ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአራተኛው ክፍል እና በመጨረሻው ቃለ ምልልሳቸው ኢትዮጵያ በታሪክ የባሕር በር (ወደብ) ያጣችበት መንገድ እንደሚያስቆጫቸው ሲናገሩ ” ኢትዮጵያ ላይ ግፍ ተፈጽሟል” በሚል ቁጭት ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ውስጥ በጠብ መንጃ ስልታን መያዝ ያከተመለት ጉዳይ እንደሆነም አስታውቀዋል። በኃይል የስልታን ፍላጎትን ለማሳካት የሚደረጉ ሙከራዎች ዋነኛ መንስኤያቸው የፖለቲከኞች ከፍተኛ የስልጣን ጥማት እና የተሳሳተ ትርክት ነው ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ባለፉት 30 ዓመታት ወደብ እንደሌላት አስታውሰው፣ በዚህ በዓለም ወደብ አልባ ሀገራት ልምምድ የሌለ ግፍ በኢትዮጵያ ላይ ተፈጽሟል ሲሉ ቁጭታቸውን ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤት መሆን አለባት የሚለው ሃሳብ ጠቅላይ ሚኒስትር ከመሆናቸው ከአስርና አስራ አምስት ዓመታት በፊት በገሃድ ያነሱት የነበረ ቁልፍ ጉዳይና የጸና አቋማቸው እንደሆነ ለኢትዮጵያ ህዝብ አስታውቀዋል። አያዘውም ጉዳዩ ዘመን አመጣሽ አጀንዳ አለመሆኑን ሲያስገነዝቡ ይህ ቁጭታቸው ከዓመታት በፊት የተነጸባረቁባቸው በረካታ የጹሁፍና የፊልም ሰነዶች እንዳለ አመልክተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ኢትዮጵያ የባህር በር እንደሚያስፈልጋትና ይህንኑ ፋልጎቷን በሰላማዊ መንገድ በሰጥቶ መቀበል ማስፈጸም እንደምትችል ማስታወቃቸውን ተከትሎ ለፖለቲካ ፍጆታ ድንገት የተነሳ ጉዳይ አድርገው ለሻዕቢያ የወገኑ የስም ኢትዮጵያዊያን ማጣጣላቸው አይዘነጋም። አብይ አሕመድ በዋናነት ለሕዝብ ሲቀጥልም አገራቸው ላይ ለዘመቱ አቋማቸውን በድጋሚ በማጽናት ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት የመሆን ህልሟን እንደምታሳካ አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያ የባህር በር አልባ የሆነችበት ውሳኔ ትክክል አንዳልነበር አጽንኦት ሰጥተው ሲናገሩ “ኢትዮጵያ ወደብ አልባ በመሆኗ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷባታል” ብለዋል፡፡ አክለውም “ማንንም ሳንጎዳ ጉዳታችንን መቀነስ ኝ አለብን” ሲሉ የመንግስታቸውን አቋም አመልክተዋል።
የኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ጥያቄ አፋጣኝ መፍትሄ ሊያገኝ የሚገባው ጉዳይ መሆኑን ያስታወቁት አብይ አሕመድ ይህን አጀንዳ ይፋ ያደረጉ ዕለት ” ጀግና ዳግም ተወለደ” በሚል በባህር አልባነት ሲብሰለሰሉ የቆዩ፣ በሕግ የኢትዮጵያን መብት ለማስከበር ሲጠይቁ “አርፋችሁ ቁጭ በሉ” የተባሉ ኢትዮጵያዊያን አድናቆታቸውን መግለጻቸው አይዘነጋም። ሕዝብም አጀንዳውን ተቀብሎ እያንዳንዷን ቀን ምን ሊከሰት እንደሚችል እየተጠባበቀ ነው።
የባሕር በር በቂ ሃብት መሆኑን የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ጥያቄዋ በንግግር እና በሕግ አግባብ መልስ እንዲያገኝ የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል፡፡ በህግና በሰላማዊ አግባብ ካልሆነ የሚሆነውንም አመልክተዋል።
“ይህ ካልሆነ” አሉ አብይ አሕመድ፣ “ይህ ካልሆነ የተጎዳ እና የተሰበረ ሀገር በዘላቂነት የሰከነ ሰላም ያመጣል ብዬ አላስብም፤ መቼም ሆነ መቼ ጉዳዩ በንግግር መስመር መያዝ አለበት” ሲሉም አስገንዝበዋል።
የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ ከጦርነት ናፋቂነት ጋር በማያያዝ ለመወንጀል፣ በዙሪያዋ ያሉ አገራትን በማስተባበር ጫና ለመፍጠር ግብጽ የምትመራቸው ኤርትራና ሶማሊያ አብረው እንደነበር የሚታወስ ነው። አሁን ላይ ሶማሊያ ከአድማው የወታች ሲሆን፣ ኤርትራ የጎጃም ፋኖንና ትህነግን በማስከተል በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ ወታደር ማስፈሯ፣ ትግራይን ነጻ የጦርነት ቀጣናዋ አድርጋ እየተንቀሳቀሰች መሆኑን ከትግራይ የሚወጡ ዜናዎች ያረጋግጣሉ።
በትጥቅ ትግል የስልጣን ፍላጎትን ማሳካት የሚቻልበት ጊዜ አብቅቷል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በትጥቅ ትግል የፖለቲካ ስልጣን ፍላጎትን ማሳካት የሚቻልበት ጊዜ አብቅቷል አሉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባደረጉት ባለ አራት ክፍል ቃለ ምልልስ በክፍል አራትን ጠቅሶ ፋና እንዳለው ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ግጭቶችና በሃይል ፍላጎትን ለማሳካት የሚደረጉ ሙከራዎች ዋነኛ መንስኤያቸው የፖለቲከኞች ከፍተኛ የስልጣን ጥማት እና የተሳሳተ ትርክት ነው ብለዋል፡፡
እነዚህ ሃይሎች ከምርጫ እና ከሕዝብ ይሁንታ ይልቅ ስልጣን የሚገኘው በመሳሪያ ብቻ ነው ወይም ደግሞ ስልጣን ስልጣን የሚሆነው እኔ ከመራሁ ብቻ ነው ብለው የሚያስቡ ናቸው ብለዋል፡፡
የለውጡ ሃይሎች ብዙ ፈተና ቢደርስባቸውም ከትጥቅ ትግል ይልቅ ሰላማዊ አማራጭን ቅድሚያ በመስጠት እና ውስጣዊ ፖለቲካ ማሻሻያ በማድረግ ለውጡን እውን ማድረግ መቻሉን አስታውሰዋል፡፡
በትጥቅ ትግል ሀሳብን ማሳካት የሚቻልበት ጊዜ አብቅቷል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፥ በግጭት የሚሳተፉ ሃይሎች ወደ ሰላማዊ አማራጭ እንዲመጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
መንግስት ለሰላም ሁሌም በሩ ክፍት መሆኑን ጠቅሰው ÷የፕሪቶሪያውን ስምምነት ጨምሮ በተለያዩ ጊዜያት መንግስት ለሰላም ያለውን ቁርጠኝነት በተደጋጋሚ አሳይቷል ብለዋል፡፡
መንግስት አካታች የፖለቲካ ሥነ ምህዳር ለመፍጠር የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሙን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፥ በዚህም ዜጎች መስተካከል አለባቸው ያሏቸውን ሀሳቦች ለኮሚሽኑ እያስረከቡ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡
ይህም እንደ ሀገር ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት የሚደረገውን ጥረት በእጅጉ እንደሚያግዝ ነው አጽንኦት ሰጥተው ያብራሩት፡፡
ስልጣን ሀሳብን በመሸጥ በሕዝብ ዘንድ ሲገዛ የሚገኝ ነው ፤ በትጥቅ ትግል እየተንቀሳቀሱ ያሉ ሃይሎች ወደ ሰላም አማራጭ በመምጣትና በፓርቲ በመደራጀት ሃሳባቸውን ማሳካት እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡
ሕዝቦች ራሳቸውን በራሳቸው ማስተዳደር የሚችሉበት እንጂ አንዱ አንዱን የሚገዛበት ሥርዓት የለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፥ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ባህል ከመገዳደል እና መጠላለፍ መውጣት እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡