ሻዕቢያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአየር ክልሉ እንዳያልፍ መከልከሉን ይፋ መደረጉን ተከልክሎ ከየአቅጣቻው ቅሬታ እየተሰማ ነው። ይህ ኢትዮጵያን በየብስ የማነቁ ቀጣይ እርምጃ በመሆኑ ጉዳዩ ከህልውና ጋር እንደሚያያዝ እየተገለጸ ነው። መንግስት የኤርትራ መንግስት የዘረፈውን ሃብት አስመክቶ “ያልተመለሰልን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ገንዘብ ብቻ አይደለም በገንዘብ የማይተመንም የምናስመልሰው ትልቅ ንብረት አለን ” ሲሉ ተደምጧል።
የኤርትራ መንግስ የአየር ክልሉን መቆለፉንና የዓለም ዓቀፍ ህጎችን በጣሰ መልኩ ከኢትዮጵያ የዘረፈውን ሃብት ለማስመለስ እየተሰራ መሆኑን ያታወቁት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዶ/ር ጌንዲዮን ጢሞጢዮስ ናቸው። ሚኒስትሩ ለተወካዮች ምክር ቤት ሻዕቢያ ተወስኖበት ያልከፈለው የካሳ ክፍያም እንዲከፈል ይደረጋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በፓርላማ ኤርትራን የአየር ክልሏን መዝጋቷን መግለጻቸውን ተከትሎ ጉዳዩ ሰፊ መወያያ ሆኗል። እሳቸው ባይገልጹትም ዜናው በግብጽ ሰብሳቢነት ኤርትራና ሶማሊያን አካቶ ኢትዮጵያ ላይ የባህር በር ለመጠርቀም ታቅዶ የከሸፈውን ሴራ ያስታወሰ ሆኗል። የቀይ ባህር አካል ያልሆነ አገር በውሃው ላይ ድርሽ እንዳይል ውል አስረው ከጨረሱ በሁዋላ ኢትዮጵያ ሶማሊያን ከስምምነቱ መመንጨቋ ሴራውን ሊያከሽፈው እንደቻለ ያመለከቱ ወገኖች፣ የኤርትራ ውሳኔ ቀይ መስመር መሆኑን እየገለጹ ነው። እነዚሁ ወገኖች መንግስት ለኤርትራ መሪዎች ምላሽ ባይሰጥም ለሕዝብ ግልጽ ማድረግ ያለበትን ጉዳይ ሊያድበሰብስ እንደማይገባም ባይ ናቸው።
ሻዕቢያ ኢትዮጵያን በወኪሎቹ አማካይነት በኮንትሮባንድ ያጥባል፤ በድንበር ሽፍታ እያሰማራ ያተራምሳታል፤ በተላላኪነት የባህርና የብስ መውጫ መግቢያ ለማሳጣት ይሰራል። አሁን ደግሞ የአየር ክልል ቆልፏል። ይህን የሚያደርገውን፣ እንዲህ ያለውን የኢትዮጵያ መርዘኛ ጠላት እየተላላኩ አገራቸውን ለመበተን፣ ዳግም ያደራጀችውን ጦር ለማፍረስ፣ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ላይ የተሰለፉ በስም ኢትዮጵያዊያን ሚዲይዎች እየተጉለት ነው። በኢትዮጵያ ባንዲራ ተጠቅልለው ቅበሩን ሲሉ የነበሩ የኢታውቁቱ ሳይቀሩ የግርድና ላይሰንስ ወስደው አገራቸውን ሃያ አራት ሰዓት እየደብደቡ ነው። ስሜነህ አያሌው በፊስ ቡክ ገጻቸው እንዳሉት መንግስትን መጥላትና ብሄራዊ አጀንዳ የማይለዩ ባንዳዎችን ትውልድና ሕዝብ በቅጡ ሊያንገዋልላቸው ይገባል
ሻዕቢያ ታጣቂ እያሰለጠነና እያስታጠቀ ኢትዮጵያን ሰላም የሚነሳት አንሶ የምድርና የአየር መውጫ በመከልከል እያደረገ ያለው ደባ የህልውና አደጋ መሆኑን ያስታወቁ ዜጎች፣ “በዚህ ደረጃ ኢትዮጵያ ላይ የተነሳን ኃይል ደግፈው፣ ወይም ተገዢ ሆነውለት አገራቸውን ሲያዋክቡ የሚታዩ በስም ኢትዮጵያዊ ሚዲያዎችና የሚታወቁ ፖለቲከኞች ጉዳይ በጥብቅ ሊታሰብበት ይገባል” ሲሉ እየተደመጠ ነው።
የፓርላማ አባሉ ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ጦርነት ስለመነሳቱ አንስተው ለጠየቁት ጥያቄ ምላሽ የሰጡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱ እንዳይበላሽ፣ ከበፊቱ በበለጠ አግባብ እንዲቀጥል መንግትና ሕዝብ እየሰሩ መሆኑ አስቀድመዋል። ኢትዮጵያ ጋር ለመጠጋት የሚመጡ የኤርትራ ተወላጆች ከሕዝቡ መልካም አቀባበል እንደሚደረግላቸው አስታውሰው መንግስት ደግሞ በህግ፣ በፖሊሲና በተቋም ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። በኤርትራ መሪዎች ተግባር ይህ የሕዝብ ግንኙነት እንደማይበላሽም አመልክተዋል።
የውጭ አገር አየር መንገዶችን ገንዘብ አንቀው የያዙ የጎረቤት አገራት መካከል ስሟ ከፊት የሚቀመጠው ኤርትራ የአንድ ወር በረራዋ ቢደመር በአዲስ አበባ አንድ ቀን እንኳን ከሚደረገው ጋር እንደማይወዳደር ያመለከቱት ሚኒስትሩ፣ የኤርትራ መሪዎች ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ አፍነው ያስቀሩትን ሃብት አስመልክቶ የዓለም አቀፍ አሰራርና የአቪዬሽን ህጉ በሚፈቅደው መሰረት ለማስመለስ እየተሰራ መሆኑን አመልክተው፣ የውጭ ምንዛሬ ችግር ካለም በንግግር ማስተካከል የሚቻልበት አግባብ ሊኖር እንደሚችል አመላክተዋል። ሚኒስትሩ አለሳልሰው ባቀረቡት ምላሽቸው የካሳ ክፍያ ጉዳይንና ኢትዮጵያ “በገንዘብ የማይተመን” የመታስመልሰው ሃብት እንዳላት ተናግረዋል።
በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች ሕይወት የቀጠፈውን፣ አካል ያጎደለውን፣ ንብረት ያወደመውና ያፈናቀለው የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት በአልጀርስ ስምምነት ሲቋጭ ከተደረሱት ስምምነቶች መካከል አንዱ፣ የካሳ ጉዳይ ነበር። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ብቻ ሳይሆን የካሳ ኮሚሽኑ የወሰነው ያልተከፈለ ሃብት መኖሩን ጠቆም አድርገው ያለፉት ይህንኑ ነው።
ባድመንና አወዛጋቢ አካባቢዎችን ለማስረከብ አቶ መለስ ፈርመው በስምምነት ከተቋጨ በሁዋላ ስምምነቱን ለማጽናት በተዋረድ ከተቋቋሙት ኮሚሽኖች መካከል የካሳና የቅሬታ ኮሚኖች ይጠቀሳሉ፡፡ ኮሚሽኖቹ ካሳን በመተመንና ቅሬታን ሰምቶ ውሳኔ የመስጠት ዓላማ ይዘው የሚሰሩ ነበናቸው:: በዚህም መሠረት ሁለቱም ኮሚሽኖች ልክ እንደ ድንበርኮሚሸኑ መቀመጫቸውን ሔግ አድርገው ውሳኔ አሳለፉ፡፡
ሰነዶች እንደሚያስረዱት ኢትዮጵያ እንዲከፈላት ያእረበችው ከአምስት ቢሊዮን ብር በላይ ነበር፡፡ ለጠፋው ሕይወት፣ ለቆሰሉትና፣ ከድንበር አካባቢ ለተፈናቀሉ ከ300 ሺህ በላይ ሕዝብ በመንግሥትና በሕዝብ ላይ ለደረሰው የሞራል ውድቀት ተዘርዝሮ ነበር ብሩ የተጠየቀው። እንደ ኤርትራ ዓይነት ደሃ ሕዝብ የያዘ አገርን በዚህ ደረጃ ከፍተኛ ገንዘብ መጠየቅ ትክክለኛ አመክንዮ አይሆንም በሚል ኮሚሽኑ ሂሳቡን ዝቅ አድርጎታል።
ብመጨረሻም ከህጻናት እስከ አዛውንት የቀተፈውን የአይደር ትምህርት ቤት የአየር ጭፍጨፋ አካቶ ኤርትራ ለኢትዮጵያ ከወጪ ቀሪ አሥር ሚሊዮን ዶላር እንዲከፈላት ቢወሰንም ዛሬ ድረስ የተከፈለ ነገር የለም።ተወሰነ። የድንበር ጦርነቱ በሚያዚያ 28/1990 ዓ.ም መጀመሩና በታህሳስ 2002 ዓ.ም አልጀርስ ላይ የሰላም ስምምነት መፈራረማቸው አይዘነጋም።
“መንግስታዊ ማጅራት መቺ” የሚባለው የሽማግሌዎች ስብስብ ለዓለም ዓቀፍ ህግና ደንቦች የማይገዛ፣ በዝርፊያ፣ በኮንትሮባንድ፣ በክፍያ የሽብር ቡድኖችን፣ ታጣቂዎችን በማሰለጠንና በማስታጠቅ የሚተዳደር። የመንግስት ቅርጽ የሌለው ክፉ ጎረቤት በመሆኑ የኤርትራም ሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲያርፉ እርምጃ ለምውሰድ ጊዜው አሁን ነው። በቃ። ሻዕቢያ እያለ ኢትዮጵያ ሰላም ልትሆን አትችልም” የሚሉ ወገኖች እየበረከቱ መሆኑ ይታወቃል።