“ጥሩ የዕለት ተዕለት የሕዝብ ግንኙነት የላቸውም” የሚባሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ መድረክ ሲያገኙ የሚሰጡት መረጃ በደጋፊዎቻቸው ዘንዳ የሚያበሳጭ ነው። እነዚሁ ወገኖች እንደሚሉት ይህ ሁሉ መረጃ እጃቸው ላይ እያለ በላይ በላዩ ለሕዝብ ማቅርበና ሕዝብ የተመጣጠነ መረጃ እግኝቶ ፍርዱን እንዲሰጥ የማይደረግበት ምክንያት እንደማይገባቸውም እነዚሁ ወገኖች ይናገራል።
ከመላው ሀገሪቱ ከተውጣጡ የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት ከተነሱላቸው ጥያቄዎች መካከል አብዛኞቹ በዕለት ተዕለት የሕዝብ ግንኙነት ስራ ሊሰሩ እንደሚገባ እንደነበር የሚገልጹ ወገኖች፣ የአገሪቱን ሰላም የረበሹት ስልሳ ከመቶ የሚሆኑት የአገሪቱ ባለሃብቶች መሆናቸውን ሲሰሙ አዝነዋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ እዛም እዚህም የሚነሳውን ጦርነት አስመልክቶ “የሰላም ያልህ” ሲሉ ጥያቄ ያቀረቡ ነጋዴዎች የተሰጣቸው መልስ “ራሳችሁ እየቀለባችሁ ፤ ፋይናንስ እያደረጋችሁ እኔን መልሳችሁ ሰላም ብትሉኝ አይሆንም። ሰላም ከፈለጋችሁ ፋይናንስ አታድርጉ” የሚል ነበር። ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ መንግስት መረጃ እንዳለው የሚያመላክት ስለመሆኑ ጥርጥር ባይኖርም የመንግስት የተለያዩ ኃላፊዎች ከሕዝብ ጋር ሲገናኙ ለሚነሳላቸው ተመሳሳይ ጥያቄ በዚህ መልኩ አንድም ቀን ሲናገሩ አለመሰማታቸው አስገርሟል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ በስብሰባው ላይ የሰላም ችግር እንደሚወራው ባይሆንም በባለሃብቶች የስራ እንቅስቃሴ ላይ ችግር እንደሚያስከትል አልካዱም ይሁንና ስላሳ ከመቶው ችግር እዛው ፊታቸው ከተሰበሰቡት ነጋዴ ባለሃብቶች የሚመነጭ መሆኑ ለሰሚዎች ድንጋጤን ፈጥሯል።
ጠ/ሚ ዐቢይ “ጫካ ያሉትን ታጠቂዎች በገንዘብ መደገፍ ወይም ማበረታታት አቁሙ፣ ገንዘብ ወደ ጫካ አትላኩ” ሲሉ በግልጽ ባስታወቁበት ንግግራቸው ተሰብሳቢ ባለሃብቶቹ እውነተኛ ሰላም ፈላጊ ከሆኑ በጫካ ያሉ ኃይሎችን መደገፍ ፣ መቀለብ አቁመው ወደ ሰላም እንዲመጡ መምከር እንደሚጠበቅባቸው አስገንዘበዋቸዋል። ሰላም በህብረት እንደሚመጣም ነገረዋቸዋል።
የበጀት ማዘጋጃ ላይ በመከር ግብአት ለመውሰድ መድረኩ መዘጋጀቱን ያመለከቱት አብይ አሕመድ፣ ” ሰላም የሚፈልግ ካለ በእኛ በኩል ምንም ችግር የለውም እንቀበላለን እናንተ ጫካ ብር አትላኩ ” ብለዋል። አክለውም መንግስት በሰላም የሚመጡ አካላትን ተቀብሎ ለማወያየት ዝግጁ መሆኑንም አስረግጠው ተናግረዋል። ለሰላም የማይገዝሹትን ደግም ” ህግ ማስከበር ስራችን ስለሆነም የሚቀጣ ካለ እንቀጣለን ” በማለት ተናግረዋል።
“የኢትዮጵያ ሃብታሞች የሀገሪቱን ሰላም በማደፍርስ ላይ 60 በመቶ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ” ሲሉ የከሰሱት አብይ አሕመድ፣ የሰላም ችግር ትልቅ ኪሳራ እንዳለው ሳይሸሽጉ ተናግረዋል።
“የሰላም ችግር ትልቅ ኪሳራ ነው ” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ” ተቃዋሚዎችም ሆኑ ባለሃብቶች ሰላምን የማረጋገጥ ግዴታ የመንግስት ብቻ አድርገው በመውሰድ ከሃላፊነት መሸሽ ተገቢ አይደለም ” በማለት ሁሉም ለአገሪቱ ሰላም መከበር የበኩላቸውን ማበርከት እንዳለባቸው አስታውቀዋል።
በሌላ በኩል መንግስት ኮንትሮባንድን እና ህገወጥ የመሳሪያ ዝውውርን ለመቆጣጠር ባዘጋጃቸው የፍተሻ ኬላዎች የኮቴ እያሉ ገንዘብ የሚጠይቁ አካላት እንዳሉ በውይይቱ ለተነሳው፣ ጸጥታን አንተርሰው ምላሽ ሰጥተዋል። የፍተሻ ኬላዎቹ የማይኖሩ ከሆነ ህገወጥ የጦር መሳሪያዎች እየገባ የሰዎችን ህይወት እንደሚቀጥፍ አመልክተ፣ ፍተሻው እየተካሄደ ክፍያ ኝ የሚቆምበትን አግባብ ለማመቻቸት እንደሚሰራ ገልጸዋል።
በየኬላው ገመድ እየወጠሩ ገንዘብ የሚለቅሙ ዞሮ ዞሮ ጫናውን የሚያሳርፉት አገልጋዩ ላይ ዋጋ በመጨመር በመሆኑ መንግስት ትኩረት እንዲያደርግ በተደጋጋሚ ጥያቄ ሲቀርብ እንድነበር ይታወሳል።
በሌላም በኩል “ዜና የዛሬን ብቻ የማሰብ ችግር መልካም ጅምሮቻችን ላይ እንቅፋት አብዝቷል” በማለት ነገን በማሰብ ለነገ ዛሬ እንቅፋት ከመሆን መቆተብ እንደሚያስፈልግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አስገንዘበዋል። ነገን ታሳቢ ያደረጉ ምክክሮችን ከማድረግ ይልቅ የዛሬን ብቻ የማሰብ ችግር መልካም ጅምሮቻችን ላይ እንቅፋት አብዝቷል።
ኢትዮጵያ ሁለት ፈተናዎች እንዳሉባት ጠቅሰው፥ መንግስታት የትናንትናውን ችግር ቢፈቱም ነገን መስራት ካልቻሉ መከራው በሚመጣውም ትውልድ ይቀጥላል ብለዋል፡፡ የአሁንን ተጨባጭ ሁኔታ ማወቅ፣ ያለፉትን ስብራቶች መጠገንና የመጪውን መሽቀዳደም የሚጠይቅ ዘመን እንደሆነ አስገንዝበዋል፡፡
ፋና ስበባው ላይ የቀረበውን አስተያየት ጠቅሶ እንዳለው አብይ አሕመድ “መከራችን የትናንት እና የነገ ነው” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ነገር ግን የእለት የእለቱን ብቻ ከማሰብ በዘለለ ነገን በማሰብ ምክክር ስለማናደርግ ብዙ ጅምሮቻችን መልካም ሥራዎችም ቢሆኑ እንቅፋቶቻቸው የበዛ ነው ብለዋል፡፡
የዕለት የዛሬን ብቻ በማሰብ ነገ እንዳያመልጠን ለማስተማር ከመንግስት ባልተናነሰ የንግዱ ማህበረሰብ ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡ አምስት ዋና ዋና ችግሮች መኖራቸውን ያነሱ ሲሆን፥ አንደኛው ችግር የወረስነው ድህነትና ድህነት ለመውረስ የተዘጋጀ ትውልድ መኖሩ ነው ብለዋል፡፡
ለአብነትም በአዲስ አበባ ካዛንቺስ አካባቢ ከአሁን ቀደም የነበረው ሁኔታ ለመኖር ምቹ እንዳልነበር አስታውሰው፤ የህብረተሰቡን አኗኗር ለማሻሻል ወደ ተሻለ አካባቢ እንዲሄዱ መደረጉን ተናግረዋል፡፡
ከአንድ አካባቢ ወደሌላ አካባቢ እንዲሄዱ ሲደረግ መሰረታዊ ጉዳዮች መሟላታቸውን ከማረጋገጥ ይልቅ ሌሎች ስሞችን የመስጠት ልምምዶች ድህነትን ወርሶ ድህነት የማውረስ ችግር መሆኑን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለጹት፡፡
ሁለተኛው ችግር ተቋማዊና መዋቅራዊ ሲሆን፥ መንግስት ይህንን ለመፍታት ስትራቴጂ ቀርጾ ሥራ ሲጀምር በዘርና በኃይማኖት ስም ሰራተኛውን ሊያባርር ነው የሚል ዘመቻ እንደተከፈተበት አስታውሰዋል፡፡
ከአራሹ ይልቅ ተኳሹን የሚያወድስና ጠዋትና ማታ ጠንክሮ ከሚሰራው ይልቅ ክላሽ እንግቶ የሚሳደበውን ሰው ጀግና የሚል አመለካከት ሌላኛው ችግር እንደሆነ አንስተዋል፡፡
ከሚሰራ ሰው ይልቅ ተኳሹን የማወደስ አመለካከት ነጋዴውን እንደ ሥራ ፈጣሪ ሳይሆን እንደሌባና እንደ አጉዳይ እንዲታይ አድርጎታል ብለዋል፡፡ በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ የሰው ኃይልን በማብቃትም ሆነ በሌሎች ዘርፎች ያለው የስልተ ምርት ችግር አራተኛው ችግር መሆኑን ገልጸው፥ ይህን በማለፍ እንዴት ውጤታማ መሆን ይቻላል በሚለው ጉዳይ ላይ ይበልጥ ማሰብ እንደሚጠይቅ ተናግረዋል፡፡ በሀገራችን ከሚስተዋሉ ዋና ዋና ችገሮች መካከል የማገልገል ችግር አንዱ መሆኑንም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያስረዱት፡፡