ኢትዮጵያ ሰፊ፣ ዘመናዊ፣ ቴክኖሎጂ የሚጠቀም፣ በአብዛኛው ተተኳሽና ድሮን ማምረት የቻለ የመከላከያ አቅም መገንበቷን የዓለም ዓቀፍ ሚዲያዎችና የአገራትን መከላከያ አቅም በመዘርዘር ደረጃ የሚያስወጡ ተቋማት በተደጋጋሚ ይገልጻሉ። በተቃራኒው ያፈረሱት ተወግደው በአዲስ እየተገነባ እዚህ የደረሰውን የኢትዮጵያ መከላከያ ዳግም ለማፍረስ ” የአብይ ጦር፣ የብልጽኛ” ጦር በሚል የባዕዳንን ተልዕኮ ይዘው ለውጡን የሚያጣጥሉ አሉ። ለሁሉም የሰጠው መልስ ግን ኢትዮጵያ በየትኛውም መልኩ የሚቃጣባትን ትንኮሳ መመከት የሚችል ኃይል ተገንብቷል የሚል ነበር።
“በአየር፣በየብስም ሆነ በባሕር የሚቃጡ ትንኮሳዎችን የሚመክት ሠራዊት ተገንብቷል” ሲሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ያስታወቁት በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የመከላከያ ሚኒስቴርን የ2017 በጀት ዓመት የ10 ወራት አቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በገመገመበት ወቅት ነው።
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በዚህ ወቅት እንዳሉት፣ የአገር መከላከያ ሠራዊቱ ከኢትዮጵያ አልፎ የምስራቅ አፍሪካ ቀጣናን ሰላምና ደህንነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራነው። ይህም የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም መሰረት ያደረገና ቀጠናዊ ሰላም አስፈላጊ በመሆኑ ነው።
ኢትዮጵያ የባሕር በር እንድታገኝ ከቀጣናው ሀገራት ጋር በትብብር ለመስራትና በጋራ ለመበልጸግ ያላሳለሰ ጥረት እያደረገች እንደምትገኝ አንስተዋል። ኢትዮጵያ የባህር በር ብታገኝ ምናቸም የማይነካና እንቅፋት ለመሆናቸው ምንም ዓየንት አመክንዮ ማቅረብ የማይችሉ ክፍሎች ኢትዮጵያ የባህር በር እንዳታገኝ ሌት ተቀን ተቧድነው እንደሚሰሩ አመልክተዋል።
በአሁኑ ወቅት በየብስም ሆነ በባሕር የሚቃጡ ትንኮሳዎችን የሚመክት እንዲሁም የሀገሪቱን ሉዓላዊነት የሚያስከብር ሠራዊት መገንባቱን ያመለከቱት አዛዡ የሁለኡም ወገኖች ምኞት እንደማይሳካ አስታውቀዋል።
በግምገማዉ የመከላከያ ሰራዊት ቀጠናዊ ተልዕኮን የመወጣት አቅም እና የሰዉ ኃይል አደረጃጀት ምን አይነት ቁመና ላይ እንደሚገኝ ከኮሚቴዉ አባላት ጥያቄ ተነስtኦ ነበር።
ለተነሱ ጣያቄዎች ምላሽ የሰጡት የኢፌዴሪ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ በተለይም በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና የሚስተዋሉ አለመረጋጋቶችን በመፍታት ረገድ፤ የመከላከያ ሠራዊቱ በርካታ ሥራዎችን ሰርቷል ብለዋል።
ኢትዮጵያ የዉስጥ ሰላሟን ለማስጠበቅ ባከናወነችው የሰላም ማስበር ሥራ በርካታ ኃይሎች በሰላማዊ መንገድ ወደ ማኅበረሰቡ መቀላቀላቸውን አንስተዋል።
ሆኖም ግን አሁንም አንዳንድ አካላት የውጭ ኃይሎችን ተልዕኮ ለማስፈፀም እንቅሳቀሴ እንደሚያደርጉና የመከላከያ ሰራዊቱ ያንን ለመመከት እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ የባህር ኃይልን በሚመለከት ለተነሳዉ ጥያቄ፤ የባህር ኃይል ባለቤት ለመሆን ከሰዉ ኃይልም ይሁን ከመሳሪያ አንፃር የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች መሟላታቸዉን ገልጸዋል።
ሠራዊቱ በተለይም ዘመኑ የሚፈልገዉን ቴክኖሎጂ በመታጠቅ፤ ሰላም የማስከበር አቅሙን አሁንም እያሳደገ ይገኛል ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፥ ለዚህ እንደማሳያ የሚሆነውን የድሮን ቴክኖሎጂን እንደሆን ጠቁምዋል። ኢትዮጵያ የምታመርታቸው ሶስት ዓይነት ድሮኖችን ወዳጅ የአፍሪካ አገራት ለመግዛት ጥያቄ እያቀረቡ መሆኑን ጠቅሰን መዘገባችን አይዘነጋም።
የመከላከያ ሠራዊት ሰላም ከማስከበር በተጨማሪ፤ ትላልቅ ሀገራዊ የልማት ሥራዎች ላይ በስፋት እየተሳተፈ እንደሆነ ያነሱት ደግሞ የመከላከያ ሚኒስትሯ አይሻ ሙሃመድ (ኢ/ር) ናቸው። ሚኒስትሯ የመንገድ ስራዎች፣ የተቋማት ግንባታ እና አረንጓዴ አሻራን ለዚህ ማሳያ አድርገው ለም/ቤቱ አቅርበዋል። ዘገባው ከኢቢሲና ኦቢኤን የተውጣጣ ነው