በተደጋጋሚ የሰላም ጥሪ መቅረቡን ተከትሎና ሕዝብ በግጭቱ ሳቢያ የሚያሰማው ምሬት እየጨመረ በመጣበት በአሁኑ ሰዓት ” የአማራ ክልል ህዝብ ወኪል ሆነን ለድርድር እንቀመጣለን” ያሉ ሁለት ቡድኖች ለድርድር ጥያቄ ማቅረባቸው ተሰማ። በመንግስት በኩል ለጊዜው የተባለ ነገር የለም።
ተቀማጭነታቸውን በውጭ አገር ያደረጉ ሁለት ቡድኖች ለድርድር አማራን ወክለው እንደሚቀመጡ በስነድ የታገዘ ጥያቄ ማቅረባቸውን የአዲስ አበባ ዘጋቢያችን ነው ያመለከተው።
ለጥንቃቄ ሲባል ስማቸው ሳይገለጽ መረጃውን እንዳገኘ የገለጸው ተባባሪያችን እንዳለው ሁለቱ ቡድኖች እርስ በራሳቸው ስለመስማማታቸው የታወቀ ነገር የለም።
“አንደኛው በቅርቡ የአማራ ህዝባዊ ሃይል የሚባለ ነገር የለም። ፈርሷል” ከሚሉት ውገን እንደሆኑ ያመለከቱት የዜናው ባለቤቶች ሁለቱም ቡድኖች ከአንድ አካባቢ መሆናቸውን አመልክተዋል።
የአማራ ህዝብ ወኪል እንደሆኑ የሚገልጹት የተለያዩ ክፍሎች የየራሳቸውን ደጋፊ ሚዲያና የግል የማህበራዊ አውዳቸውን በመጠቀም እርስ በርስ እየተወቃቀሱና እየተዘላለፉ ባለበት ወቅት የሰላም ትሪውን ተቀብለው ለድርድር ጥያቄ ያቀረቡት ቡድኖች አላማቸው ስለመሳካቱ ዜናውን ያቀበሉት ጥርጣሬ አላቸው።
በከፍተኛ ደረጃ የገንዘብ ዝርፊያ እንደተፈጸመ በመጥቀስ በግልጽ እነ ሃብታሙ አያሌው ላይ በሰነድ የተደገፈ መረጃ እየወጣ መሆኑንን ተከትሎ በተፈጠረው ጸብ ” መረጃ ቲቪ የማን ነው? ዓላማውስ ምንድን ነው?” ሲል ምላሽ ከሰጠው ሃብታሙ አያሌው ጋር ግንኙነት ያላቸው ታጣቂዎች በዚህ ቡድን ውስጥ ስለመኖራቸው ተጠይቆ ” ለጊዜው ግልጽ አይደለም” ተብሏል።
ከትግሉና ከገንዘብ ማሰባሰቡ ራሳቸውን እንዳገለሉ የተናገሩት ሻለቃ ዳዊ ወልደ ጊዮርጊስ ከአንደኛው ወገን ጀርባ ሊኖሩ እንደሚችሉ ፍንጭ የተሰጠ አለ። ይሁን እንጂ የመረጃው ባለቤቶች ዝርዝር መረጃ ለመስጠት አልወደዱም።
ሻለቃ ዳዊት በቅርቡ በአንከር የዩቲዩብ ገጽ ላይ መሳይ ከሚፈልገው አውድ በመውጣት ራሳቸውን ከትግሉ ማግለላቸውን ማስታወቃቸው አይዘነጋም።
የንግግር ጥያቄውን ያቀረቡት ሁለቱም ቡድኖች በአገር ቤት ከሚታወቁት የፋኖ መሪዎች ከየትኞች ጋር ግንኙነት እንዳላቸው መረጃ ለሰጡት ክፍሎች ጥያቄ ቢቀርብም ትንሽ መታገሱ አንደሚበጅ አመልክተዋል።