እንቡዝ ሰው የሚሠራውንና የሚናገረውን በጤነኛ አእምሮ መረዳት አይቻልም። ጤነኛ አእምሮ በተጠየቅ፣ በሞራል ሕግ፣ በመረጃ፣ በማስረጃ፣ በሐሳብ ሙግት፣ ወዘተ. ነው የሚረዳው። እንቡዝ ጋ ይህ ሁሉ የለም። መቅበዝበዝ፣ መስከርና ማበድ አንድ ላይ ሆነው የሚፈጥሩት ሰብእና ነው።
በገድለ ተክለ ሃይማኖት የምናገኘው ሞተለሚ የተባለው የዳሞት ንጉሥ ለ25 ዓመታት እንቡዝ ሆኖ መኖሩን ይነግረናል። እንቡዝ የሚለውን ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ሲተረጉሙት፦ በቁሙ ልቡ የጠፋ፣ የተነበዘ፣ ነባዛ፣ ንብዝ፣ ቅብዝብዝ፣ ሰካር፣ እብድ፡፡ ሰብእ እንቡዛን፡፡ ብእሲት እንብዝት፡፡ እንቡዛነ ልብ ወድንቅዋነ እዝን (ኢሳ፳፭፡ ፭፡፡ ፶፬፡ ፮፡፡ መጽ፡ ምስ) ይሉታል። “ቅብዝብዝ ሰካር፣ እብድ” በሚሉት ነው አለቃ ለመበየን የሞከሩት።
ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን ታሪክ በጻፉ ጊዜ ሁሉ “እንቡዝ” የሚለውን “Insane” ብለው ነው የሚተረጉሙት። ኦክስፎርድ የእንግሊዝኛ መዝገበ ቃላት “Insane” የሚለውን ሲፈታ “in a state of mind which prevents normal perception, behaviour, or social interaction; seriously mentally ill.”
ይላል።
ሞተለሚ እንቡዝ ከሆነ በኋላ ያደረገው ነገር ይሄንን ትርጉም ያጠናክረዋል። ሥራው ያገኘውን ሁሉ ማጥፋት ነበር። ዓለም ልትጠፋ የሚገባት፣ ነገር ግን በደካሞች ምክንያት ሳትጠፋ የቀረች ትመስለው ነበር።
እንቡዝን ለመግለጥ አለቃ ኪዳነ ወልድ የተጠቀሙባቸውን ቃላት መመርመር የተሻለ ነገሩን ያሳየናል። መቅበዝበዝ – የመንፈስ አለመረጋጋት ነው። ይሄንን መጀመሪያ የተጠቀመው ቃየል ነው። ቃየል ወንድሙን በግፍ ከገደለ በኋላ መንፈሱ ያልተረጋጋ በመሆኑ ቅብዝብዝ ነበር። ወያኔም ገና ከጅምሩ መንገዱ የቃየል ነበር። ሰካር የአእምሮ መናወዝ ነው። በተጠጣ አስካሪ ነገር የሚመጣ ነው። ወያኔ ጎሰኝነት የሚባል አስካሪ መጠጥ ወስዷል። እብደት የልቡና መናወጽ ነው። ሥነ ልቡናዊ በሽታ ነው።
እንቡዝ ሰው የሚሠራውንና የሚናገረውን በጤነኛ አእምሮ መረዳት አይቻልም። ጤነኛ አእምሮ በተጠየቅ፣ በሞራል ሕግ፣ በመረጃ፣ በማስረጃ፣ በሐሳብ ሙግት፣ ወዘተ. ነው የሚረዳው። እንቡዝ ጋ ይህ ሁሉ የለም። መቅበዝበዝ፣ መስከርና ማበድ አንድ ላይ ሆነው የሚፈጥሩት ሰብእና ነው።
ወያኔ እንቡዝ ስለሆነ ለጤነኛ ሰው የሚሰጡ ነገሮች አይስማሙትም። የሚናገረውና የሚሠራው ከሰብእና ውጭ የሆነው በንብዘቱ ምክንያት ነው። ለምን አደረገ? ብትሉ ንዴቱ እናንተን ያሳምማችኋል እንጂ ወያኔ አይሰማውም። ያንን ሁሉ ጥፋት ሠርቶ፣ ያንን ሁሉ ወጣት አስፈጅቶ ፈገግ ይላል። ለምን ቢሉ? እንቡዝሰ እንቡዝ ውእቱ። እንቡዝ ምን ብታደርጉት እንቡዝ ነው።
By Daniel kebret
- Ethiopia Prioritizes Exploiting Lowland Area Potentials for Irrigation Dev’t, Says MILLs MinisterMinister of Irrigation and Lowlands (MILLs) Abraham Belay emphasized expansion of irrigation and exploiting the lowland areas of… Read more: Ethiopia Prioritizes Exploiting Lowland Area Potentials for Irrigation Dev’t, Says MILLs Minister
- ምንጩ ያልታወቀ ንብረት የሚወረስበት ረቂቅ አዋጅ ጫጫታ አስነሳ፤ ብሄራዊ ምክር ቤቱ በሺህ የሚቆጠር ጥቆማ ደርሶታል“በኢትዮጵያ ሌብነት ወይም ሙስና የከፋ ደረጃ ላይ ደርሷል” የሚለው ዜና አያከራክርም። ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ሌብነት፣ ሌቦች ” ሲሉ የሚጠሩት… Read more: ምንጩ ያልታወቀ ንብረት የሚወረስበት ረቂቅ አዋጅ ጫጫታ አስነሳ፤ ብሄራዊ ምክር ቤቱ በሺህ የሚቆጠር ጥቆማ ደርሶታል
- ሀሰተኛ ክስና ማስረጃ የሚያስከትለው የሕግ ተጠያቂነትሰዎች ሌሎች ሰዎችን በሀሰት ከሰው የማስቀጣት፣ ያልተገባ ጥቅም የማግኘት ወይም ሀሰተኛ ማስረጃ በማቅረብም ሆነ በሀሰት ቀርቦ የመመስከር አዝማሚያ… Read more: ሀሰተኛ ክስና ማስረጃ የሚያስከትለው የሕግ ተጠያቂነት
- ስኳር ያለባቸው ነፍሰ ጡር እናቶች ኢንሱሊንን ሆድ ላይ መወጋት ይችላሉ?በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ5 እናቶች አንዷ በእርግዝና ጊዜ ለሚከሰት የስኳር ህመም ተጋላጭ ናት። የእናት ጤንነት እና የጽንስ ደህንነትን… Read more: ስኳር ያለባቸው ነፍሰ ጡር እናቶች ኢንሱሊንን ሆድ ላይ መወጋት ይችላሉ?
- Ethiopia MoU agreement will open a new page for the Horn of Africa connectivity,The Minister of Transport and Logistics of the Federal Government of Ethiopia, H.E Alemu Sime, said that the… Read more: Ethiopia MoU agreement will open a new page for the Horn of Africa connectivity,
- “ወደ ቅድመ 2010 እንመለስ” ሲባል?”ቅድመ 2010″ ምን ነበር? እንዴትስ ነበር?It is with the strongest possible terms that We say NO to any such cognitive bias of “rosy… Read more: “ወደ ቅድመ 2010 እንመለስ” ሲባል?”ቅድመ 2010″ ምን ነበር? እንዴትስ ነበር?
- “በኢትዮጵያ የኒውክሌር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ማዕከል ለመገንባት እየተሰራ ነው”የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 25ኛ መደበኛ ስብሰባ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን የ2016 ዓ.ም የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም ገምግሟል፡፡… Read more: “በኢትዮጵያ የኒውክሌር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ማዕከል ለመገንባት እየተሰራ ነው”
- ወልቃይት – ትህነግ ከ2 ሚሊዮን በላይ የተፈናቃይ ዝርዝር አቀረበ፤ ተቀባይነት አለገኘምከጦርነቱ ጋር ተያይዞ የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ ቀደመው ቀያቸው እንዲመለሱ በተደረሰው ስምምነት መሰረት ከወልቃይት አካባቢ የተፈናቀሉ መሆናቸውን ገልጾ ትህነግ… Read more: ወልቃይት – ትህነግ ከ2 ሚሊዮን በላይ የተፈናቃይ ዝርዝር አቀረበ፤ ተቀባይነት አለገኘም
- ይህንን የህዝብ ድምጽ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ይወቀው፣ መንግስት ይስማው!!ወትሮ ከጥፋቱ የማይማረውና ከግጭት አዙሪት ውጭ ህይወት የሌለው አሸባሪው ህወሃት ከራያ አካባቢወች ለቆ እንዲወጣ የራያ ህዝብ በተለያዩ ከተሞች… Read more: ይህንን የህዝብ ድምጽ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ይወቀው፣ መንግስት ይስማው!!