ሰሞኑን የመሬት መንቀጥቀጥ ሲስተዋልባቸው ከነበሩት አካባቢዎች አንዱ በሆነው ዱለቻ ወረዳ ዶፋን ተራራ ላይ ዛሬ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ተከስቷል መባሉ ትክክል እንዳልሆነና የተከሰተው እንፋሎትና ውሃ መሆኑ ተጠቁሟል።
በስህተት እሳተጎሞራ ቢባልም በፍተኛ ሙቀት ያለው እንፋሎትና በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን በአፋር ክልል የጋቢ ረሱ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አብዱ ዓሊ ለፋና ዲጂታል መናገራቸው ተመልክቷል። ይሁን እንጂ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ምን እንደሆነ ዜናው አላብራራም።
በዶፋን ተራራ ላይ ምን እንድተከሰተ የሚያሳ ቪዲዮ
የርብርቡን ዓይነት ዝርዝር ባያስረዱም በተቀናጀ ሁኔታ ወደ በስፍራው የሚኖሩ ወደ ጊዜያዊ መጠለያ የማጓጓዝ ሥራ እየተሠራ እንደሆነ አመልክተዋል።
የመሬት መንቀጥቀጡ አሁንም በተደጋጋሚ መቀጠሉን ጠቅሰው፣ እሳቸው “የእሳተ ገሞራ ” ያሉትን የዕንፋሎት ክስትተ ዛሬ መታየቱን ገልጸዋል። የተከስተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱም ከሰሞኑ ከፍያለ እና ጠንካራ እንደነበር ገልጸዋል።
በስምጥ ሸለቆ ውስጥ የቀጠናውን የጂኦግራፊ አቀማመጥ ሊቀይር የሚችል ሁኔታ ወይም የመሬት ለውጥ ሊከሰት እንደሚችል ታላላቅ የሚባሉ የሳይንስ ውጤቶች ማስታወቅ ከጀመሩ ከራርሟል።
አስገራሚ የሆነ የመሬት ቅርጽ ለውጥ ምስራቅ አፍሪቃ እንደሚከተሰት የሚያትተውና ሰሞኑን የወጣው ጽሁፍ፣ በመሬት ውስጣዊ እንቅስቃሴ ወይም tectonic forces አማካይነት አዲስ ውቅያኖስ እንደሚፈጠር ያትታል። ይህም የሚሆነው በምስራቅ አፍቂቃ የሰምጥ ሸለቆ አምብርት ውስጥ ነው። A dramatic transformation is unfolding in Africa as tectonic forces drive the continent toward the formation of a brand-new ocean. At the heart of this shift lies the East African Rift System ሊንኩን ተጭነው ያንብቡ። ኢትዮጵያ ለውጡ የሚታይባት ናት።