የኢትዮጵያ መንግስት መሥመሩን በጠበቀ መልኩ ከአሜሪካ መንግስት ጋር በተለያዩ የአገሪቱ ጉዳዮች ለመነጋገር ዝግጁነት እንደሆነ አስታወቀ። ይህ የተገለጸው ኢትዮጵያ አብዝታ በተቃወመችው “የዲፕሎማሲ አግባብን ያልተከተለ” በተባለው በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የፖሊሲ ንግግርን ተከትሎ ለተነሳ ጥያቄ መልስ በተሰጠበት ወቅት ነው።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢዩ ተድላ ኀሙስ ዕለት ለተለያዩ ሚዲያዎች በሰጡት መግለጫ እንዳሉት መንግስት አግባብ ያለውና መስመሩን የጠበቀ እስከሆነ ድረስ ከአሜሪካ ጋር ለመነጋገር ዝግጁ ነው። በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ በሰሞኑ በአሜሪካን ግቢ ያደረጉትን የፖሊሲ ንግግር መንግስት መስመሩን የሳተና የዲፕሎማሲ አግባብን ያልተከተለ፣ እንዲሁም ዘራፊ፣ ህዝብን ያማረሩ፣ የሚያሰቃዩና የሚያግቱ ድርጅቶችን ከመንግስት ጋር እኩላ ማንሳቱን ጠቅሶ እርምት እንዲደረግ ማሳሰቡ አይዘነጋም።
ቀደም ሲል የአምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ መግለጫ የሁለቱን ሀገራት ወዳጅነትና ታሪካዊ ግንኙነት የሚፃረር ነው ሲል ያጣጣለው የውጭ ገዳይ ሚኒስቴር በዛሬው መግለጫው “መመልከት የሚገባን ጉዳዮች ካሉ በመመካከር አብረን ልንሠራ የምንችል ይሆናል” ሲል ችግሩ የዲፕሎማሲ አግባብንና መስመርን ያለመከተሉ እንደሆነ አመልካቷል። አምባሳደሩ የተኩስ ማቆምን ስምምነትን ጨምሮ በአገሪቱ ውስጥ ጠብ መንጃ ካነሱ ሃይሎች ጋር ሰላማዊ ውይይት እንዲደረግ አሜሪካ አቋሟ እንደሆነ መጥቀሳቸው፣ “ራሱን ፋኖ ብሎ የሚጠራው” ያሉት ሃይል የመንግስትን የሰላም ጥሪ እንደማይቀበል ማስታወቁ እንደማይጠቅመው ማስታወቃቸው ይታወሳል።
የይዘት ልዩነት ካልሆነ በቀር፣ የቁርጠኛነቱ መጠን በለኪያው ቢለያይም መንግስት በተደጋጋሚ የሰላም ጥሪና የእንወያይ ግብዣ በተደጋጋሚ ህዝብ እይሰማ ማቀረቡ አይዘነጋም።
በኢትዮጵያ ለውጡን ተክትሎ የተነሳው የጠብ መንጃ ትግል ቦታን ጊዜ ሳይመርጥ ብሄር በመለየት ለበርካቶች ሞት፣ መፈናቀል፣ ስደትና መከራ ምክንያት የሆነ ግጭት አሁን ድረስ መቀጠሉ ህዝቡን ምሬት ውስጥ እንደከተተ እየተሰማ ነው።
ትህነግ ዳግም ስልጣን ላይ ለመመለስ አፋርና አማራ ክልሎችን ወሮ በነበረበት ወቅት የተስፋፋው የሽፍትነት ይዘት ያለው እንቅስቃሴ አሁን በአንዳንድ አካባቢዎች ወደ ሙሉ ዝርፊያ የተዛወረበት አግባብ ህዝብ ፍጹም እንዲሰላች ማድረጉን በይፋ ከሚሰጡ አስተያየቶች ለመረዳት ይቻልል። ከተለያዩ የቪዲዮ መረጃዎች ለመመልከት እንደተቻለው የህዝብ መገለገያ ንበረቶችና አገልግሎት ምስጫ ጣቢያዎች ወድመዋል። ከጦርነት ያላገገመው አማራ ክልል ዳግም እየፈረሰ እንደሆነ የሚያሳዩ ምስሎች ኤ ምንድን ነው ዓላማዌ የሚል ጥያቄም እያስነሳ ነው።
በዚህና በሌሎች አማሪካና ሃሳብ እንደገባት ጠቅሳ የዕርቅ አሳብ ማቅረቧ ብዙም ችግር እንደሌለው የሚገልጹ ወገኖች መንግስት እልህ ሳይጋባ ለህዝብ ሰላም ሲል አሁን እንዳለው ቀደም ሲል ማሳሰቢያው እንዳለ ሆኖ ቢቀበለው ችግር እንዳልነበረበት ገልጸዋል። አሜሪካ በኢትዮጵያ ጉዳይ ጣልቃ እየገባች ተደጋጋሚ ክህደት መፈጸሟን የሚያስታውሱ ደግሞ የመንግስትን ጥንቃቄና ወዲያውኑ ተቃውሞ ማሰማቱ ትክክል እነደሆነ ጠቁመዋል።
አሜሪካ ዚያድባሬ ኢትዮጵያን ሲወር መርዳቷ፣ ማስታጠቋና ኢትዮጵያ የገዛችውን መሳሪያ መከልከሏ አይዘነጋም። ሄርማን ክኾን የተባሉ አሜሪካዊ ጡረተኛ የጦር መኮንና ዲፕሎማት በሎንደን የኢትዮጵያን መንግስትና ትህነግን ሲያሸናግሉ የሰሩት ግፍና ደባ ዛሬ ኢትዮጵያ ለወደቀችበት የዘር መገዳለል ዋና መንስኤ መሆኑም የሚታወስ ነው።
አሜሪካ ኢትዮጵያ ላይ የምታራምደውን የክህደትና የሴራ ዕቅድ ለማስፈጸም በከፈትችው የአማርኛ፣ ኦሮምኛና ትግርኛ ፕሮግራሞች አማካይነት እንደወቅታዊ አጀንዳዋ “በኢትዮጵያዊያን” አንደበት ስትረጭ ኖራለች። አሁንም እየረጨች ነው። በርካታ ኢትዮጵያዊያን እንደሚሉት ኢትዮጵያ ላይ ተቀጥረው የሚዘምቱና እየዘመቱ ያሉ ወደፊት ታሪክ ያበጥራቸዋል።
አሜሪካ ብቻ ሳትሆን ጀርመንና እንግሊዝ በተመሳሳይ ከኢትዮጵያ ከአብራኳ በወጡ “ልጆቿ” አማካይነት አጀንዳቸውን በሚፈልጉት መጠንና በሚፈልጉት ዓይነት እየረጩ እንደሚገኙ ይታወቃል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ዘወትር የሽግግር መንግስት የሚጠይቁትና ዘር ላይ የተመሰረቱ ድርጅቶችን ያካተተው የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ስብስብ ኮከስ፣ የአሜሪካን ጥሪ በበጎ እንደሚያየው እና መንግሥት “ጥሪውን ተቀብሎ ወደ ሃቀኛ ድርድር እንዲገባ” ድምጻቸውን አሰምተዋል። ‘ፓርቲዎቹ ጠብመንጃ ከያዙት ሃይሎች ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ወይም እንደሌላቸው ሳይገልጹ ድርድር እንዲደረግ በጠየቁበት መግለጫቸው እንዳሉት’
ዘጠኝ የፖለቲካ ድርጅቶችን ያቀፈው ይህ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ስብስብ “ሃቀኛ፣ አሳታፊና ተዓማኒ ሀገራዊ መግባባትና ዕርቅ ለነገ የማይባል የዛሬ ጥያቄ ነው” ባወጡት መግለጫ የአምባሳደሩን ንግግር አወድሰዋል።
ኮከስ የሚታየው የሰብዐዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ረገጣ ከሰላማዊ ህዝብና የፖለቲካ ፓርቲዎች አባላትና ደጋፊዎች ማሳደድ፣ አፈናና እስራት ወደ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እስራትና ግድያ በማደጉና የሰላማዊ ትግል በር መዘጋቱ ን በመግለጫው አስፍሯል። የፓርቲዎች ስብስብ መንግስት ከአሜሪካ የቀረበውን ጥያቄ እና ጥሪ ተቀብሎ “ወደ ሃቀኛ ድርድር እንዲገባ” ብሏል “መንግሥት እንደነዚህ ያሉ ምክሮች ከወዳጅ ሀገራት ሲሰጡ ሁልጊዜ ተከላካይ ሳይሆን፤ በቀና ወስዶ ለሀገሪቱ በሚጠቅም፣ ሰላም እና መረጋጋትን በዘላቂነት ለመፍታት ግብአት አድርጎ እንዲወስድ” ይገባል ብለዋል።