በአፍላ እድሜው የተለያዩ የፈጠራ ውጤቶችን በመስራት ታዋቂነትን አትርፏል፡፡ በፈጠራ ሥራዎቹ 14 የተለያዩ ሽልማቶችን ማግኘት ችሏል፤ የፈጠራ ባለሙያና የድርጅት ባለቤት ወጣት ኢዘዲን ካሚል፡፡

ወጣት ኢዘዲን ካሚል የመጀመሪያውን ሀገር አቀፍ የሳይንስና ምህንድስና የፈጠራ ስራዎች ውድድር ካሸነፈ በኋላ በርካታ እድሎች እንደተከፈቱለት ይናገራል፡፡
በ2010 እና 2011 ዓም የሀገር አቀፍ የሳይንስና ምህንድስና የፈጠራ ስራዎች ውድድር አሸናፊ እንደነበር የሚገልጸው ወጣት ኢዘዲን፣ የፈጠራ ሥራዎቹ የተሻለ ሀብት፣ የሥራ እድል ለመፍጠርና የማህበረሰቡን ችግር ለመፍታት ያስቻለው መሆኑን ይናገራል፡፡
ወጣቱ የፈጠራ ሥራዎቹን ተግባራዊ ወደ ማድረግ መግባቱን በመግለጽ፣ አሁን ላይ የቴክኖሎጂና ፕሮሞሽን ድርጅት ባለቤት ነው። ለ18 ሥራተኞችንም የስራ ዕድል ፈጥሯል።
ከ400 በላይ የሀገር ውስጥና ዓለምአቀፍ ተቋማት የድርጅቱን የሶፍት ዌር ውጤቶች እየተጠቀሙ እንደሚገኝ የሚገልጸው ወጣቱ፣37 በላይ ሀርድዌር ሥራዎች ላይ መስራቱንና 14 ሽልማቶች ማግኘት መቻሉን ያስረዳል፡፡
የአሜሪካ እዳ ከ36 ትሪሊየን ዶላር ማለፉ ተነገረ
አመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የ2 ትሪሊየን ዶላር ጭማሪ ያሳየው የአሜሪካ እዳ፥ ከጥር እስከ ህዳር 2024 በ6 በመቶ ማደጉ ተዘግቧል።
47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት እንዲሆኑ በቅርቡ የተመረጡት ዶናልድ ትራምፕ የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ ስብራቶች የሚጠግኑና በፍጥነት የሚያድገውን እዳ መቆጣጠር የሚያስችሉ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ይጠበቃል።
በትራምፕ የመጀመሪያ የስልጣን ዘመን የአሜሪካ እዳ በ8 ትሪሊየን ዶላር መጨመሩን የሚያነሱ ተንታኞች ግን ስጋታቸውን አጋርተዋል።
Via : alain
በቀብር ስፍራ በመገኘት የቲክቶክ ቪዲዮ ሲሰሩ የቆዩ ወጣቶች በፖሊስ ተያዙ‼️
በቀጨኔ ወረዳ 4 ቀጨኔ ዘላቂ ማረፊያ በሚባለው የቀብር ቦታ በመገኘት ሙዚቃ በመክፈት የቲክቶክ ቪዲዮ እየሰሩ ሲለቁ የነበሩ ወጣቶች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ።
በቁጥጥር ስር ከዋሉት ወጣቶች መካከል አንዱ ድርጊቱን የፈፀምነው ተመልካችን ለማዝናናት ብለን ነበር ተጠያቂ እንደሚያደርግ ባለማወቃችን ስህተት ፈፅመናል ብሏል።
ድርጊታቸው በኢትዮጵያ የወንጀል ህግ አንቀጽ 493 የሙታንን ሰላም እና ክብር መንካት በሚል እንደሚያስጠይቅ ከዚህ ቀደም መምህር፣ ጠበቃና የህግ አማካሪ አበባየሁ ጌታ መረጃን አጋርቶ ነበር ።
ሂዝቦላ የሚዲያ ኃላፊው በእስራዔል ተገደሉ
የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር የሂዝቦላህ የሚዲያ ሃላፊ የሆነውን ሞሃመድ አፊፍ ሰይድን መግደሉን አስታውቋል፡፡
የእስራኤል ጦር በማዕከላዊ ቤሩት እና በሰሜን ጋዛ የሚፈጽመው የአየር ጥቃት ተጠናክሮ መቀጠሉ ተመላክቷል፡፡
ጦሩ በዛሬው ዕለት በማዕከላዊ ቤሩት የሂዝቦላህ ደጋፊ የሆነ የፖለቲካ ፓርቲ ሕንጻ ላይ የአየር ጥቃት መፈጸሙን ሬውተርስ ዘግቧል፡፡
በጥቃቱም ለልዩ ስብሰባ ሕንጻው ውስጥ የነበረው የሂዝቦላህ የሚዲያ ሃላፊ ሞሃመድ አፊፍ መገደሉ ነው የተገለጸው፡፡
ሞሃመድ አፊፍ በቅርቡ በእስራኤል ጥቃት የተገደለው የቡድኑ የቀድሞ መሪ ሃሰን ነስራላህ የሚዲያ ጉዳዮች አማካሪ እንደነበር ተጠቁሟል፡፡
በሊባኖስ በሚዲያ ግንኙነት ጉዳዮች ዙሪያ አንቱታን ያተረፈ የቡድኑ ቁልፍ ሰው እንደነበርም ዘገባው አመላክቷል፡፡
በሌላ በኩል የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት በሰሜን ጋዛ በፈጸመው ጥቃት የ72 ዜጎች ሕይወት ማለፉን ተሰምቷል፡፡
ቤይት ላሒያ በተሰኘ ግዛት በሚገኝ ባለብዙ ፎቅ መኖሪያ ሕንጻ ላይ በተፈጸመው ጥቃት ከሞቱት በተጨማሪ በርካታ ዜጎች መጎዳታቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት አስታውቀዋል፡፡
ዩክሬን – የሩስያ ከፍተኛ ድብደባ
የዩክሬን-ሩሲያ ጦርነት በይፋ ከተጀመረ ወዲህ ሩሲያ ከፍተኛ የተባለውን የአየር ድብደባ የዩክሬን የሀይል ማመንጫዎችን ኢላማ በማድርግ ጥቃት መፈጸሟ ተነገረ፡፡
በዚህም ሩሲያ 120 ሚሳኤሎችን እንዲሁም 90 ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በመጠቀም በሁሉም የዩክሬን ግዛቶች ጥቃት መፈጸሟን የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘሌንስኪ አስታውቀዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ሞስኮ የሀገሪቱን የሀይል ማመንጫ መሰረተ ልማቶችን ኢላማ በማድርግ ጥቃቱን መፈጸሟን ነው የገለፁት፡፡
በዚህም ጥቂት በማይባሉ የዩክሬን አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ሀይል መቋረጡን ይፋ አድርገዋል፡፡
በሌላ በኩል ዘሌንስኪ የሀገራቸው አየር መከላከያ 140 የሚጠጉ ኢላማዎችን ማምከኑንም ተናግረዋል፡፡
ሩሲያ በሁሉም የዩክሬን ግዛቶች በሰነዘረችው በዚህ ጥቃት በማይኮላይቭ ግዛት ሁለት ሴቶች የተገደሉ ሲሆን÷ በመካከለኛው ዩክሬን ደግሞ ሁለት የባቡር መንገድ ሰራተኞች መገደላቸውን ሀገሪቱ አስታውቃለች፡፡
በዩክሬን የሚገኝ አንድ ከፍተኛ የሀይል ዘርፍ ኩባንያ የሩሲያ ጥቃት ከፍተኛ ውድመት ማስከተሉን ጠቁሟል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡