የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ2 ሺህ 700 በላይ አጠራጣሪ የፋይናንስ ማጭበርበር ጥቆማዎች እንደደረሱትና አንድ መቶ ሰባ ሰባቱን ለሕግ አካላት ማስተላለፉን ገለጸ። ይህ የተገለጸው አገልግሎቱ ከፌዴራል የፍትህና ህግ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር አዳማ ባዘጋጀው መድረክ ላይ ነው።
የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን አማረ እንደገለጹት አገልግሎቱ የሀገሪቷ የፋይናንስ ደህንነት ለማረጋገጥ ባንኮችና እንሹራንሶችን እንዲሁም ከማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሰራ ነው።
በተለይ በታክስ ማጭበርበር፣ ከህጋዊ የፋይናንስ ተቋማት ውጭ የሚንቀሳቀስ የውጭ ምንዛሪ ዙሪያ ከፍትህ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብርና ቅንጅት እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
በዚህም ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከቀረቡት 2 ሺህ 700 አጠራጣሪ የፋይናንስ ጥቆማዎች ውስጥ 177 የሚሆኑትን አጠራጣሪ ጥቆማዎች በመለየትና በመተንተን ለህግ አካላት ማስተላለፉን ዋና ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል።
በተጨማሪም በህገ ወጥ መንገድ የተገኘውን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ መጠቀም ወንጀሎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከ166 አገሮች ጋር መረጃ መለዋወጥ ተችሏል ብለዋል።
የተቋሙን አሰራር የማሻሻልና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግ ሪፎርም በመከናወን ላይ እንደሚገኝም አቶ ሙለቀን ተናግረዋል። መድረኩ ተግባር ተኮር የሆነ የፋይናንስ ደህንነትን ማረጋገጥ፣ በዘርፉ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል ተጨማሪ አቅም እንደሚፈጥርም ገልጸዋል።
የፌዴራል የፍትህና ህግ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዘካርያስ ኤርጉላ በበኩላቸው ተቋሙ የሀገሪቱን የፋይናንስ ደህንነት ለማረጋገጥ በኦፕሬሽንና ወንጀሎችን በጋራ መከላከል ላይ በትብብር እንደሚሰራ አስታውቀዋል።
በዚህም ሽብርን በገንዘብ መደገፍና በህገ ወጥ የተገኘውን ገንዘብና ሀብት ህጋዊ አስመስሎ መጠቀም ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በጋራ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።
”ህግን ማስከበርና ወንጀልን ከመከላከል አንፃር ከአገልግሎቱ ጋር በቅንጅት እንሰራለን” ያሉት ምክትል ዳይሬክተሩ፤ ከፖሊስ፣ ከአቃቤ ህግ፣ ከባንኮችና ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት ጋር በመሆን ተባብረው እንደሚሰሩም ተናግረዋል።
መድረኩ የዘመኑን የቴክኖሎጂና ስልቶችን በመጠቀም በፋይናንስ ዙሪያ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን በቅንጅት ለመከላከል ያግዛል ያሉት አቶ ዘካርያስ፣ ከፋይናንስ ውጭ በማዕድን፣ በብረታ ብረትና ሌሎች ሀብቶች ላይ ጭምር የሚፈፀሙ የማጭበርበርና የቅሸባ ወንጀሎችን ለመከላከል በጋር እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
በመድረኩ ላይ ከተለያዩ የፋይናንስ ተቋማት፣ ከፍትህና ህግ ማስከበር የተውጣጡ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።
- የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራኢትዮጵያ ከጅቡቲ ማግኘት የነበረባትን የባህር በር ሳታገኝ እንዲሁም በተመሳሳይ ኤርትራ ስትሄድ ለመውጪያም ሆነ ለመግቢያ ይጠቅማት የነበረን የባህር በር ሳታገኝ መቅረቷ ልብ ያደማል። የፖለቲካ ሳይንስን በቅጡ የሚገነዘቡ ምሁራን የራስ ዱሜራን ጉዳይ ወደ አደባባይ ይዘውት… Read more: የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራ
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የሆነው ሁሉ እረፍት እየነሳቸው ያሉ ይመስላል፡፡ በጦርነቱ ወቅት ሲነገሩ የነበሩ ቁልፍ ሚስጢሮችን ሲከላከሉና ሲያመክኑ ቆይተው አሁን ላይ ራሳቸው ይፋ እያደረጉ… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው። ዶክተር ብሩክ ወይሻ ሙሽራነቱን አቋርጦ ነብስ ታድጓል፡፡ ” ለሆስፒታሉ ብቻ ሳይሆን ለአከባቢውም ብቸኛ ስፔሻሊስት ስለነበርኩ ሌላ አማራጭ አልነበረኝም ”… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው” ሲሉ አጣጣሉት። ፋኖ አስራ ሶስት አመራሮችን መርጦ ድርጅት መመሰረቱ ተገለጸ። መሪ አለመሰየሙ እያነጋገረ ነው። በቅርቡ የትምህርት ሚኒስቴር አማካሪ… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ
- The Wars We Still Can StopCameron Hudson (New York TimesMay Opinion Mr. Hudson is a senior fellow in the Africa program at the Center for Strategic and International Studies in Washington. Conflict, famine and a great-power competition are… Read more: The Wars We Still Can Stop
- ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማልእየተንገዳግደ የፕሪማየር ሊጉን ዋናጫ ባያነሳም ኤፍ ኤ ካፕን ጨምሮ ሌሎች ዋንጫዎችን መውሰድ የቻለው ማንችስተር ዩናይትድ ለዩሮፕያን ሊግ ፍጻሜ ከቶትንሃም ጋር ደርሷል። ማንችስተር አትሌቲክን በድምሩ ሰባት ለአንድ፣ ቶትነሃም ቦዶን በድምሩ አራት ለአንድ አሸንፈው ነው… Read more: ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማል
- ያለ ኪልያን ምባፔ ለሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ የደረሰው ፒኤስጂበኳታራውያን ባለሀብቶች የሚተዳደረው የፈረንሳዩ ሀያል ክለብ ፒኤስጂ በሀገር ውስጥ ያለውን ተደጋጋሚ የበላይነት በአውሮፓ ለማሳየት ከአሰልጣኞች አስከ ስመ ጥር የእግር ኳስ ኮከቦች ወደ ፓሪሱ ቤት ቢኮበልሉም የሚፈለገው የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ ሊመጣ አልቻለም። ኔይማርን ከባርሴሎና፤… Read more: ያለ ኪልያን ምባፔ ለሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ የደረሰው ፒኤስጂ