በሚቀጥሉት ሳምንታት ተጨማሪ አገራት ለፍልስጤም እውቅና እንደሚሰጡ በመግለጽ ዛሬ አየርላንድ ፣ ኖርዌይና ስፔን ለፍልስጤም ነጻ አገርነት እውቅና እንደሚሰጡ ይፋ አደረጉ።
አገራቱ ውሳኔውን የወሰኑት ጦርነት ውስጥ ያሉት እስራኤልና ፍልስጤም ለሚካሄደውን ድርድር አጋዥ ይሆናል በሚል ምክንያት መሆኑንን አመልክተዋል።
የአየርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳይመን ሃሪስ፣ የኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዮናስ ጋሀርና የስፔን ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ ውሳኔያቸውን ተከትሎ በሰጡት መግለጫ ለፍልስጤም ዕውቅና ለመስጠት መወሰናቸውን አስታውቀዋል። ስፔንና ኖርዌይ በሚቀጥለው ሳምንት ውሳኔያቸውን ይፋ አድርገው ለፍልስጤም እውቅና ለመስጠት ቀጠሮ ይዘዋል።፡
አገራቱ ይህን ቢሉም እስራኤል በውሳኔያቸው ተቆጥታ በተጠቀሱት አገራት የሚገኙ አምባሳደሮቿን ጠርታለች። ውሳኔው ይበልጥ አለመረጋጋትን የሚፈጥር እንደሆነም አስታውቃለች።
የኖርዌይ መንግስት በመንግስታዊ ድረገጹ ምክንያቶቹን ዘርዝሮ፣ ሽብርና አሸባሪነትን እንደሚያወግዝ ጠቅሶ ኖርዌይ የፍልስጤምን መንግስትነት አውቃለች ሲል በይፋ አውጇል “Norway recognises Palestine as a state”
ቀኑንን ለፍልስጤም እጅግ ታሪካዊ እንደሆነ ተመልክቷል። ሶስቱም አገራት በየፊናቸው ይህን እርምጃ ለመሰዳቸው ምክንያታቸውን አስታውቀዋል። የአየርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲሞን ሃሪስ ዛሬ አየርላንድ ፣ ኖርዌይ እና ስፔን ለፍልስጤም የነጻ ሀገርነት እውቅና እንደሰጡ ይፋ አድርገዋል። ይህንኑ ውሳኔያቸውን ተከትሎ አገራቱ ማንኛውንም አይነት ብሔራዊ እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል።
የስፔኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ እና የኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት ኢስፔን ባርት ኢይድ ሀገራቸው ከግንቦት 28 (እ.ኤ.አ) ጀምሮ ለፍልስጤም ግዛት እውቅና እንደሚሰጡ በይፋ አሳውቀዋል።
የስፔኑ ጠ/ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ ፥ ” ምንም እንኳን ከአሸባሪው ቡድን #ሃማስ ጋር የሚደረገው ውጊያ ህጋዊ ቢሆንም ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ለፍልስጤም የሰላም ፕሮጀክት የላቸውም ” ብለዋል።
የኖርዌይ ጠ/ ሚኒስትር ጆናስ ጋህር ስቶር ለፍልስጤም እውቅና ካልተሰጠ በመካከለኛው ምስራቅ ምንም ሰላም ሊኖር እንደማይችል አስታውቀዋል። አቋሙ በሂደት የመጣ የኖርዌይ የጸና አቋም ውጤት እንደሆነም አመልክተዋል። የኖርዌይ መንግስት ለዚህ ውሳኔ የደርሰበትን አግባብ በኢፊሳል የመንግስት ገጹ ላይ ዘርዝሯል።
በአካባቢው የሚፈጸመውን ተደጋጋሚ ጥቃት አስመልክቶ ” ሽብር የተፈፀመው በሃማስና የሁለት ሀገር መፍትሄን በማይቀበሉ እንዲሁም የእስራኤልን መንግሥት በማይደግፉ ታጣቂ ቡድኖች ነው ” ብለው ፍልስጤም እንደ አገር እውቅና ብታገኝ ይህ ችግር ሊወገድ መፍትሄ እንደሚያመጣ አመልክተዋል።” ፍልስጤም ነጻ አገር የመሆን መሠረታዊ ህጋዊ መብት አላት ” ሲሉም ድምጻቸውን አሰምተዋል።
የፍልስጤም #የነጻ_ሀገርነት እውቅና መስጠት በይፋ ከተሰማ በኃላ የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር #በኖርዌይ እና #በአይርላንድ የሚገኙ አምባሳደሮችን በአስቸኳይ ወደ እስራኤል እንዲመለሱ አዘዋል።
ዜናውን ተከትሎ በድጋፍና በተቃውሞ በርካታ መረጃዎች እየወጡ ሲሆን፣ በኖርዌይ የአክራሪው ፓርቲ ተቃውሞ እንደሚያሰማ ይጠብቃል።