የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ሃይል በአላማጣ ዙሪያ ይዞታውን ሲያጠናክር ከርሞ አላማጣ ከተማን ለመያዝ ሰፊ ሃይል አሰልፎ መነሳቱ ተሰማ። መከላከያ አልፈቀደሞ። የመንግስትን ውሳኔ አልተሰማም። በአፋር በኩል ግጭት መቀስቀሱና የትግራይ ሃይሎች ሶሶት ቀበሌዎች ዘልቀው ወደ አፋር ክልል መግባታቸው እየተገለጸ ሲሆን ሁለቱም ዜናዎች በክልሉ መንግስት አልተረጋገጡም። የክልሉ ጊዜያዊ ርዕሰ መስተዳድር ትህነግ ባደረገው ስብሰባ ከአላማጣ አካባቢዎች የትግራይ ሃይል መውጣቱን አስታወቁ።
ብልጽግናና ትህነግ በመቀለ ባደረጉት ሶስተኛ ስብሰባቸው “በቅርቡ በራያ የተፈጠረውን የግጭት ክስተት በተመለከተ በዝርዝር ውይይት በማካሄድ፣ ክስተቱ መፈጠር ያልነበረበትና ከጀመርነው ዘላቂ ሰላም የማረጋገጥ ሂደት ጋር የሚቃረን እንደሆነ መግባባት ላይ ደርሰናል” ባሉ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ይህ ዜና መሰማቱ “ምን እየሆነ ነው” የሚል ጥያቄ አስነስቷል።
እማኞች እንዳሉት ከሆነ ከተማዋን እየተቆጣጠረ ያለው የመከላከያ፣ የፌደራል ፖሊስና የአካባቢው የጥበቃ ሃይል በጋር የከለከሉት የትግራይ ታጣቂ ሃይል ይህ ዜና እስከተጻፈ ድረስ ሃይል ለመጠቀም ተኩስ ስለመክፈቱ የተባለ ነገር የለም። ይሁን እንጂ ከጀርባው ሰፊ ሃይል አሰልፎ መጠጋቱን እማኞች ገልጸዋል።
በአላማጣ ከተማ የተወሰኑ ደጋፊዎችን በማነሳሳት “ህዝብ ይፈልገናል ” በሚል የትግራይ ታጣቂዎች አላማጣን ለመያዝ መነሳታቸውን ሉዓላዊ ሚዲያ አስታውቋል። ይህንኑ ተከትሎ ውጥረቱ አይሎ እንዳለም ጠቁሟል።
አቶ ጌታቸው ረዳ በኤክስ ገጻቸው የትግራይ ሃይሎች ያሉዋቸው ታጣቂዎች አላማጣ ከተማ አቅራቢያ ካሉ ሁለት የገጠር ቀበሌዎች መውጣታቸውን አስታውቀዋል። ይህም የሆነው በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት የፌደራል መንግስትና የአማራ ክልል የፕሪቶሪያው ስምምነት ተግባራዊ እንዲሆን ነው ብለዋል። በዚሁም መሰረት ከትግራይ የተፈናቀሉ ወደ ቀያቸው ተመልሰው የሚሰፍሩበት አግባብ ሊተገበር ጫፍ መደርሱን አመልክተዋል።
አቶ ጌታቸው ይህን ቢሉም፣ የትግራይ ሃይሎች አላማጣን፣ ባላን፣ ራያን፣ ዛራን፣ ኦፍላንና ኮረምን ይዘዋል። እማኞችን በመጠቀስ አቶ ጌታቸው መረጃ ስር የተሰጡ ምላሾች እና በሚታወቁ የማህበራዊ ገጾች እንደሚታየው የትግራይ ሃይሎች ሃይል ተጠመዋል። የአቶ ጌታቸው ተኤክስ ገጽ ዜና ለውጭ አገር ሃይላት ሆን ተብሎ የተዘጋጀ እንደሆነም ተመልክቷል።
ይህንኑ ተከትሎ የአማራና ክልል ባለስልጣናት ከፌደራል መንግስት ጋር ንግግር ላይ መሆናቸውም ተሰምቷል። ይሁን እንጂ መገሃድ የአምራ ክልልም ሆነ የፌደራሉ መንግስት በጉዳዩ ላይ በይፋ የሰጡት መግለጫ የለም።
ይህንን ዜና ተከትሎ በወልቃይት በኩል ህዝብ፣ የአካባቢው አስተዳደር ሚሊሻና ታጣቂዎች ዙሪያ መለስ ዝግት አድርገው በንቃት እንደሚጠብቁ፣ ትንኮሳ ከተሞከረ አጻፋውን እንደሚመልሱ እየተገለጸ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በራያ በራያ አዘቦ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ሰባት ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎ ፤ የትግራይ ሃይሎች አጻፋ ጥቃት መክፈታቸው ተሰምቷል። ሶስት ቀበሌዎችን አልፈው መግባታቸው፣ ይህም ሲሆን ራሳቸውን በደንብ እንዳዘጋጁ የተነገረላቸው የአፋር ታጣቂዎች ምላሽ ሰጥተው ከሁለቱም ወገን ሰዎች መሞታቸው ተሰምቷል።
በአፋር ክልል መጋሌ ወረዳ ቶምሳ ቀበሌ ውስጥ ሰው የተገደሉ ንጹሃን መኖራቸውን የሚጠቁሙ የክልሉ አቂዎች፣ በስፍራው ከሚኖሩ አርብቶ አደሮች ላይ ዘረፋ መፈጸሙንና ህዝብ በስጋት መፈናቀሉን እየገለጹ ነው። እነዚህ ወገኖች ቀደም ሲል በራያ አዘቦ የተገደሉትን ንጽሃን አስመልክቶ ሁለቱ ክልሎችና ፌደራል መንግስት በጋራ መክረው አንድ ነገር ላይ ሳይደርሱ የትግራይ ሃይሎች ወደ ብቀላ ማምራታቸውን ነቅፈዋል። አሁንም ግጭቱ ሳይሰፋ በስከነ መንፈስ መነጋገሩ እንደሚበጅ አመልክተዋል።
“ይህ ካልሆነ በአፋርም የንፁሃን ደም ሲፈስ ዝም ብሎ የሚያይ የለምና ነገሮች መልካቸውን ይቀይራሉ” ሲሉ የሚገልጹት የማህበራዊ አንቂዎች እንጂ የክልሉ መንግስት ያለው ነገር የለም። የአፋርም ሆነ የትግራይ ህዝብ ጦርነት እንደሰቻቸው በመግለጽ አካሄዱን የነቀፉም ጥቂት አይደሉም።
“በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደርና በትህነግ መካከል ያለው የስላጣን ሽኩቻ ተካሮ አንዱ በአንዱ ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻው በግላጭ እየተካሄደ ከመሆኑም አልፎ ጎራ ለይተው እስከመገዳደል እንዳይደረስና የተገኘው አንጻራዊ ሰላም እንዳይደፈርስ ብዙዎቹ የክልሉ ነዋሪዎች ስጋታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ” ሲል የጀርመን ድምጽ ከመቀለ መዘገቡ ይታወሳል።
የጊዚያዊ አስተዳደሩ ምክትል መሪ ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ ቀደም ባሉት ቀናት ችግር መኖሩን አምነው በውይይት የሚፈታ እንጂ ወደ ሌላ የእርስ በርስ ግጭት የሚያመራ እንዳልሆነ ማስታወቃቸውም አይዘነጋም።
ቀደም ሲል እሳቸው ይህን ቢሉም በድጋሚ የጀርመን ድምጽ ራዲዮ ከመቀለ ራሳቸውን ጀነራሉን ጠቅሶ እንዳስታወቀው ሽኩቻው የስልጣን ነው። ሽኩቻው ውሎ አድሮ ገሃድ በመውጣቱ ህዝብ የርስ በርስ መገዳደል እንዳይከሰት ስጋት ላይ መውደቁን አምልክቷል።
“በዚህ መነሻ የትግራይ ሃይሎችን የሚያዘው ማን ነው?” የሚለው የሰሞኑ ጥያቄ ዳግም አገርሽቷል። ተፈናቃዮችን በቅድሚያ ወደ ቀድሞ መኖሪያቸው መመለስና ቀሪውን ጉዳይ ሰክኖ በመነጋገር ቋሚ መፍትሄ ለማፈላለግ ስምምነት መደረጉ በተሰማ ሳምንት ጊዜ ውስጥ በአላማጣ ሊደረግ የታሰበው የተፈራውን ግጭት ሊያስነሳ እንደሚችል ስጋቱን አብሶታል።