ጦርነት በሌለበትና ተዋጊ የሆኑ ሁለት ኃይሎች በማይታዩበት ሁኔታ ተኩስ አቁሙ የሚለው የአሜሪካን ጥሪ ግራ የሚያጋባ መሆኑን የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኢሶዴፓ) ፕሬዚዳንትና የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ተናገሩ::
ፕሮፌሰር በየነ በተለይም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳሉት በሰላም ተነጋግራችሁ ችግራችሁን ፍቱ የሚለው አባባል የተለመደ ነው፤ ነገር ግን ጦርነት በሌለበትና ተዋጊ የሆኑ ሁለት ኃይሎች በማይታዩበት ሁኔታ ተኩስ አቁሙ ማለት ግራ የሚያጋባ ነው::
እንደ ፕሮፌሰር በየነ ገለጻ ይህ አሁን ያሉትም የተኩስ አቁሙም ሆነ ተደራደሩ የሚለው ሃሳባቸው እውነታውን የሚያሳይ ነው ወይ ? ወይም ደግሞ ኢትዮጵያን የሚመለከት ነው፤ አይደለም? የሚለውን በጥንቃቄ ማየት ያስፈልጋል::
ይህ አባባል “ህወሓት አሁንም እየተዋጋ ነው፤ የኢትዮጵያ መንግሥትም በትግራይ ክልል ውስጥ ጦርነት ላይ ነው፤” የሚል እንደምታ ያለው ነው ፤ ያሉት ፕሮፌሰር በየነ ነገር ግን የመንግሥት አቋምም ሆነ መሬት ላይ ያለው እውነት ህገወጥ የሆኑ ኃይሎች ላይ እርምጃ በመውሰድ ወንጀል የፈጸሙትን አድኖ የመያዝ ሂደት መሆኑን አብራርተዋል::
በመሆኑም ጦርነት በሌለበትና ተዋጊ የሆኑ ሁለት ኃይሎች በማይታዩበት ሁኔታ ተኩስ አቁሙ ማለት ትንሽ ግራ የሚያጋባ በመሆኑ ይህንን አቋማቸውን ከቻሉ ሰላማዊ መንገድ ፈልጉ፤ የሚሸሹትንም ጁንታዎች ሽሽታችሁን አቁማችሁ ለህግ ተገዙ በማለት ለማስማማት ቢሞክሩ የተሻለ እንደሚሆንም ጠቅሰዋል::
በአገር ውስጥም ይሁን በዓለም አቀፍ ደረጃ ወንጀል ፈጽሞ የተደበቀን አካል አሳዶና አድኖ መያዝ ያለና ወደፊትም የሚሠራበት አካሄድ ነው ያሉት ፕሮፌሰር በየነ መንግሥት ይህንን እያደረገ ባለበት ሁኔታ ላይ እንዲሁም የታቀደ ወይም የተለዩ ሁለት ኃይሎች ኖረው ያልተከፈተን ጦርነት ተኩስ አቁሙ ማለት ግራ የገባው ውሳኔ ይመስላል ብለዋል::
ባለኝ መረጃ በሁለት ወገን የተደራጁ ወታደሮች ውጊያ እያደረጉ አይደለም ያሉት ፕሮፌሰር በየነ፤ መንግሥትም ሁኔታው ይህ ነው አላለም ፤ነገር ግን ወንጀለኞቹ ዛሬ ከተደበቁበት ዋሻ ነገ ደግሞ ወደሌላ እየሄዱ እንዳሉና እነሱን እያደነ መሆኑን ገልጿል፤ ይዞም ፍርድ ቤት ያቀረባቸው አሉ ብለዋል፡፡
እነርሱ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሱት ከሚሰጣቸው የተሳሳተ መረጃ በመነጨ ነው ያሉት ፕሮፌሰር በየነ መገናኛ ብዙሃኑ እንዳንገባ ተደረግን በማለት ይጮሁና ሲገቡ ደግሞ ሪፖርት የሚያደርጉት ያልሆነና የተሳሳተ፤ መሬት ላይ ያለውን እውነት የማያሳይ ነው፤ በሌላ በኩልም ዕርዳታ እንሰጣለን በማለት የሚመጡትም ሥራቸው የተዛባ መረጃን ማቅረብ ነው፤ እነሱ ደግሞ ይህንን ይዘው የተሳሳተ ውሳኔ በማሳለፍ ላይ ናቸው ብለዋል::
“አሁን እነሱ እንደሚሉት ግጭት ቢኖር ኖሮ እኮ በክልሉ ጊዜያዊ መንግሥትም ለማቋቋም አይቻልም ነበር፤ ነገር ግን ሁሉም እንደሚባለው ስላልሆነ በክልል እስከ ወረዳ ድረስ አስተዳዳሪዎች እየተሾሙ ነው፤ በመሆኑም የሚደርሳቸውን መረጃ ማጥራትና ነባራዊ ሁኔታውን መመልከት አለባቸው” ብለዋል ፕሮፌሰር በየነ::
መንግሥት እነሱ የሚሉትን ወይም የሚያደርጉትን ወደጎን በመተው ለህዝቡ የሚጠቅመውን፤ እነሱንም ተዓማኒ የሚያደርገውንና ህዝቡን ከህወሓት አስተሳሰብ አውጥቶ በትክክልኛ መስመር ላይ እንዲገኝ የሚያስችለውን አቅምና እውቀት መጨመር ላይ ጠንክሮ መሥራት እንዳለበትም ፕሮፌሰር በየነ ጠቁመዋል::
በተጨማሪም ህወሓቶች ወጣቱ በሙሉ ከእኛ ጋር ነው እያሉ ልቡን የሚያሸፍቱበትን እንዲሁም እነሱ በእብሪት የሚወጠሩበትን አካሄድ እንዲተው ለማድረግም ከፍተኛ የሆነ ሥራ መሥራትና የተግባር ሰው መሆን እንደሚያስፈልግ ፕሮፌሰር በየነ ተናግረዋል፡፡
እፀገነት አክሊሉ አዲስ ዘመን
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው። ዶክተር ብሩክ ወይሻ ሙሽራነቱን… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው” ሲሉ አጣጣሉት። ፋኖ… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ
- The Wars We Still Can Stop Cameron Hudson (New York TimesMay Opinion Mr. Hudson is a senior fellow in the Africa program at the… Read more: The Wars We Still Can Stop
- ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማልእየተንገዳግደ የፕሪማየር ሊጉን ዋናጫ ባያነሳም ኤፍ ኤ ካፕን ጨምሮ ሌሎች ዋንጫዎችን መውሰድ የቻለው ማንችስተር ዩናይትድ ለዩሮፕያን ሊግ ፍጻሜ… Read more: ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማል
- ያለ ኪልያን ምባፔ ለሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ የደረሰው ፒኤስጂበኳታራውያን ባለሀብቶች የሚተዳደረው የፈረንሳዩ ሀያል ክለብ ፒኤስጂ በሀገር ውስጥ ያለውን ተደጋጋሚ የበላይነት በአውሮፓ ለማሳየት ከአሰልጣኞች አስከ ስመ ጥር… Read more: ያለ ኪልያን ምባፔ ለሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ የደረሰው ፒኤስጂ