እዛም እዚህም በብሄርና በሰፈር ተቧድነው ኢትዮጵያና ሕዝቧን መከራ እያበሉ ያሉ ባንዳዎች ወደ ቀልባቸው እንኳን ቢመለሱ ማስተባበል የማይችሉት መረጃዎች ይፋ እየሆኑ ነው። ከመረጃዎች መካከል ኢል ፋትህ ኢርዋ (El Fateh Irwa) የተባለው ሰላዩ ሱዳናዊ የትህነግና ሻዕቢያ ወዳጅ ኑዛዜ፣ እንዲሁም የወይዘሮ ኬርያ ኢብራሂም ምስክርነት ቀዳሚውን የሚይዝ የሰሞኑ መነጋገሪያ ሆኖ በየማህበራዊ ሚዲያዎች እየተዘዋወረ ነው።
የአባይ ግድብን አስመልክቶ የግብጾችን ሴራ በማጋለጥ የሚታወቀው ኡስታዝ ጀማል በሽር ቃል በቃል (እዚህ ላይ ይጫኑና ቪዲዮውን ያድምጡ) የሱዳናዊውን ኑዛዜ እየተረጎመ እንዳስረዳው የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፉወርቂ ድብቅ ዓላማና ለአማራ ህዝብ ያላቸው ጥላቻ መጥንና ጥልቀቱ በቃላት የሚገለጽ አይደለም። ይህ በኡሳታዝ ቃል በቃል እየተተረጎመ ይፋ የሆነው መረጃ ” ኢሳያስ ኢትዮጵያን ይወዳሉ፤ ለኢትዮጵያ ያስባሉ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ የብሄር ፖለቲካ እንዳይሰፍን ደጋግመው ምክር ይሰጡ ነበር ” ወዘተ እያሉ ሲቀሰቅሱ ለነበሩና አሁንም “አብረን እንሰራለን፣ ሞት ከኢሳያስ ጋር” ለሚሉ ማጣፊያ የሚያሳጣቸው ሆኗል።

መንግስትን፣ መሪዎችን ወይም ፓርቲን፣ ወይም የፓርቲን ፖለቲካ መጥላትን ከብሄራዊ ጥቅም መለየት አቅቷቸው የኢትዮጵያን ቀንደኛ ጠላት ለሚያመልኩ ምላሽ የሚሆነው ይህ መረጃ በትክክል ምስክር ከሚሆን ግለሰብ መገኘቱ ደግሞ “እነዚህ ወገኖች ይህን ሃቅ እንዴት ያስተባብሉታል?” የሚል ጥያቄም እያስነሳ ነው።
በሱዳን መንግስት ተወክሎ ኢትዮጵያን የባህር በር ያሳጣትን የትህነግን የክህደት ትጥቅ ትግል አስፈላጊውን ትጥቅና ስንቅ ሲያቀርብ የነበረው ሱዳናዊ ኢል ፋተህ ኢዋር ይባላል። ይህ ሰው ኢህአዴግ አዲስ አበባ እንዲገባ ሲደረግ፣ አቶ መለስና ባልደረቦቻቸውን ከካርቱም ወደ አዲስ አበባ እራሱ በሚያበራት አወሮፕላን ማጓጓዙ ይታወሳል። ከሳምንት በፊት ህይወቱ ላለፈው ሱዳናዊ ሰላይ ትህነግ ውለታ ቆጥራ ከመቀለ መግለጫ አውጥቷል። ለቅሶም መቀመጡ ተመልክቷል።
የሱዳን ስለላ ተቋም አባል የነበረው ኢል ፋተህ ኢርዋ ሳይሞት የሰጠውን ምስክርነት እየተረጎመ ያቀርበው ኢትዮጵያዊ ኡስታዝ ጀማል ይፋ እንዳደረገው የኤርትራ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ “ጭፍን የአማራ ጥላቻ ነበረው” ሲል የቀደመው ወዳጃቸው ምስክርነቱን ሰጥቷል።
ኢሳያስን “ከትህነግ ጋር ቢቀላቅል ምን አልባትም መሪ ሊሆን ይቻላል” ሲል የተደመጠው ሱዳናዊ ሰላይ፣ ምስክርነቱን የሚሰጠው መቀለ ሆኖ፣ በስም በሚጠራው ቤትና ስፋራ ያየውን ፣ የሰማውንና ምልልስ ያደረገበትን ቃላት በመጠቀም ነው።
ኢሳያስ መሪ ሊሆኑ ይችሉ እንደነበር ካወሳ በሁዋላ ዋናው ችግሩ “ኢሳያስ ቅጥ አንባሩ የጠፋና በአማራ ጥላቻ የታወረ መሆኑ ነው” ይላል። አስከትሎም የሚገርመው በዛ ደረጃ ከሚጠላቸው ጋር አሁን ላይ ሕብረት መፈጠሩ እንደሆነ ይገልጻል።

“በአማራ ጥላቻ የታወረ” ሲል የገለጻቸውን ፕሬዚዳንት ኢሳያስ፣ አንድ ጊዜ መቀለ እራት ሲበሉ ከነበረው ገጠመኝ ጋር አያይዞ ሱዳናዊው ሰላይና ባለሃብት ምስክረነቱን ይሰታል።
ለውለታው ትህነግ አራት ኪሎ ከገባ በሁዋላ ረብጣ ብር ሸልሞት ቱጃር ነጋዴ ሆኖ ይህቺን ዓለም እንደተሰናበተ የተነገረለት ሱዳናዊ ሰላይ፣ “አንዴ እኔ፣ ኢሳያስ፣ መለስ ቃታ የሚባል የድሮ ቤት ውስጥ ቁጭ ብለን እራት እንበላ ነበር” በማለት ትዝብቱን ይጀምራል። ለማስታወስና ምስክርነቱን ለመስጠት አስቀድሞ በወቅቱ ቴክኖሎጂ እንደሌለ፣ ሞባይልና መሰል መረጃ መሰብሰቢያ ቁሶች አለመኖራቸውን ጠቁሞ፣ ኢሳያስ የተናገሩትን ቃለ በቃል መገረም በሚታይበት ፊት ይገልጻል።
ቦታው የወቅቱ ታዋቂ ቪላ እንደሆነ ይጠቁምና፣ እሱ፣ አቶ መለስና ኢሳያስ የነበሩባት ክፍል ውስጥ አንድ ካሴት የሚገባባት የድሮ ቲቪ መሳይ ማጫወቻ መኖሯን ይገልገልጻል።
በጠቀሰው አሮጌ ቲቪ ነገር አንድ ካሴት ከተው የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች ሲጨፍሩ ሲያዩ ነበር። የደቡብ፣ የትግርኛ፣ ጉራግኛ፣ አማርኛ ወዘተ የተለያዩ ጭፈራዎች በየተራ ሲታዩ ነበር። አል ፋተን እንደመሰከረው ልክ የአማርኛ ዘፈን ሲመጣና እስክስታ የሚወርዱ ሲታዩ፣ ኢሳያስ “ኡፍ ምን አመጡብን” በሚል ይወራጩ ነበር። “ኧረ ባክህ ንገራቸው ሌላ ዘፈን ይቀይሩ ይለኝ ነበር”
ይህን ቪዲዮ ቃለ በቃል እየተረጎመ ያቀረበው ኡስታዝ ጀማል በሽርን በማመስገን መረጃውን የሚያሰራጩ እንዳሉት ” ኢሳያስ ኢትዮጵያን ይወዳሉ?” በሚል ሌት ከቀን እንደ ዳዊት ለሚደግሙ ይህ መረጃ አፍረታቸው ነው”
“አሁን ላይ መንግስት ይውደቅ እንጂ ከሻዕቢያ ጋር አብረን እንሰራለን” የሚሉትን ክፍሎች “ባንዳ” ሲሏቸው ” መንግስት ይውደቅ እንጂ ” በሚል በግልጽ ወጥተው በሚናገሩበትና አብረው ኢትዮጵያን እያደሙ ባለበት በዚህ ወቅት የተሰማው ምስክርነት በርካታ ጉዳዮችን ዘወር ብሎ ለመመርመር እድል እንደሰጠ እየተገለጸ ነው።
“ይህን የሚሉ ወገኖች የኢሳያስ ማንነትና ጀርባቸው ድሮም ግልጽ ነው። ኢትዮጵያ ላይ ተቃዋሚ ሲያደራጁ እድሜያቸውን የገፉት ኢሳያስ፣ በውክልና ኢትዮጵያን ማፍረስ፣ ማውደም ዋንኛ ዓላማቸው ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላም ሲሰፍንና በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ሲደረግ ሌላ ካርድ በመሳብ ወደ አማራ ክልል የተወረወሩት ከዚሁ ኢትዮጵያን ሰላም የመንሳት ልክፍት ነው” በማለት አስቀድመው አስተያየት ሲሰጡ የነበሩ “አስቅድሞ ሲነገራቸው ለመማት ያልፈለጉ ምስኪኖች፣ ራሳቸውን የሸጡ ባንዶች፣ እኩል ከጌታቸውና አሳዳሪያቸው ጋር ለምን የፕሪቶሪያ ስምምነት ተፈረመ በሚል በነጋ ጠባ መንጋጋቸውን የሚያላቅቁ የሱዳኑን ሰላይ ምስክርነት ያድምጡ” ብለዋል። ምስክርነቱን ” በወሳኝ ወቅት ለኢትዮጵያ የቀረበ ስጦታ” ብለውታል።
ይህ እየተሰማ እያለ ነው የቀድሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ወ/ሮ ኬሪያ ” ለስልጣን እንጂ ለሌላ ለምንድን ነው?” ሲሉ አሁን ላይ ከሻዕቢያ ጋር እየተደረገ ያለውን ሽርክና ኮንነዋል።
ድርጅታቸው በጥቂት ቆመው የቀሩና በአስተሳሰብ ኃላ በቀሩ ውስን አዛውንቶች እንደሚመራ አመልክተው ” ከሻዕቢያ ጋር ወዳጅነት ማንን አብሮ ለመምታት?” በሚል ጥያቂ አንስተው፣ ሻዕቢያ የፈጸመውን ወንጀል ዘርዝረዋል።
የትህነግ ስራ አስፈጻሚ በመሆናቸው ሻዕቢያ ሊያጣቃቸው ዝግጅት እንዳለው በየጊዜው መረጃ ይቀርብ እንደነበር፣ በዚህም ሳቢያ “ላኪውን እንጂ የሚላከውን አናጠቃም” በሚል ሻዕቢያ ለመቅደም እቅድ እንደነበር የጠቆሙት ወ/ሮ ኬሪያ “ኢሳያስ በፌደራል መንግስት ግብዣ ወደ ጦርነት ግብቷል” የሚሉትን በሙሉ ዝም የሚያስብል፣ የሚያስደነግጥና የፈጠራ ትርክታቸውን የሚንድ አስተያየት ሰጥተዋል መስጠታቸው ከሱዳናዊው ሰላይ መረጃ ጋር ተዳምሮ አየሩን ይዟል።
“የምታወጣው ህገ መንግስት በስልጣን ላይ እያለህ ሳይሆን ስትወርድ ራስህን የምትከላከልበት መሆን ይገባዋል”ሲሉ ለርዕዮቱ ቴድሮስ የገለጹት ወ/ሮ ኬሪያ “አንቀጽ 39 ያለ አንዳች ተኩስ ስንበት የሚደረገበት አንቀጽ ነው በሚል ሲሰጠን የነበረው ስልጣና አላዳነንም” በማለት ትህነግ ራሱ ያወጣውን ህግ፣ ሲሟገትለት የኖረውን አንቀጽ ጠቅሶ ስንብት ማወጅ ሲገባው ስለምን ጦርነት እንደመረጠ እንደማይገባቸው ኬሪያ በቁጭት ሲናገሩ ተደምጠዋል።፡ለወትሮው ነገሮች በፈለገው መንገድ ካልሄዱለት ተናጋሪውን ሲጎትትና ሲራክስ የሚታወቀው ቴዎድሮስ በዚህ ጉዳይ ተጨማሪ ጥያቄ ሳያነሳ ማለፉ ለገባቸው ከፍተኛ ጥያቄ ጭሯል። ለጦርነቱ መንስዔ ሲቀርብ የነበረውን የትህነግ ደጋፊዎች ትርክት አመክኗል።
የቀድሞዋ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉቤ ይህ ከማለታቸው በፊት አቶ ስብሃት ነጋ መቀለ ሆነው ከዳዊት ከበደ ጋር ቃለ ምልልስ ሲያደርጉ ” ልገንጠል ብትል ማን ይፈቅድልሃል” በማለት ዳዊት ላነሳላቸው የመገንጠል ጥያቄ ከሰጡት መልስ ጋር ያገናኙ ወገኖች፣ ኬሪያ ኢብራሂም እነ ጌታቸው ረዳ ሳይቀር የሸፋፈኑትን ጉዳይ እንደገለጡት ገልጸዋል። አክለውም ይህን የመወያያ አጀንዳ በመያዝ የህግ ባለሙያዎችና ጦርነቱን አስቀድመው የተቃወሙ የትግራይ ተወላጆችን በማሰባሰብ እንዲያስተነትኑ ለሚዲያ ሰዎች ጥሪ አቅርበዋል።
“ወ/ሮ ኬሪያ በቃለ ምልልሳቸው ምርጫ ለማድረግ አንድ ዓመት መታገስ ቢቻል ኖሮ ጦርነቱ አይደረግም ነበር” ሲሉ ፓርቲያቸው የፌደራሉን ህግ አለማክበሩን በነቀፌታ አስቀምጠዋል። ይህም ታክቲካሊ የማሰብ ችግር እንደሆነ ገልጸዋል።