በእስራኤልና ኢራን መካከል የተጀመረው ጦርነት ተባብሶ ቀጥሏል። ከሁለቱም ወገን የሚወጡ ዜናዎችን የሚያሰራጩ የሚዲያ አውታሮች ይህንኑ በማስተላለፍ ስራ በዝቶባቸዋል። በቀጥታ ስርጭት ጨምሮ የሁለቱንም አገራት የሚሳይል ጦርነት እያሳዩ “ጦርነትን በላይቭ” የሚዘግቡ ሚዲያዎች ከሁለቱም ወገኖች ባለስልጣናትንና የሚመለከታቸውን እየጠየቁ በፍጥነት መረጃ እያሰራጩ ነው።
እስራኤል የኢራንን የአየር ክልል ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሯን ስታስታውቅ፣ የኢራን ፕሬዝዳንት ዶክተር ማሱድ ፔዜሽኪያን ሃገራቸው የኑክሌያር ቦም’ብ የመታጠቅ ፍላጎት እንደሌላት መግለጻቸው በዛሬው ዕለት ተሰምቷል።
የእስራኤል መከላከያ ሃይል የተመረጡ ስትራቴጂክ እርምጃዎችን ከወሰደ በሁዋላ በኢራን የአየር ክልል ላይ ሙሉ የበላይነት መውሰዱን ሲያስታውቅ እንዳለው የኢራንን ወታደራዊ ተቋማት፣ የተመረጡ የጦር ማከማቻና የሚሳይል ማወናጨፊያ፣ እንዲሁም የአየር ላይ ጥቃት ማምከኛ መሰረተ ልማቶችን በጥልቅት እየደበደበ መሆኑን በማስታወቅ ነው።
ኢራን እስራኤላውያንን ከሀገሪቱ ለቀው እንዲወጡ፣ በተመሳሳይ እስራኤልም ኢራን ውስጥ ያሉ በሦስት ከተማ የሚገኙ ዜጎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ እያስጠነቀቀች የቀጠለው ጦርነት እያስመዘገበ ያለው የሟቾች ቁጥር እየጨመረ ነው።
አንዳንድ ነጥቦች
- የኢራን ጦር ኃይሎች ባወጣው መግለጫ፣ እስራኤላውያን በተቻላቸው ፍጥነት ከሀገሪቱ መልቀቅ እንዳለባቸው አሳስባለሁ ብላሏል።
- እስራኤል በቴህራን የሚገኘውን የኢራን የመንግስት ብሮድካስት IRIB በቦምብ ደበደበች፣ ቢሮዎቹ የኢራን ታጣቂ ሃይሎች ይጠቀሙበታል ብሏል። የኢራን ባለስልጣናት ጥቃቱን አጣጥለውታል፣ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በበኩሉ ይህ “እውነትን” ዝም ለማሰኘት የታለመ “ክፉ የጦር ወንጀሎች” ነው ብሏል።
- ኢራን ወደ እስራኤል ሚሳኤሎችን ማሰውንጨፍ ቀጥላለች የእስራኤል ጦርአስሩን ጠልፌ ጥያለሁ ብሏል።
- ፕሬዚደንት ትራምፕ በካናዳ በተካሄደው የጂ 7 ስብሰባ ላይ እንደተናገሩት ኢራን እስራኤል “ጊዜው ከማለፉ በፊት” መነጋገር አለባት ብለዋል። በሆርሙዝ ባሕረ ሰላጤ እና በሰፊው ባህረ ሰላጤ አካባቢ የመርከብ አገልግሎት መስተጓጎል መከሰቱንተመክቷል። በመርከቦ ፈሰት ላይ ጣልቃገብነት እየጨመረ መምጣቱን ተናግረዋል።
- “ግጭቱን አያባብስም፣ እንዲያውም ግጭቱን የሚያቆም ነው” ኔትናሁ የኢራንን ጠቅላይ መሪ ላይ ዒላማ ከማድረግ እንዲቆጠቡ የቀረበውን ጥያቄ አልተቀበሉም
- ከኢራን ጎን መሰለፏን በተደጋጋሚ ያስታወቀችው ፓኪስታን ከኢራን ጋር የሚያዋስናትን ድንበር መዝጋቷን ገልጻለች።
- የኢራን አብዮታዊ ዘብ የስለላ ድርጅት (IRGC) ሃላፊ የሆኑት መሀመድ ካዚሚ እና ምክትላቸው ሀሰን ሞሃቅ በእስራኤል ጥቃት መገደላቸውን ድርጅቱ አረጋግጧል።
- የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የቱርክ አቻቸው ረሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን እስራኤል እና ኢራን በአስቸኳይ ተኩስ አቁመው ወደ ድርድር እንዲገቡ ድምጻቸውን ማሰማታቸውን አልጀዚራ አስታውቋል።
- የእስራኤል መከላከያ ኃይል ቃል አቀባይ እስራኤል፣ “ የቴህራንን አየር ክልል ሙሉ በሙሉ መቆጣጣር ችላለች” ሲሉ መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። ብርጋዴር ጄኔራል ኤፊ ዴፍሪን ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ፤ “የኢራን አንድ ሦስተኛ የምድር ለምድር የሚሳኤል ማስወንጨፊያዎችን አውድመናል” ሲሉ ተናግረዋል።
- የእስራኤል ጦር ከ120 በላይ የሚሳኤል ማስወንጨፊያዎችን ማውደሙን እንደገለጸ ዘገባው ጠቁሟል።
- እስራኤል አርብ ዕለት ጥቃት መሰንዘር ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ ኢራን ከያዘችው አጠቃላይ ማስወንጨፍያዎች ውስጥ አንድ ሦስተኛውን ማውደሟን ገልጻለች።
- የአየር ኃይሉ ትናንት ምሽት ብቻ ከ20 በላይ ማስወንጨፊያዎችን ማውደሙን የገለፁት ቃል አቀባዩ፤ “ከደቂቃዎች በፊት” ወደ እስራኤል ሚሳኤሎችን ለማስወንጨፍ ጥቅም ላይ ውለው እንደነበር ዴፍሪን ተናግረዋል።
- እስራኤል በማዕከላዊ ኢራን ኢስፋሃን ውስጥ ወደ 100 የሚጠጉ ወታደራዊ ዒላማዎች ላይ ጥቃት ለማድረስ 50 የሚጠጉ ተዋጊ ጄቶችን አሰማርታለች። በዚህ ጥቃትም የሚሳኤል ማከማቻ ስፍራዎችን፣ ማስወንጨፊያዎችንና የማዘዣ ማዕከሎችን አውድማለች ሲሉ መናገራቸው ተዘግቧል፡፡