የዩክሬን ቁልፍ ደረጃዎች
- በአውሮፓ ቁጥር አንዱ ከፍተኛ ዩራኒየም ክምችት አላት
- ቲታኒየም ማዕድን ክምችት ከአውሮፓ 2ኛ ከዓለም 10ኛ
- በማንጋኒዝ ማዕድን ክምችት ከአለም ሁለተኛ፤ መጠኑም የአለማችንን 12% ክምችት ድርሻ ይሸፍናል።
- በብረት ማዕድን ክምችት ከዓለም 2ኛ ስትሆን መጠኑም 30 ቢሊዮን ቶን፤
- በሜርኩሪ ማዕድን ሀብት ክምችት ከአውሮፓ 2ኛ፤
- የሼል-ጋዝ ክምችት መጠን ከአውሮፓ 3ኛ ከአለም 13ኛ
- [በአጠቃላይ] በተፈጥሮ ሀብቶች ጅምላ ዋጋ ከአለም አራተኛ፤
በግብርና
▪️ዩክሬን ያላት ለም የእርሻ መሬት መጠን ከአውሮፓ 1ኛ ነው።
▪️የጥቁር-አፈር መሬት ሀብቷ ከአለም ሶስተኛው ሲሆን የአለምን 25% ድርሻ ይወስዳል።
▪️የሱፍ ዘይትና ራሱን ሱፍን ወደ ውጭ በመላክ ከዓለም ቁጥር አንዷ ዩክሬይን ናት።
▪️በማሽላ corn አምራችና ላኪነት ከአለም ሶስተኛ፤
▪️ዩክሬይን በድንች ምርት ከዓለም 4ኛዋ ደገኛ ሀገር ናት።
▪️በአጃ ምርት ከዓለም 5ኛ፤
▪️በንብ ማነብ ከዓለም 5ኛ ናት። አመታዊ ምርቷ 75,000 ቶን
▪️የጫጩት እንቁላል በማምረት ከዓለም 9ኛ
▪️ዩክሬን የእርሻ ምርት ለ600 ሚሊዮን ሰዎች የምግብ ፍላጎት ያሟላል፤
ዩክሬን በኢንዱስትሪ
▪️ከአውሮፓ 2ኛውና ከአለም 4ኛው ግዙፍ የጋዝ ማስተላለፊያ ቧንቧ መሰረተ-ልማት በዩክሬን የሚገኝ ነው።
▪️በኒዩክሌር ማብላያዎቿ Installed capacity ከአውሮፓ 3ኛ ከዓለም 8ኛ
▪️ዩክሬን ያላት የባቡር ኔትወርክ ከአውሮፓ 3ኛ ሲሆን ከአለም 11ኛው ነው። ርዝመቱ 21,700 ኪ.ሜ፤
▪️የመገናኛ ቴክኖሎጂዎችን በማምረት ከአሜሪካና ፈረንሳይ በመቀጠል ከአለም ሶስተኛዋ፤
▪️በብረት ማዕድን እክስፖርት ከዓለም 3ኛ ትልቋ ላኪ ናት፤
▪️ለኑክሌር ኃይል ማመንጫዎች የሚሆነውን ተርባይን ኤክስፖርት በማድረግ ከአለም 4ኛዋ፤
▪️የሮኬት መተኮሻ አምርታ በመላክ ከአለም 4ኛዋ፤
▪️በሸክላ ኤክስፖርት ከአለም 4ኛ፤
▪️በቲታኒየም ኤክስፖርት ከአለም 4ኛ
▪️የመከላከያ ኢንዱስትሪ ምርቶችን ወደ ውጭ በመላክ በዓለም 9ኛ ደረጃ
▪️በብረት ምርት ከአለም 10ኛዋ ስትሆን መጠኑም 32.4ሚሊየን ቶን ነው።
Esleman Abay የዓባይልጅ ✍️