የኬንያ ብሄራዊ ፖሊስ ‘የኦሮሞ ነጻት ሰራዊት’ን ኢላማ ያደረገ ዘመቻ በማርሳቢትና ኢሲዮሎ መክፈቱን አስታውቋል
የኬንያ ብሄራዊ ፖሊስ በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል አካባቢ በሚገኙ ‘የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት’ን ኢላማ ያደረገ ዘመቻ በይፋ መጀመሩን አስታውቋል።
የኬንያ ብሄራዊ ፖሊስ በኤክስ ይፋዊ ገጹ ባጋራው መረጃ በማርሳቢትና ኢሲዮሎ አካባቢ በሚንቀሳቀሱ የኦሮሞ ነጻት ሰራዊት ላይ ዘመቻ መክፈቱን ገልጿል።
ልዩ የተባለው የደህንነት ዘመቻው በተከታታይ የድንር ዘለል ወንጀሎች ተጠያቂ የሆነው የኦሮሞ ነጻት ሰራዊት ላይ ያነጣጠረ መሆኑንም ፖሊስ በመግለጫው አስታውቋል።
የኬንያ ብሄራዊ ፖሊስ ትናንት ሰኞ ጥር 26 በሰጠው መግለጫ “ወንጀለኞችን የማስወገድ ኦፕሬሽን” በማርሳቢትና ኢሲዮሎ ውስጥ በተለይም በሶሎሎ፣ ሞያሌ፣ ሰሜን ሆር እና መርቲ አካባቢዎች ተደብቀው የሚገኙ የኦሮሞ ነጻት ሰራዊት ወንጀለኞችን ለማጥፋት ያለመ መሆኑን አስታውቋል።
የኬንያ ፖሊስ የኦሮሞ ነጻት ሰራዊትን በህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ እና አደንዛዥ እጽ ዝውውር፣ ህገወጥ የሰዎች ዝውውር፣ የኮንትሮባንድ እቃዎች ንግድ፣ ህገ-ወጥ ማዕድን ማውጣት፣ የጎሳ ግጭቶችን በማነሳሳት እና ሰዎችን አግቶ ገንዘብ በመቀበል ወንጀሎች ይከሳል።
የኦሮሞ ነጻት ሰራዊትን በፈረንቹ 2005 በቱርቢ የተካሄደውን እልቂት ጨምሮ በተለያዩ ግጭቶች ውስጥ ተሳትፏል በሚልም ይከሰሳል።
‘የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት’ በኬንያ ብሄራዊ ፖሊስ ለቀረቡበት ውንጀላ እስካሁን በይፋዊ ገጹ የሰጠው ምላሽ የለም።
የኢትዮያ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ባለንት ጥር ወር መጀመሪያ ላይ ወደ ናይሮቢ አቅንተው ከኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር መነጋራቸው ይታወሳል።
የኬንያው የብሔራዊ መረጃ አገልግሎት ዳይሬክተር ጄኔራል ኑረዲን ሐጂ በተገኙበት በተደረገው ውይይት ላይም ኢትዮጵያ እና ኬኒያ ሽብርተኝነትን ጨምሮ የተደራጁ ወንጀሎችን በጋራ መካላከል በሚችሉበት አግባብ ላይ ምክክር መደረጉም በወቅቱ ተነግሯል።
ምንጭ፡- አል አይን
TIPS
Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security