በተለያዩ አደረጃጀቶች ከሚታውቁት የፋኖ አካላት መካከል በደቡብ ወሎና ሰሜን ሸዋ የሚገኘው ኃይል በሰላም አማራጭ ድርድር ወደ መግባባቱ መድረሳቸው ተሰማ። በክረምት ጦርነትን ለመክፈት ዝግጅት እያደረጉ ካሉት ጋር ለመገናኘት ሱዳን ያመሩ መኖራቸው ታውቋል።
የኢትዮሪቪው የዜና አቀባዮች እንዳሉት ከሆነ በደቡብ ወሎ የሚንቀሳቀሰው የአማራ ፋኖ በወሎ ዕዝ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ፋንታሁን ሙሃባ ጋር እየተደረገ ያለው ንግግር መግባባት ላይ የተደረሰበት ነው። ይህ ኃይል አሁን ላይ ደላንታ አካባቢ የተቀመጠ ሲሆን ውጊያም ሆነ ተኩስ እንደሌለ፣ ሕዝቡም ስጋቱ የቀነሰለትና ስምምነት እንዲደረግ የሚሻ ነው።
የዝግጅት ክፍላችን ተባባሪ ከአዲስ አበባ ለኮሎኔል ፋንታሁን ደውሎ ” አይመቸኝም” የሚል ምላሽ እንደሰጡት አመልክቷል። ደግሞ ሲደውል ጥሪውን አስቁመዋል። ጉዳዩን የሚከታተሉት ወገኖች ዝርዝር ጉዳይ ውስጥ መግባት ባይፈልጉም በቅርቡ ይፋ የሚሆን ጉዳይ ስለመኖሩ አስታውቀዋል።
በሰሜን ወሎ አካባቢ የሚንቀሳቀሰው የምሬ ወዳጆን ኃይል አስመልክቶ እነዚሁ ወገኖች እንዳሉት ከሆነ በቅርቡ ከእገት ጥቆማ ጋር ተያይዞ የአገር መከላከያ በወሰደው እርምጃ ላስታ የነበረውን መሰረታቸውን ማስጠበቅ አቅቷቸው የተረፈውን ኃይል በመያዝ ትግራይ ድንበር ኮረም አካባቢ ለጊዜው ማረፋቸውን ጠቅሰዋል።
ምሬ ከሚመራው ኃይል ውስጥ በብዛት እጃቸውን መስጠትና መግባት የሚፈልጉ እንዳሉ የሚጠቅሱት ወገኖች ችግር እንደገጠማቸው ገልጸዋል። የአገር መከላከያ እጃቸውን የሚሰጡ የፋኖም ሆነ የሸኔ ኃይሎች መሳሪያ ይዘው ካልመጡ አይቀበላቸውም። አሰራሩን የሚያውቁት ኧዚሁ ክፍሎች እጃቸውን ከሰጡ መስማታቸውን በማለከት እንዳሉት የምሬ ፋኖ ኃይላት መሳሪያ ፈትተዋል።
ሲያብራሩም ሲያስፈልግ ካልሆነ በቀር ታጣቂዎች መሳሪያ አይይዙም። በአካባቢው ቋንቋ ” መሳሪያ ይከዘናል” በዚህም የተነሳ እጃቸውን መስጠት የሚፈልጉ የምሬ ኃይሎች ችግር ገጥሟቸዋል። ያም ሆኖ ባገኙት አጋጣሚ ሲታጠቁ ሸሽተው የሚመጡ አሉ።
ሰሜን ሸዋ የመሸገው እስክንድር ነጋን አስመልክቶ “እሱም በንግግር ላይ ነው፤ ከኮሎኔል ፋንታሁን የተለየ ነገር የለውም” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። እስክንድር ባለበት አካባቢ አሁን ላይ ምንም ጦርነት እንደሌለ የአካባቢው ነዋሪዎች ምስክር ናቸው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የጎጃም ፋኖ አመራሮች ወደ ሱዳን ማቅናታቸው ታውቋል። ስማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ በዱባይ የሚኖሩና ለድርጅቱ ቅርብ እንደሆኑ የሚናገሩ እንዳሉት የጉዞው ዓላማ በክረምት ለታቀደው ውጊያ ለመነጋገርና ነው።
ሱዳን ላይ የትህነግ፣ የሻዕቢያና የአማራ ፋኖ በጎጃም ወኪሎች እየመከሩ እንደሆነ በተላያዩ አካላት ሰሞኑን ሱገለጽ መሰንበቱ ይታወቃል። በትግራይ ሕዝብ ጦርነት መቃወሙና ጭራሽ የጦርነት ወሬ መስማት እንደማይፈልግ ማስታወቁ፣ በጎንደር አካባቢ ያለው የፋኖ አደረጃጀት በብዛት ወደ ሰላማዊ መንገድ መመለሱና በወልቃይት ሰፊ ህዝባዊ አደረጃጀት መፈጠሩ፣ መከላከያ ሰፊ ኃይልና ትጥቅ ማደራጀቱ አንድ ላይ ተዳምሮ የክረምት የውጊያ ዕቅዱ ላይ ስጋት ማስነሳቱን አንዳንድ ወገኖች ይናገራሉ።
በቀርቡ ልደቱ አያሌው፣ ቴድሮስ ጸጋዬና ጃዋር መሐመድ ያዘጋጁት የሰማይ ላይ ትዕይነት ላይ የተሳተፉት አካላት ” መንግስት ቢለመን፣ ለውይይትና ለድርድር ቢጋበዝ፣ ሁሉንም ያካተተ የሽግግር መንግስት እንዲያቋቁም ቢጠየቅ እምቢ ስላለ ግንባር ለመፍጠር ተዘጋጅተናል” ለማለት ዝግጅት ላይ መሆናቸውን ያስታወቁት የዜናው ሰዎች የሱዳኑ ምክክር የዚሁ ጅማሬ እንደሆነ አመልክተዋል።
በዚሁ የኢንተርኔት ሰልፍ ላይ ከተሳተፉት መካከል አንዱ የሆኑትና የሶማሌ ህዝብን ኮንግረንስን ወክለው የተሳተፉት ዶከተር ኢስማኤል ጎርሴ “ተሸውደን ነው። የሸወደን ልደቱ ነው። ከስብሰባው በሁዋላ በስልክ አነጋግሬው ሁሉንም ጉዳይ እናጋልጣለን። የሰራችሁት ሁሉ ስህተት ነው። ማጭበርበር ነው” በማለት ቅሬታቸውን ሲገልጹ አቶ ልደቱ ” ኮሚቴው አስገድዶኝ ነው ጠብ መንጃ ያነሱ ኃይሎችንና እነ ስብሃትን የጋበዝኩት” የሚል መልስ እንዳገኙ በስልክ ለኢትዮሪቪው ገልጸዋል። እሳቸው እንዳሉት የብሄር ብሄረሰቦች ክምችት እንዳለው ለማስመሰለ ታስቦ የተሰራው ስብሰብ ቀጣይ ዕቅዱ ግ ንባር መመስረት ነው። ከዶከተር ኢስማኤል ጎርሴ ጋር ያደውረገነውን ቃለ ምልልስ ሙሉውን እናቀርባለን።
በዚሁ መነሻ በሱዳን የተሰባሰቡት አካላት ግንባር ሊፈጥሩ የሚችሉበትን አግባብም ያመቻቻሉ ተብሎ የጠበቃል፤ ጥምረቱ አሁን ያፋ ባይሆንም አካሄዱ ግን ወድዚያው እንደሆነ እንቅስቃሴውን የሚከታተሉ ገልጸዋል።
በሌላ ዜና ሻዕቢያ በበላይነት እየሰራው ያለውን ይህን ጥምረት በፕሮፓጋንዳ ለማገዝ 460 ሺህ ዶላር መመደቡን የስብሰባው ተሳታፊዎች አጋልጠዋል። ካጃዋር ጋር ተጣልተው የነበሩ የኦሮሞ ልሂቃንና አብረውት ሲሰሩ የነበሩ አክቲቪስቶችን በማስማማት ፕሮፓጋንዳው ኦሮሚያ ላይ ስንጥቅ እንዲፈጥር እንዲጠናከር ዕቅድ ተያዟል።
የአቶ ታዬ ደንደአ ቃለ ምልልስ የዚሁ ኦሮሚያን የመከፋፈልና ትህነግ ያጣውን ስም ለመመለስ የሚደረግ ዘመቻ አንዱና የመጀመሪያው ምዕራፍ እንደሆነ ተመልክቷል። አቶ ታዬ ብቻ ሳይሆኑ ሌሎችም ከመሃል በማውጣት ” ይህን ሰምቻለሁ፣ ይህን በሚስጢር አድርገናል ወዘት …” በሚል መንግስትን በተለይም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ያነጣጠረ፣ መከላከያን የሚከፋፍል ዘመቻ አከታትሎ ለማቅረብ ሰፊ ዕቅድ መያዙን የዲሲው ተባባሪያችን አስታውቋል።
በግብጽ የበላይነት ሻዕቢያ የሚመራው ይህ ኃይል መዳረሻ ዕቅዱ የኢትዮጵያን መከላከያ ማፍረስ እንደሆነ፣ ይህንንም ለማሳካት ልክ በደርግ ጊዜ ” የመንግስቱ ጦር፣ የፋሽስት ጦር” ወዘተ በማለት የአገር መከላከያን ለማፍረስ የዳቦ ስም እንዳወጡት ሁሉ አሁንም በዘመናዊ አደረጃጀት የተሰራውን የኢትዮጵያ አገር መከላከያ ለመበተን ” የአብይ ጦር፣ የብልጽግና ጦር…” ወዘተ በማለት የሚሰራው ማጠልሸት እንደሆነ ፕሮፓጋንዳውን እንዲሰሩ ከተመደቡት ጋር ቅርበት ያላቸው ለዲሲው ተባባሪያችን ነግረውታል። የአገር መከላከይ ሰራዊት አባላት ሜዳ ላይ ተጥለው ለማኝ እንደተደረጉ የሚታወስ ነው።