጫወቱ ይነገርላቸዋል። ሳይንቲስቱ ከዚህ ቀደም በአውሮፓውያኑ 2010 በቴህራን ጎዳና ላይ ከተቃጣባቸው የግድያ ሙከራ ተርፈው ነበር።
ሌላኛው በዚህ ጥቃት የተገደሉት የኒውክሌር ሳይንቲስት በቴህራን የሚገኘው የእስላሚክ አዛድ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት መህዲ ቴህራንቺ ናቸው። ኢራን አሜሪካ የእስራኤልን ጥቃት ደግፋለች ስትል የከሰሰች ሲሆን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በበኩላቸው አገራቸው እንዳልተሳተፈች ተናግረዋል ሲል አልጀዚራ ዘግቧል።
ኢራን የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት በአስቸኳይ ስብሰባ እንዲያካሂድ ጠየቀች
ኢራን በእስራኤል ከተፈጸመባት የአየር ጥቃት በኋላ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ እንዲያካሂድ ጥሪ አቅርባለች። አናዶሉ አይ አር ኤን ኤ የተባለውን የዜና ወኪል ጠቅሶ እንደዘገበው ኢራን በእስራኤል ላይ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድ የሚጠይቅ ደብዳቤ ለፀጥታው ምክር ቤት ልካለች፡፡ ቻይናና ቱርክ የስራኤልን ጥቃት ሲያወግዙ አሜሪካ መቃወሟ ተሰምቷል።
ኢራን በደብዳቤው የእስራኤልን ጥቃት አውግዛ፤ “ግልጽ የሆነ ጥቃት” ተፈጽሞብኛል ብላለች። የፀጥታው ምክር ቤት ጉዳዩን ተመልክቶ ድርጊቱ የዓለም አቀፍ ሕግ ጥሰት መሆኑን በመገንዘብ የራሱን ውሳኔ እንዲያሳልፍም ጠይቃለች። ኝ ይህ ነው የሚባል ነገር አልተሰማም። ያው መግለጫና የቃላት ተቃውሞ ነው።
የእስራኤል ድርጊት ለዓለም ሰላም እና ፀጥታ ጠንቅ ነው ያለችው ኢራን፤ ጉዳዩን በትኩረት በመመልከት መፍታት እንደሚያስፈልግ አስገንዝባለች። አሁን ላይ የሚወጡ መረጃዎች የእስራኤል አየር ሃይል በኢራን አየር ክልል ያለ ስጋት እየበረረ የኑክሌያር ተቋማትን፣ ወታደራዊ ይዞታዎችንና የሚሳኤል ማምረቻ ፋብሪካዎችን እያወደመ ነው።
የኢራን ጦር ተጨማሪ ሁለት ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦቹ በእስራኤል ጥቃት መገደላቸውን አስታወቀ። ሟቾቹ የጠቅላይ ኢታማዦር የስለላ ምክትል ኃላፊ ጎላምሬዛ መህራቢ እና የአሠራር ክፍል ምክትል ኃላፊ መህዲ ራባኒ ናቸው።
ጥቃቱ ይቀጥላል
እስራኤል በኢራን ላይ የጀመረችው ጥቃት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል፣ ይህም ለሁለት ተከታታይ ሣምንታት እንደ ኢሆን አመልክታለች። የተባበሩት መንግስታት ዓለም አቀፍ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ሃላፊ ራፋኤል ግሮሲ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢራንን ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን በማስታወስ በኢስፋሃነሰ የሚገኘውና በእስራኤል ጥቃት የደረሰበት የኑክሌያር ጣቢያ አንዳች ጉዳት እንዳልደረሰበት ከኢራን ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ማረጋገጫ ማግኘታቸውን ይፋ አድርገዋል። ለዚህ ይመስላል እስራኤል የኢራንን የአየር ላይ መመከቻዎች አውድም ዱላውን አተናክራ ቀጥላለች።
ኢራን በእስራኤል ጥቃት የተገደሉባትን ወታደራዊ መሪዎች መተካቷን ቀጥላለች

የኢራን መሪ አያቶላ ሰይድ አሊ ካሚኒ አዲስ የተሾሙትን የኤሮስፔስ ሃይል አዛዥን ስም ይፋ አድርገዋል።
ጀነራል ሰይድ ማጂድ ሙሳቪን የእስልምና አብዮት ጠባቂዎች ኮርፕስ (IRGC) የኤሮስፔስ ሃይል አዛዥ ሆነው መሾማቸውን የኢራን ዜና አገልግሎት ዘግቧል። በትላንትናው እለት ኢራን በእስራኤል ጥቃት የተገደሉ ከፍተኛ የጦር መሪዎችን እና ባለስልጣናትን የሚተኩ ሹመቶችን መስጠቷን መዘገባችን ይታወሳል።
በዚህም ሜጀር ጄነራል ሰይድ አብዱረሂም ሙሳቪ የኢራን ጦር ኃይል ኤታማዦር ሹሞች ሊቀመንበር እንዲሁም ሜጀር ጄነራል አሊ ሻዴማኒ የኻታም አል-አንቢያ ዋና መሥሪያ ቤት አዛዥ ሲሆኑ፣ ሜጀር ጄነራል መሀመድ ፓክፑር የኢራን አብዮታዊ ዘብ ዋና አዛዥ ሆነው ተሹመዋል።
ኢራን ቀይ መስመሩን አልፋለች – የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር
ኢራን ቀይ መስመር አልፋለች ሲሉ የእስራኤሉ መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ ተናገሩ። እስራኤል ሐሙስ ለአርብ አጥቢያ ኢራን ላይ ባደረሰችው ጥቃት የጀመረው የሁለቱ ሀገራት ግጭት ከዚህ የበለጠ እንዳይባባስም ከፍተኛ ስጋትን ፈጥሯል።
የኢራንን የተለያዩ ቦታዎች ካጠቃው የእስራኤል ወታደራዊ እርምጃ በኋላ ኢራን ትንናት ማምሻውን በጀመረችው ጥቃት እስካሁን 150 የሚሆኑ ባለስቲክ ሚሳይሎችን ወደ እስራኤል ትኩሳለች። ሚሳኤሎቹ በእስራኤል የአየር መቃወሚያ ስረዓት ቢመክኑም የተወሰኑት ግን መከላከያውን አልፈው በዋና ከተማዋ ቴላቪቭ መሃል ላይ ሲያርፉ ተስተውለዋል።
በተለያዩ የቴልአቪቭ ቦታዎች ላይ በወደቁት የኢራን ሚሳኤሎች ምክንያት የተነሳውን እሳት ለማጥፋት ምሽቱን የከተማዋ እሳት አደጋ ሰራተኞች መሰማራታቸው ታውቋል። በዚህ የኢራን የሚሳኤሎች ጥቃት እስካሁን 40 እስራኤላውያን መጎዳታቸውንና የሦስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ሲኤንኤን ዘግቧል ።
ከዚህ ጥቃት በኋላ መግለጫ የሰጡት የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ኢዝራኤል ካትዝ ኢራን አሁን ቀይ መስመር አልፋለች፤ ለዚህም የኢራን መንግስት ዋጋ ይከፍላል ብለዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሴት የጦር ጄት አብራሪ በምርኮ እንዳልተያዘበት የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር ገለጿል።
በኢራንና እስራኤል ግጭት የእስራኤል ጦር ኢራንን እንዲደበድቡ፤ ከላካቸው የጦር አውሮፕላኖች መሀል ሁለቱን መትቶ መጣሉን የኢራን ሚዲያዎች ዘግበዋል።
ተስኒም የተባለው ከኢራን መንግስት ጋር ግንኙነት ያለው የዜና ምንጭ፤ በፓራሹት የሚወርድ የጦር ጄት አብራሪ የሚታይበት ተንቀሳቃሽ ምስል ጋር አያይዞ ዜና አሰራጭቷል።
ከተመቱት ሁለት የእስራኤል የጦር ጄቶች መካከል የአንዱ አብራሪ የሆነችው ፓይለት በፓራሹት መውረዷን እና በኢራን ሠራዊት ተማርካ በቁጥጥር ስር እንደምትገኝ ዘግቧል። የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ ዘገባው ሀሰት ነው የተማረከብን ፓይለት የለም ሲል ማስተባበሉን የዘገበው ቢቢሲ ነው።
ዜናው የተሰባሰበው ከተለያዩ መረጃ አውታሮችና ከአገር ውስጥ መገናኛዎች ነው።