ግለሰቦቹ የመቐለ ነዋሪ ናቸው።
5 የወርቅ መስቀሎችን ከመቐለ ወደ ዓዲግራት ወስደው ሊሸጡ ሲደራደሩ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የዓዲግራት ፓሊስ ፅ/ቤት አስታውቀዋል።
የዓዲግራት ከተማ ፓሊስ ዋና አዛዥ የማነ ኪዳኑ ፥ ” ቅዳሜ ግንቦት 10 ቀን 2016 ዓ/ም የግል ተበዳይ ከመቐለ ወደ ሽረ ከተማ የወርቅ መስቀሉን ጭኖ በመውሰድ ላይ ሳለ ነው ተጠርጣሪዎቹ ሰርቆቱን ፈጽመው የተሰወሩት ” ብለዋል።
ግለሰቡም በመቐለ ከተማ ለቀዳማይ ወያነ ፓሊስ ፅህፈት ቤት ያመለከተውን መረጃ መነሻ በማድረግ በተካሄደው ክትትል ተጠርጣሪዎች በዓዲግራት ከተማ ውስጥ ሊያዙ እንደቻሉ ገልጸዋል።
ተጠርጣሪዎች የሰረቁትን አንዱ ብር 25 ሺህ የሚያወጣ መስቀል ፤ በ15 ሺህ ሊሸጡት ተሰማምተው በዋጋው ማነሰ የተጠራጠረ ገዢ በኩል መረጃው ወደ ፓሊስ በመድረሱ ግለሰቦች ከነእግዚብታቸው በፓሊስ ቁጥጥር ስር እንደዋሉ የፖሊስ አዛዡ ገልጸዋል።
ግለሰቦቹ 4 ሲሆኑ ነዋሪነታቸውም መቐለ ነው።
የዓዲግራት ፖሊስ ፤ እንዲገዛ ግብዣ የቀረበለት ግለሰብ ጊዚያዊ ጥቅም እና ትርፍ ሳያሸንፈው ለፓሊስ ያደረገው ትብብር ሌላው እጅግ አርአያ የሚሆነው ሲል አወድሷል።
መረጃው ይህ ሆኖ ሳለ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ” የዓዲግራት ወጣቶች የሆኑ ከቤተክርስቲያን ቤተመቅደስ ውስጥ ንዋየ ቅዱሳን ዘረፉ ” እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው።
@tikvahethiopia