የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ “የአሜሪካ መርከቦች በስዊዝ እና ፓናማ ቦዮች ያለምንም ክፍያ ማለፍ አለባቸው” አሉ። ተፈሳሚ እንዲሆንም መመሪያ ሰጡ። እሳቸው ይህን ማለታቸውን ተከትሎ ግብጽ ሌላ አታብቂኝ ውስጥ እንደምትገባ ተሰማ።
በሁለቱ ቁልፍ የዓለማችን አቋራጭ የውሃ ላይ መተላለፊያዎች የአሜሪካ ወታደራዊ እና የንግድ መርከቦች ሳይከፍሉ መግባት እና መውጣት ይኖርባቸዋል በሚል በትሩዝ ማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል ፕሬዚዳንቱ።
እነዚህ ቦዮች ያለአሜሪካ መቀጠል የማይችሉ ናቸው ያሉት ትራምፕ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ይህን ጉዳይ አሁኑኑ እንዲከታተሉ ጠይቄቸዋለሁ ብለዋል፡፡
ከዚህ ባሻገርም ግብጽ ልክ እንደ ፓናማ ከአሜሪካ ጋር እሰጥ አገባ ውስጥ ልትገባ የምትችልበትን ሁኔታ ካለ አሉታዊ አጋጥሚ ሊፈጥር ይችላል የሚል መረጃም ተጋርቷል፡፡
ዶናልድ ትራምፕ ወደ ስልጣን ከመጡበ ጊዜ አንስቶ ፓናማን እና ግሪንላንድን እንጠቀልላለን በሚል በተደጋጋሚ ሲዝቱ ቆይተዋል፡፡
አሁን ላይ ደግሞ የግብጹን ስዊዝ ቦይ ማማተር መጀመራቸው የካይሮን ፖለቲከኞች እንቅልፍ የሚነሳ ጉዳይ እንደሚሆንባቸው ይጠበቃል፡፡
በመካከለኛው ምስራቅ የአሜሪካ ቁልፍ አጋር ለሆነችው ግብጽ የትራምፕ ሀሳብ ዱብ ዕዳ ሆኖባታልም ተብሏል።
ከ1970ዎቹ አንስቶ በየዓመቱ ረብጣ ቢሊዮን ዶላር ከአሜሪካ የምታገኘው ግብጽ በስዊዝ በኩል ትራምፕ መጥተውባታል፡፡
ግብጽ በዓመት እስክ 9 ቢሊዮን ዶላር ገንዘብ መርከቦች ሲተላለፉ ክፍያ በማስፈጸምና በሌሎች ምክንያቶች ከስዊዝ ቦይ ገቢ እንደምትሰበስብ ይታወቃል፡፡ የትራምፕ ውጥን እውን ከሆነ ካይሮ እና ዋሽንግተንም እጣ ፈንታቸው ልክ እንደ ዴንማርክ እና ፓናማ ውጥረት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
ኢትዮሪቬውን ከታች ባሉት ማስፈንጠሪያዎች የከተሉ – የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ @ethioreview
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ ethioreview
ኤክስ ፡ twitter