በእስር ላይ ያሉትና በጦርነቱ ወቅት ጃዋርን ብቻቸውን መክተው የያዙት አቶ ታዬ ደንደአ አዲስ መነጋገሪያ ሆነዋል። ከስልጣን ከተነሱ በሁዋላ እልህ ውስጥ ገብተው ሁሉንም ጉዳይ፣ ራሳቸው የሰሩትንም በመቃወም የተጠመዱት አቶ ታዬ አዲስ ቃለ ምልልሳቸው ላይ አስገራሚ መረጃ አካፍለዋል። የሰጡት ቃለ ምልልስ አዲሱ የሻዕቢያ ፕሮፓጋንዳ አካል ቢሆንም በዚህ ልክ የአገር መለካከያ ላይ የተሰነዘረውን ጥቃት ውሸት ነው በማለት የትህነግን ኃጤያት ያጥባሉ ብሎ የገመተ አልነበረም።
ነብሳቸውን ይማረውና አቶ ሴኮ ቱሬ፣ ሌተናል ጄነራል ጻድቃን እንዲሁም በግፍ የተከዱት የመከላከያ አባላት በአደባባይ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የተናገሩትንና የመስከሩልንን ዕውነት ነው አቶ ታዬ ሃሰት እንደሆነ የተናገሩት። ክህደትና ግፍ የፈጸሙት፣ ግፋ የተፈጸማባቸውና የተካዱት አደባባይ የነገሩንን ሃቅ፣ እዛው ከመከላከያ አባላት ጋር ጎጆ የመሰረቱ የትግራይ እህቶችና ቤተሰቦች እንዳ እየተራጩ ይፋ ያደረጉትን የክህደት ድራማ ነው አቶ ታዬ ሃሰት ነው በሚል የፖለቲካ ኩርፊያ ያጣፉት።
ከሃያ ዓመት በላይ በጉድጓድ ውስጥ ሆናችሁ አገራችሁን ስትጠብቁ የነበራችሁ የኢትዮጵያ መከላከያ አባላት፣ ወንድሞቻችሁን የተነጠቃችሁ እናንተ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች፣ ነብሳችሁ ያለፈና አካላችሁ የጎደለ፣ በመቀሌ አየር ኃይል ግቢ ተከማችታችሁ የነበራችሁ እህት መታደሮች፣ በባዶ እግራችሁ እንደ ምርኮኛ እየተተፋባችሁ …. ይህን የታዬ ደንደዓን ክህደት መዝግቡት፤ መንግስትን፣ መሪን፣ ፖለቲካን መጥላት ያለ ነው። ግን በጥላቻ የአገር አለኝታ በሆነው መከላከያ ላይ የተፈጸመ ክህደትን ከባለቤቱ ነጥቆ ለሌላ ለማቀበል መሞከር አሳፋሪም፣ ወራዳ ተግባርም ነው።
ከስር የኤርሚያስ ለገሰ ምልከታ ቀውርቧል።
ኦቦ ታዬ ደንደአ ምን ነካቸው?
የሰማነውን ሁሉ ወደ አደባባይ መውጣት አስቸጋሪ ይሆናል። በተለይም በሕግ ቁጥጥር ስር ያለ ሰውን በተመለከተ መናገር ከሞራልም አንጻር አስቸጋሪ ነው። እስሩ ከፖለቲካ ጋር ተያይዞ የሚነሳ ሰው ላይ ከሆነ ደግሞ ጉዳዩን የበለጠ ውስብስብ ያደርገዋል። እየተናገርኩ ያለሁት ስለ ቀድሞው የብልጽግና አመራር እና የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ የነበረው አቶ ታዬ ደንደአ ነው።
ሰሞኑን አቶ ታዬ ደንደአ በቁጥጥር ሥር ከመዋላቸው በፊት በአንድ ውጭ አገር ከሚገኝ የመንግስት ተቃዋሚ በሆኑ እና የኦሮሞ ብሔርተኞች ባለቤት የሆኑበት አንድ ሚዲያ ላይ የሰጡት ቃለ-መጠይቅ እየቀረበ ነው። ቃለ-መጠይቁ በአፋን ኦሮሞ እና አማርኛ የተሰጠ ሲሆን ፤ የኦሮምኛው ቃለ-መጠይቅ በአራት ተከታታይ ክፍል እንዲቀርብ ተደርጓል። የአማርኛው ክፍል ደግሞ ከቀጣዩ ሰኞ ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት እንደሚተላለፍ የፕሮግራሙ አዘጋጅ ኢተና ሃብቴ (ፒ.ኤች.ዲ.) በማስታወቂያ እንድንጠብቅ ነግሮናል።
ቀደም ብዬ በጠቀስኩት ምክንያትም ሆነ ለጊዜው ከመናገር በተቆጠብኩበት ከባድ ምክንያት አስተያየት ላለመስጠት ተቆጥቤ ነበር። ነገር ግን በአንድ በኩል የአቶ ታዬ ቃለ ምልልስ ከዚህ በኋላ በአደባባይ የተሰጣ ‘ሕዝባዊ እውነት’ መፍጠሪያ ሆኗል። በሌላ በኩል ታዬ የተናገረውን ተመርኩዞ አስተያየቶች መሰጠታቸው ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ለምሳሌ ያህል በአብዛኛው አስተያየት እየሰጡ ያሉት አቶ ጃዋርን እና ዳንኤል ብርሃኔን የጨመረ በተቃውሞ ጎራ ያሉ የኦሮሞ እና አማራ ብሔርተኞችን ለመመልከት በመቻሌ ለጊዜው የሞራል ጥያቄዬን አንስቻለሁ። እርግጥ ነው በተቃወሞ ጎራ ያሉት የአማራ፣ የኢትዮጵያ ብሔርተኞች እና የሻዕቢያ አሮጌ ድመቶች አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል። ለምን ይሆን? የሆነው ሆኖ አቶ ታዬ ደንደአ ከሰጡት ቃለ መጠይቅ ውስጥ የሚከተሉትን አራትት ጉዳዮች ላይ ላተኩር። የተናገረውን ብቻ።
፩. አቶ ታዬ ደንደአ በዚህ ቃለ መጠይቁ ላይ የሚከተለውን ብሏል። “ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከ1,500 በላይ የብልጽግና አመራሮች በተሰበሰብንበት የትግራይን ጦርነት የጀመርኩት እኔ ነኝ ብሎናል” ይለናል።
በተቃወሞ ጎራ ያላችሁ የአማራ፣ የኢትዮጵያ ብሔርተኞች እና የሻዕቢያ አሮጌ ድመቶች በዚህ የኦቦ ታዬ መረጃ ላይ ምን አስተያየት አላችሁ?
፪. በማስከተልም ታዬ ደንደአ የራሱን መረጃ እና እምነት በተመለከተ ”የሰሜን እዝ በተኛበት መብረቃዊ ጥቃት ደርሶበታል የሚባለውም ውሸት ነው” ብሏል።በተቃወሞ ጎራ ያላችሁ የአማራ፣ የኢትዮጵያ ብሔርተኞች እና የሻዕቢያ አሮጌ ድመቶች ምን አስተያየት አላችሁ?…በእኔ በኩል ደግሞ “ኦቦ ታዬ ደንደአ የሴኮ ቱሬን ምስክርነት በህይወት የሌሉ አድርገህ ብትወስደው እንኳን እንዴት የጋዜጠኛ ያየሰውን መጽሐፍ<ፖለቲኮ-ኦፕሬሽን> ማንበብ ተሳነህ?” ብዬ መጠየቅ እፈልጋለሁ።
፫. ኦቦ ታዬ ደንደአ በዚሁ ቃለ መጠይቁ ላይ” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የትግራይ ኃይሎች ወደ አማራ ክልል ዘልቀው እንዲገቡ ያደረግነው አቅም አንሶን ሳይሆን ሆን ብለን የፋኖ ኃይሎች ላይ እርምጃ እንዲወስዱባቸው ብለን ነው ብለውናል” ብሏል። እዚህ ላይ እንኳን እጄን በአፍ ከመጫን ውጭ የምጠይቀው የለኝም።
፬. በአራተኛ ደረጃ ኦቦ ታዬ የነገሩን “ጠቅላይ ሚኒስትሩ እየሰረቃችሁ እና እየዘረፋችሁ ለልጆቻችሁ የሚሆን ጥሪት አካብቱ ብለውናል” ብሏል። የእኔ ጥያቄ ይሄ የጠሚሩ ምክር አቶ ታዬ 2ሚሊዮን ብር የያዘ ቦርሳዬ ተሰረቀ ካሉ በኃላ ነው ወይንስ በፊት?
በኤርሚያ ስለገሰ