አሸባሪው ህወሃት ለትግራይ ክልል የሚላከው የሰብዓዊ ድጋፍ እንዳይጓጓዝ ማስተጓጎሉና ስላሳ የሚጠጉ እህልና ቁሳቁስ የጫኑ ተሸከርካሪዎች እንዳያልፉ ከባድ መሳሪያ በመተኮስ መንገስድ መዝጋቱ ተገለጸ። መንግስት በአፋር በኩል የትህነግ ሃይል ድንበር አልፎ ሲመጣ ለምን ዝምታን እንደመረጠ አልተገለጸም። ይሁንና ክልሉ የጸጥታ ሃይሉና ሕዝቡ እንዲዘጋጅ አሳስቧል።
ኢዜአ እንዳለው ለትግራይ ክልል የሚላከው የሰብዓዊ ድጋፍ በአፋር በኩል ወደ መቀሌ ሲጓጓዝ የአሸባሪው የህወሃት ቡድን አካባቢውን በከባድ መሳሪያ በመደብደብ መንገድ ዘግቷል። መንግስት ወደ ትግራይ ክልል ሰብዓዊ ድጋፍ በተገቢው መልኩ ለማዳረስ የተናጥል ተኩስ ማቆሙ ተከትሎ ወደ አጥቂነት የተዛወረው አሸባሪው ቡድን ይህን ተግባሩን እንዲያቆም የገሰጸው አካል እንደሌለ መንግስት በተደጋጋሚ እያስታወቀ ነው።
ለትግራይ ክልል ሰብዓዊ ድጋፍ እየቀረበ መሆኑን የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በይፋ ባስታወቀበትና ተጨማሪ የኬላ ጣቢያዎችን በማቋቋም ፍተሻውን በማጣደፍ እርዳታ ቶሎ ቶሎ ወደ ተረጂዎች እንዲደርስ እየሰራ መሆኑንን ባመለከተበት ወቅት አሸባሪው ሃይል አፋርን በከባድ መሳሪያ የሚደበድብበት ምክንያት ግልጽ አይደለም። ይሁን እንጂ አቶ ጌታቸው በጤና ሆነው ከሚናገሩት አግባብ ውጭ አንደበታቸው እየተጎተተ ለቪኦኤ ” በወልቃይት በኩል እርዳታ እንዲገባ እናደርጋለን” ካሉት ጋር ሊገናኝ እንደሚችል ግምት አለ።
ዛሬ በአፋር ክልል በኩል ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎችን የጫኑ 60 ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ ክልል እየተጓዙ ሳለ የአሸባሪው ህወሃት ቡድን ተኩስ በመክፈት እንዳይጓጓዝ መንገድ መዝጋቱ ኢዜአ ሲዘግብ መንገዱ እንዲከፈት ምን ጥረት እንደተደረገ የትኛውንም ወገን ጥቀሶ ያለው ነገር የለም።
ለትግራይ ክልል የሚሂድ የእርዳታ ቁስና ምግብ ነክ የሆነ ተፍትሾ እንዲያልፍ ሰርዶ 60 እና ሚሌ ኬላዎች ላይ እየተሰራ ቢሆንም፤ አሸባሪው ህወሃት በዞን አራት ያሉ የአፋር ፖሊስና ልዮ ሀይል አባላትና ማህበረሰብን በከባድ መሳሪያ እየደበደበ “ወደ ትግራይ የሚሄድ እርዳታ አይኖርም” በማለት ሰርዶ ኬላ ላይ መዝጋቱን ከአካባቢ የተገኙ ምንጮች ለኢዜአ ተናግረዋል።
ህወሃት የተኩስ አቁም ውሳኔውን “አልቀበልም” በማለት ግጭቱን ወደ አፋር ክልል ለማስፋት እየሰራ መሆኑም ታውቋል። በቅርቡም መንግስት ሁኔታዎች በማመቻቸቱ ለክልሉ ሰብዓዊ ድጋፍ የጫኑ 61 ከባድ ተሽከርካሪዎች ትግራይ ክልል መድረሳቸው ይታወሳል።
ከዚህ ውስጥ 34ቱ ምግብ ነክ ድጋፎችን የጫኑ ሲሆን፤ 26 ተሽከርካሪዎች ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን የጫኑ ሲሆኑ፤ ከ47 ሺህ ሊትር በላይ ነዳጅ የጫነ አንድ ከባድ ተሽከርካሪም መቀሌ መድረሱ ተዘግቧል።
በአፋር ክልል ያለውን መንገድ ማስተጓጎል የተፈለገው በውልቃይት በኩል ድንበሩ እንዲከፈት ያለውን ግፊት ለመጨመር ሆን ተብሎ የተደረገ እንደሆነ የሚገልጹ አሉ። ትህነግ በወልቃይት በኩል ያለውም ግምብ ማለፍ ስለማይቻለው በአፋር በኩል ችግር በመፍጠር በወዳጆቹ አገራት አማካይነት የሱዳን ድንበር እንዲከፈትለት ተጨማሪ ጫና ይፈጥራል ተብሎ ይገመታል። በሌላ በኩል ከመንግስት በኩል ከወታደራዊ ጠቀሜታ አንጻር አሸባሪ ቡድኑ ወደ አፋር ሜዳማ ቦታ እንዲወጣ ይፈለጋል የሚሉም አሉ። እነዚህ ክፍሎች አክለው እንደሚገልጹት ሳይሆን ይህ ሃይል አፋርን ወሮ የጅቡቲን መንገድ ለማስተጓጎል ህልም እንዳለው፣ ወደ አሰብም የማምራት እቅድ እንዳለው ለወዳጆቹ መረጃ መስተቱን የሚያውቁ እየተናገሩ ነው።
- Ethiopia Prioritizes Exploiting Lowland Area Potentials for Irrigation Dev’t, Says MILLs MinisterMinister of Irrigation and Lowlands (MILLs) Abraham Belay emphasized expansion of irrigation and exploiting the lowland areas of potential that has been… Read more: Ethiopia Prioritizes Exploiting Lowland Area Potentials for Irrigation Dev’t, Says MILLs Minister
- ምንጩ ያልታወቀ ንብረት የሚወረስበት ረቂቅ አዋጅ ጫጫታ አስነሳ፤ ብሄራዊ ምክር ቤቱ በሺህ የሚቆጠር ጥቆማ ደርሶታል“በኢትዮጵያ ሌብነት ወይም ሙስና የከፋ ደረጃ ላይ ደርሷል” የሚለው ዜና አያከራክርም። ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ሌብነት፣ ሌቦች ” ሲሉ የሚጠሩት ይህ አሳሳቢ ጉዳይ ዋና… Read more: ምንጩ ያልታወቀ ንብረት የሚወረስበት ረቂቅ አዋጅ ጫጫታ አስነሳ፤ ብሄራዊ ምክር ቤቱ በሺህ የሚቆጠር ጥቆማ ደርሶታል
- ሀሰተኛ ክስና ማስረጃ የሚያስከትለው የሕግ ተጠያቂነትሰዎች ሌሎች ሰዎችን በሀሰት ከሰው የማስቀጣት፣ ያልተገባ ጥቅም የማግኘት ወይም ሀሰተኛ ማስረጃ በማቅረብም ሆነ በሀሰት ቀርቦ የመመስከር አዝማሚያ በስፋት ይስተዋላል። በተለይ በአሁኑ… Read more: ሀሰተኛ ክስና ማስረጃ የሚያስከትለው የሕግ ተጠያቂነት
- ስኳር ያለባቸው ነፍሰ ጡር እናቶች ኢንሱሊንን ሆድ ላይ መወጋት ይችላሉ?በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ5 እናቶች አንዷ በእርግዝና ጊዜ ለሚከሰት የስኳር ህመም ተጋላጭ ናት። የእናት ጤንነት እና የጽንስ ደህንነትን ለማረጋገጥ ስኳርን በጥብቅና በጊዜ… Read more: ስኳር ያለባቸው ነፍሰ ጡር እናቶች ኢንሱሊንን ሆድ ላይ መወጋት ይችላሉ?
- Ethiopia MoU agreement will open a new page for the Horn of Africa connectivity,The Minister of Transport and Logistics of the Federal Government of Ethiopia, H.E Alemu Sime, said that the agreement between the Republic… Read more: Ethiopia MoU agreement will open a new page for the Horn of Africa connectivity,