ኢትዮጵያ በኮቪድ -19 በሚያዙና እና በፅኑ ህሙማን ቁጥር ከአፍሪካ ቀዳሚ መሆኗን በጤና ሚኒስቴር የኮቪድ -19 ምላሽ ግብረ-ሃይሎች አስተባባሪ ዶክተር ሚዛን ኪሮስ አስታወቁ። የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ምጣቱን አመለከቱ።
ዶክተር ሚዛን ኪሮስ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት ፣ ኢትዮጵያ በኮቪድ -19 በሚያዙና እና በጽኑ ህሙማን ቁጥር ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆናለች። ከቅርብ ጊዜ ወዲህም በሀገሪቱ የኮቪድ -19 ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መጥቷል፡፡
በሽታው ያለባቸው እና በጽኑ ህክምና ላይ የሚገኙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ በየጊዜው እየጨመረ መምጣት የበሽታው ስርጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው ፡፡ ይህም የበሽታው ስርጭት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ጠቋሚ ነው ብለዋል፡፡
የምርመራ ውጤቶች ከቀን ቀን የሚሊያዩ ቢሆንም ባለፉት ሶስት ሳምንታት በተለይ በአዲስ አበባ እና በሃዋሳ የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ ማሻቀቡን አመልክተው፣ በሚፈለገው ልክ ምርመራዎች እየተካሄዱ ባለመሆናቸው እንጂ በሌሎች ክልሎችም የበሸታው ስርጭት እየጨመረ ስለመምጣቱ ጠቋሚ ምልክቶች እንዳሉ አመልክተዋል። የቫይረሱን አጠቃላይ ትክክለኛ ስርጭት ለማወቅም በቅርቡ ሰፊ ሀገራዊ ጥናት እንደሚካሄድም ጠቁመዋል፡፡
(ኢ ፕ ድ)
- ምንጩ ያልታወቀ ንብረት የሚወረስበት ረቂቅ አዋጅ ጫጫታ አስነሳ፤ ጸረ ሙስና በሺህ የሚቆጠር ጥቆማ ደርሶታል“በኢትዮጵያ ሌብነት ወይም ሙስና የከፋ ደረጃ ላይ ደርሷል” የሚለው ዜና… Read more: ምንጩ ያልታወቀ ንብረት የሚወረስበት ረቂቅ አዋጅ ጫጫታ አስነሳ፤ ጸረ ሙስና በሺህ የሚቆጠር ጥቆማ ደርሶታል
- ሀሰተኛ ክስና ማስረጃ የሚያስከትለው የሕግ ተጠያቂነትሰዎች ሌሎች ሰዎችን በሀሰት ከሰው የማስቀጣት፣ ያልተገባ ጥቅም የማግኘት ወይም… Read more: ሀሰተኛ ክስና ማስረጃ የሚያስከትለው የሕግ ተጠያቂነት
- ስኳር ያለባቸው ነፍሰ ጡር እናቶች ኢንሱሊንን ሆድ ላይ መወጋት ይችላሉ?በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ5 እናቶች አንዷ በእርግዝና ጊዜ ለሚከሰት የስኳር… Read more: ስኳር ያለባቸው ነፍሰ ጡር እናቶች ኢንሱሊንን ሆድ ላይ መወጋት ይችላሉ?
- Ethiopia MoU agreement will open a new page for the Horn of Africa connectivity,The Minister of Transport and Logistics of the Federal Government… Read more: Ethiopia MoU agreement will open a new page for the Horn of Africa connectivity,
- “ወደ ቅድመ 2010 እንመለስ” ሲባል?”ቅድመ 2010″ ምን ነበር? እንዴትስ ነበር?It is with the strongest possible terms that We say… Read more: “ወደ ቅድመ 2010 እንመለስ” ሲባል?”ቅድመ 2010″ ምን ነበር? እንዴትስ ነበር?